በኢየሱስ ክርስቶስ በማዳኑና በፀጋው የተካፈልነው ህይወትና ኑሮ ታላቅ ብድራት ያለው በእውነትና በፅድቅ ደግሞም በጥንቃቄ ልንኖረው ልንጠብቀውም የሚገባ ነው::
በክርስትና እምነት ውስጥ ካሉት ታላላቅ እውነቶች አምስቱን በዚህ ትምህርት እንማራለን:--
- መዳናችን እጅግ ታላቅ ነው:: ከሞት ወደ ህይወት ከጨለማ ወደሚደነቅ ብርሃኑ የመጣንበት::
- የጌታ እረኝነት:: ነፍሱን ሰለ በጎቹ አሳልፎ የሰጠ መልከምና ታላቅ እረኛ::
- የጌታ የሊቀ ካህንነት ሥራ:: ፍፁም የሆነ የዘላለም ሊቀካህን::
- ታላቅ ብድራት:: ጌታን በማመን የምናገኘው ብድራት እጅግ ታላቅ ነው::
- ታላቅ መጋደል:: በነፃ የተቀበልነው የክርስትና ህይወት ታላቅ መጋደል ያለበት መፅናትንም የሚጠይቅ ነው::
ክርስቶስ የሰራውና እኛም የእርሱ የሆንበት ነገረ እጅግ ታላቅ ነውና ከዚህ ሌላ ተመክህት አይኖረንም:: ሰለዚህ ትምክህታችንን አንጥልም ብድራቱ እጅግ የላቀ ነውና::