Sign up to save your podcastsEmail addressPasswordRegisterOrContinue with GoogleAlready have an account? Log in here.
ዶይቼ ቬለ የዕለቱን ዋና ዋና ዜናዎች ከኢትዮጵያ እና ከመላው ዓለም በየቀኑ ያቀርባል። የኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ፖለቲካዊ እና ኤኮኖሚያዊ ጉዳዮችን ጨምሮ የመላው ዓለምን ውሎ የተመለከቱ ጠቃሚ መረጃዎች በሰባቱም የሣምንቱ ቀናት ከምሽቱ አንድ ሰዓት ከዶይቼ ቬለ ያድምጡ። የዶይቼ ቬለን ዜናዎች በአፕል ፖድካስት... more
FAQs about የዓለም ዜና:How many episodes does የዓለም ዜና have?The podcast currently has 2,943 episodes available.
September 15, 2016የዓለም ዜናከጳግሜ መጨረሻ ጀምሮ የኮንሶ የፀጥታ ኃይላት የተለያዩ ቀበሌዎች ዉስጥ ጥቃት ማድረሳቸዉን የዓይን እማኞች ለዶይቼ ቬለ ዛሬ ገለፁ። እንደ አካባቢ ነዋሪዎች ገለፃ ጥቃቱ ዛሬም ቀጥሎአል። በሽዎች የሚቆጠሩ ተፈናቅለዋል። ኬንያ በሃገሪቱ የሚገኙ የሶማልያ ስደተኞችን ዓለም አቀፍ መለኪያዎችን ባላሟላ መልኩ እያስገደደች በመመለስ ላይ መሆንዋን የመብት ተሟጋቹ ድርጅት፣ «ሂውመን ራይትስ ዎች» ዘገባ አመለከተ። በእርስ በርስ ጦርነት በተጠመደችዉ ሊቢያ 235 ሺህ ስደተኞች ተመዝግበዉ ሜዲተራንያን ለማቋረጥ በመጠባበቅ ላይ ናቸዉ ሲል የተመድ አስታወቀ። የምሽቱን የዓለም ዜና ተከታተሉ!...more11minPlay
September 13, 2016የዓለም ዜናከምሽቱ የዓለም ዜናዎች መካከል፤ ሶማልያ በሠላሳ ዓመት ጊዜ ዉስጥ ለመጀመርያ ጊዜ የአካካቢ ሃገራት ጉባዔን በማስተናገድ ላይ መሆንዋ ተገለፀ። ጉባዔዉ በስፋት ከሚነጋገርባቸዉ ነጥቦች መካከል በተለይ የደቡብ ሱዳን ቀዉስና በቅርቡ በሶማልያ ስለሚካሄደዉ ምርጫ ይሆናል። በጀርመን በሽሊዝቪግ ሆልሽታይን እራሱን «እስላማዊ መንግሥት ብሎ የሚጠራዉ አሸባሪ ቡድን አባላት ናቸዉ ተብለዉ የተጠረጠሩ ሰወስት ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸዉ ተነገረ። አትሌት ታምሩ ደምሴ በርዮ የዓራ ኦሎምፒክ መድረክ የኢትዮጵያ መንግሥትን በመቃወም የተቃዉሞ ምልክትን አሳየ። የተሰኙት ይገኙበታል! የድምፅ ማድመጫ ማዕቀፉን በመጫን ይከታተሉ!...more10minPlay
September 12, 2016የዓለም ዜናበከፊል በእሳት ቃጠሎ በወደመው የቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ስለነበሩ የተወሰኑ እስረኞች እና ስለአደጋው ጥርት ያለ መረጃ ማግኘት እንዳልቻሉ ጠበቆች እና የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ገለጹ፤ፕሬዝዳንት ሳልቫ ኪር፤የቀድሞው ምክትል ፕሬዝዳንት ሪየክ ማቻር እና የጦር ሹማምንቶቻቸው በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በተገደሉበት የደቡብ ሱዳን የርስ በርስ ጦርነት ትርፍ እያጋበሱ ነው ሲል አንድ የምርመራ ሰነድ ወነጀለ፤ሳዑዲ አረቢያ መራሹ ጥምረት በየመን የውሃ ጉድጓድ ላይ በፈጸመው ጥቃት 30 ሰዎች መገደላቸውን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ባለስልጣን አስታወቁ...more9minPlay
September 10, 2016የዓለም ዜናየኢትዮጵያ መንግሥት በአሸባሪነት ክስ ካሰራቸው የኢትዮጵያ የሙስሊሞች ጉዳይ መፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ መሪዎች፥ አባላትና ተባባሪዎች መካከል አስራ ሦስቱ በምህረት መለቀቃቸው ተገለጠ፤በኮንጎ የሚገኘው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ተልዕኮ ድንበር ያቋረጡ ወደ 300 የሚጠጉ የደቡብ ሱዳን አማፅያንን እና ሰላማዊ ዜጎችን ታደገ፤የጀርመን አገር ውስጥ ጉዳይ ሚንስትር ቶማስ ደ ሚዜይር በቡድንና በተናጠል ጥቃት ሊፈፅሙ የሚችሉ ከ500 በላይ እስላማዊ ታጣቂዎች በአገራቸው እንደሚገኙ አስጠነቀቁ፤አሜሪካ እና ሩሲያ ለአምስት አመታት የዘለቀውን የሶርያ ጦርነት ለማብቃት ያለመ የተኩስ አቁም ሥምምነት ላይ ደረሱ።...more9minPlay
September 09, 2016የዓለም ዜናየተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን የኢትዮጵያ መንግስት በተቃዋሚዎች ላይ ከልክ ያለፈ ኃይል መጠቀሙን እንዲያቆም ጫና እንዲያሳድር የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ተቋማት ጠየቁ፤የተ.መ ድርጅት ደቡብ ሱዳን ርዕሠ ከተማ ጁባ ለሚሠፍረዉ አዲስ ሠላም አስከባሪ ጦር ወታደሮች እና ሔሊኮፕተሮች የሚያዋጡለት አገሮች እየፈለገ ነው፤በደቡብ ሱዳን ከፍተኛ ሹማምንት የሚመራው ጦርነት በሐምሌ ወር መባባሱንና የአገሪቱ መሪዎች በነፍጥ ሊፈቱት ያቀዱት ቅራኔ በተለያዩ ጎሳዎች መካከል ውጥረት መፍጠሩን አንድ አንድ ሰነድ ጠቆመ፤የጋቦን ተቃዋሚ የፖለቲካ መሪ ለአገራቸው ሕገ-መንግስታዊ ምክር ቤት የምርጫው ውጤት በድጋሚ እንዲቆጠር አመለከቱ...more9minPlay
September 08, 2016የዓለም ዜናከባድ የጤና መታወክ ያጋጠማቸዉ ከ100 የሚበልጡ የደቡብ ሱዳን መንግሥት ተቃዋሚ ታጣቂዎች የሃገሪቱን ድንበር አቋርጠዉ ወደ ኮንጎ መግባታቸዉ ተገለፀ። በአዉሮጳ ኅብረት የእግር ኳስ ማኅበር የተዘጋጀና ወደ 120 የሚሆኑ ስደተኞች የሚሳተፉበት የእግር ኳስ ግጥሚያ በሚቀጥለዉ ሳምንት ስዊዘርላንድ ዉስጥ እንደሚካሄድ ተዘገበ። ለእግር ኳሱ ግጥምያ ከተዘጋጁት ከነዚህ ስደተኞች መካከል አብዛኞቹ ከኢትዮጵያና ከኤርትራ የተሰደዱ። የአዉሮጳ ኅብረት በሩስያ ላይ የጣለለዉን ማዕቀብ አራዘመ። የሩሲያ መንግሥት በበኩሉ ከኅብረቱ የተጣለበት ማዕቀብ ፍርደ ገምድል ርምጃ ሲል ነዉ የገለፀዉ።...more8minPlay
FAQs about የዓለም ዜና:How many episodes does የዓለም ዜና have?The podcast currently has 2,943 episodes available.