የዓለም ዜና

የዓለም ዜና

Download on the App Store

የዓለም ዜና episodes

  • DW Amharic የኅዳር 28 ቀን 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና
    የዛሬው የዓለም ዜና፤ በቤኒን መፈንቅለ መንግስት መክሸፉን እስራኤል ከሃማስ ጋር ወደ ሁለተኛው ምዕራፍ የተኩስ አቁም ስምምነት እደምትሸጋገር መገለፁን፣ጀርመን በእስራኤል ታሪካዊ ሃላፊነት አለባት ሲሉ መራሄ መንግስት ፍሬድሪሽ ሜርዝ መግለፃቸውን፣ እንዲሁም ሩሲያ ፤በዩክሬን ክሬሜንቹክ ከተማ የአየር ጥቃት መፈፀሟ የሚያስቃኙ ዜናዎችን አካቷል።
    8 min
  • DW Amharic የኅዳር 27 ቀን 2018 የዓለም ዜና
    ዩናይትድ ስቴትስ በኢትዮጵያ፣ ኤርትራ እና ሶማሊያ መካከል “አዲስ ግጭት እንዳይቀሰቀስ መከላከል” ላይ ማተኮር እንዳለባት የፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር ይፋ ያደረገው የብሔራዊ ደሕንነት ፖሊሲ ሰነድ አሳየ። ኢትዮጵያ ከመጪው ሰኞ ጀምሮ የማርበርግ ቫይረስ የሙከራ ክትባት መስጠት ልትጀምር ነው። የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይል በድሮን በፈጸመው ጥቃት 33 ሕጻናትን ጨምሮ 50 ሰዎች መገደላቸውን የሐኪሞች ቡድን አስታወቀ። በደቡብ አፍሪካ በርካታ ተጠርጣሪዎች በከፈቱት ተኩስ ሕፃናትን ጨምሮ 11 ሰዎች መገደላቸውን ፖሊስ ገለጸ። የጀርመን መራኄ መንግሥት ፍሬድሪሽ ሜርስ ወደ እስራኤል እና ዮርዳኖስ አመሩ።
    10 min
  • የህዳር 26 ቀን 2018 ዓ.ም. የዓለም ዜና
    የህዳር 26 ቀን አርዕስተ ዜና
    ዛሬ ያስቻለው የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት፣ በቀድሞው የሰላም ሚኒስቴር ሚንስትር ድኤታ አቶ ታዬ ደንደአ ላይ የ ሰባት ዓመት ከሁለት ወራት ጽኑ እስራት ፈረደ። የአምስት ሺህ ብር መቀጮም ወሰነ
    የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ፓርቲ ኢህአፓ አቅዶ የነበረው ህዝባዊ ስብሰባ መስተጓጎሉን አስታወቀ። የፓርቲውት ስብሰባው የተስተጓጎለው ገዢው ፓርቲ ባሳደረው ጫና ምክንያት ነው ሲል ዛሬ ለዶቼ ቬለ ተናግሯል።
    የሩስያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን እና የህንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ በ23ተኛው የሩስያ ህንድ ጉባኤ የሁለቱን ሀገራት ንግድ ለማስፋትና ለማብዛት ተስማሙ።
    12 min
  • የሐሙስ ኅዳር 25 ቀን፣ 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና
    መቐለ፥ ወታደራዊ እንቅስቃሴ፣ የተኩስ ድምፅና ፍንዳታ ተሰማ፣ ዋሽንግተን፥የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚንሥትር ከጠቅላይ ሚንሥትር ዐቢይ አሕመድ ጋር ተነጋገሩ፣ ጆሐንስበርግ፥ የኬንያው ሣፋሪኮምን የደቡብ አፍሪቃው ግዙፉ የቴሌዶን አገልግሎት አቅራቢ ቮዳፎን ሊጠቀልል ነው፤ ጄኔቫ፣ የዓለም ጤና ድርጅት (WHO) የወባ ወረርሺኝ በዓለም መጨመሩን ዐሳወቀ፣
    11 min
  • የህዳር 24 ቀን 2018 ዓ.ም. የዓለም ዜና
    የህዳር 24 ቀን 2018 ዓ.ም. የዓለም ዜና
    አሜሪካን የጉዞ እገዳ የጣለችባቸውን የ19 ሀገራት ዜጎችን የጥገኝነት ማመልከቻዎች ለጊዜው መቀበል ማቆሟን አስታወቀች። እገዳው የግሪን ካርድ እና የዜግነት ማመልከቻዎችንና ተያያዥ ውሳኔዎች ያካትታል።
    የሩስያ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ለሰላም ፍላጎት ያላቸው እያስመሰሉ ነው በማለት አውሮጳውያን ሲወቅሱ ፑቲን አውሮጳች ሩስያን ከተነኮሱም ከአውሮጳ ጋር ጦርነት ለመግጠም ዝግጁ እንደሆኑ አስጠንቅቀዋል።
    የሦስት ቀናት ጉብኝት ለማድረግ ዛሬ ለንደን ለገቡት የጀርመን ፕሬዝዳንት ፍራንክ ቫልተር ሽታይንማየር እና ለባለቤታቸው ኤልከ ቡዩድንቤንደር ደማቅ አቀበላል ተደረገላቸው።
    11 min
  • የሕዳር 23 ቀን 2018 ዓ/ም የዓለም ዜና
    አርስተ ዜና፤
    -የቀድሞው የሰላም ሚንስቴር ምንስትር ዴታ እና የጨፌ ኦሮሚያ አባል አቶ ታዬ ደንደአ አዲስ የተመሰረቱባቸውን ክሶች ተቃወሙ ።
    -በደቡባዊ ሱዳን የብሔራዊ ጦር ኃይሉ ሳይፈጽመው አልቀረም በተባለ ጥቃት በትንሹ 40 ያህል ሰዎች ተገደሉ።
    -አሜሪካ ይክሬን ውስጥ እየተካሄደ ያለው ጦርነት ፍጻሜ ያገኝ ዘንድ ከሩስያ ጋር ፊት ለፊት ልትነጋገር ነው።
    -የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ከ22 ዓመታት ጥበቃ በኋላ ለአፍሪካ ዋንጫ አለፈ።
    12 min
  • የዓለም ዜና፤ ኅዳር 22 ቀን 2018 ሰኞ
    -በአሜሪካና በዩክሬን መካከል ፍሎሪዳ በተካሄደዉ ውይይት ተስፋ እንዳላቸዉ ትራምፕ ገለፁ።-በአማራ ክልል የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን ባቲ ወረዳ ላለፉት ሦስት ተከታታይ ዓመታት መፍትሔ አጥቶ የዘለቀዉ ግጭት በሽምግልና ስርአት መቋጨቱ ተነገረ።-ደቡባዊ ኢትዮጵያ ውስጥ በተከሰተው የማርበርግ ቫይረስ የስምንት ሰዎች ሕይወት ማለፉን የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።-ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በሚቀጥለዉ በቡድን 20 የመሪዎች ጉባኤ ደቡብ አፍሪቃ አትጋበዝም ማለታቸዉን ራማፎሳ ውድቅ አደረጉ።-በዓለም ዙርያ በርካታ ግጭቶች በሚካሄዱበት በአሁኑ ወቅት የጦር መሳሪያ ኢንዱስትሪዉ ከፍተኛ የጦር መሳርያ ንግድ ገቢን ማስመዝገቡ ተዘገበ።
    12 min
  • DW Amharic የኅዳር 21 ቀን 2018 የዓለም ዜና
    በጦርነት የምትታመሰው ሱዳን “የገጠሟትን ከባድ ፈተናዎች ለማሸነፍ የምታደርገውን ጥረት” ኤርትራ መደገፏን እንምትቀጥል ፕሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂ ለጠቅላይ ሚኒስትር ከማል ኢድሪስ በድጋሚ አረጋገጡ። በደቡብ ምሥራቅ እስያ ሦስት ሀገራት የጣለ ከባድ ዝናብ ባስከተለው ጎርፍ እና የመሬት መንሸራተት ሕይወታቸውን ያጡ ሰዎች ቁጥር ከ600 በላይ ደረሰ። በእስራኤል ወታደራዊ ዘመቻ የተገደሉ ፍልስጤማውያን ቁጥር ከ70,000 እንደበለጠ የጋዛ የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ። የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ ለቀረበባቸው የሙስና ክስ የይቅርታ ጥያቄያቸውን ለሐገሪቱ ፕረዚደንት አቀረቡ።
    9 min
  • የሕዳር 20 ቀን 2018 ዓ/ም የዓለም ዜና
    • የአፍሪቃ ህብረት ጊኒ ቢሳዎን ከህብረቱ አባልነት አገደ።
    • የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የቬንዙዌላ አየር ክልል መዘጋቱን አስታወቁ።
    • የአሜሪካ የዜግነት እና የስደተኞች አገልግሎት ለሁሉም የተገን ጥያቄ ውሳኔ መስጠት ማቆሙን አስታወቀ።
    • የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘለንስኪ ተደራዳሪዎቻቸው ከሩስያ ጋር የሚደረገውን ጦርነት ለማብቃት ዛሬ ወደ ዋሽንግተን መጓዛቸውን አስታወቁ።
    • ሩሲያ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቱን ሂውማን ራይትስ ዎችን አገደች
    • ተመራማሪዎች ኢትዮጵያ አፋር ክልል ውስጥ የተገኘው «የቡርተሌ እግር » ለተባለው የቅድመ የሰው ልጅ ቅሪተ አካል እንቆቅልሽ መልስ አገኙ ።
    10 min
  • የህዳር 19 ቀን 2018 ዓም የዓለም ዜና
    የህዳር 19 ቀን 2018 ዓ.ም. አርዕስተ ዜና
    ትናንት በመቀሌ ከተማ በአዲ ሃቂ ክፍለ ከተማ የቦምብ ጥቃቱ መፈጸሙን ነዋሪዎች እና የጸጥታ ባለስልጣናት አስታወቁ። ጥቃቱ ስማቸው ያልተጠቀሰ የሰላም እና የፀጥታ ኃላፊ መኖሪያ ቤት ላይ ያነጣጠረ ሳይሆን አይቀርም ሲሉ አንድ የከተማዋ ነዋሪ ለዶቼቬለ ተናግረዋል።
    የምዕራብ አፍሪቃ አገራት የኤኮኖሚ ማኅበረሰብ ኤኮዋስ መፈንቅለ መንግሥት የተካሄደባትን ጊኒ ቢሳውን ከውሳኔ ሰጭ አካልነት እንደሚያግድ አስጠነቀቀ።
    የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከሦስተኛው ዓለም ሀገራት ወደ አሜሪካን የሚሰደዱ ሰዎች በሙሉ ወደ አሜሪካን መግባታቸውን እንደሚያስቆሙ አስታወቁ።
    10 min

About የዓለም ዜና

From the publisher's feed

ዶይቼ ቬለ የዕለቱን ዋና ዋና ዜናዎች ከኢትዮጵያ እና ከመላው ዓለም በየቀኑ ያቀርባል። የኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ፖለቲካዊ እና ኤኮኖሚያዊ ጉዳዮችን ጨምሮ የመላው ዓለምን ውሎ የተመለከቱ ጠቃሚ መረጃዎች በሰባቱም የሣምንቱ ቀናት ከምሽቱ አንድ ሰዓት ከዶይቼ ቬለ ያድምጡ። የዶይቼ ቬለን ዜናዎች በአፕል ፖድካስት…