የዓለም ዜና

የዓለም ዜና

Download on the App Store

የዓለም ዜና episodes

  • የኅዳር 18 ቀን 2018 ዓ.ም. የዓለም ዜና
    የኦሮሚያ ክልል ዐቃቤ ሕግ ቢሮ አራት ዐቃቢያነ ሕግ ምሥራቅ ወለጋ ውስጥ በታጣቂዎች ታግተው አንዱ መገደላቸውን የክልሉ ዐቃቢያነ ሕግ ማኅበር አስታወቀ።
    ሕዝባዊ ወያነ ሃርነት ትግራይ /ህወሃት/ በምርጫ ቦርድ የተሰረዘበት ሕጋዊ ሰውነቱ እንዲመለስለት ጠየቀ። የፕሪቶሪያው ስምምነት አደራዳሪ አካላት ስምምነቱን ከዳር እንዲያደርሱም ጥሪ አቀረበ።
    የአፍሪቃ ሕብረት በዛሬው ዕለት የጊኒ ቢሳው ፕሬዝደንት ባስቸኳይና ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲለቀቁ ጠየቀ።
    ሆንግ ኮንግ ውስጥ በደረሰው የእሳት አደጋ የሞቱት ቁጥር 65 ደረሰ። በአደጋው የተጎዱት 71 ደርሰዋል። ከ200 በላይ ደግሞ እስካሁን የገቡበት አልታወቀም።
    12 min
  • የኅዳር 17 ቀን፣ 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና
    ቤርሊን፥ ኢትዮጵያ ውስጥ በሲቪሎች ላይ የሚፈጸም « ግድያና በደል» የተቃወመ ሰልፍ ቤርሊን ከተማ ተደረገ፤ በማርበርግ ተሐዋሲ የ6 ሰዎች ሕይወት ማለፉን የጤና ሚኒስቴር ዐሳወቀ፤ አ.አ፥ አፍሪኮም «ኢትዮጵያ በሠላማዊ መንገድ የባሕር በር ለማግኘት የምታደርገውን» ጥረት እንደሚደግፍ ገለጠ፤ ሞቃዲሹ፥ አፍሪኮም ሶማሊያ ውስጥ አይኤስ ላይ ልዩ ዘመቻ ከፈተ፤ ሞቃዲሹ፥ አፍሪኮም ሶማሊያ ውስጥ አይኤስ ላይ ልዩ ዘመቻ ከፈተ፤ ዋሽንግተን፥ ፕሬዚደንት ትራምፕ የዩክሬን የሰላም ዕቅድ ቀነ ገደብን ለማራዘም ፍንጭ ሰጡ፤ ብራዚሊያ፥ ቀኝ አክራሪው የብራዚል የቀድሞ ፕሬዚደንት የ27 ዓመት እስራቸውን ጀመሩ፤
    12 min
  • የዓለም ዜና፤ ኅዳር 16 ቀን፣ 2018 ዓ.ም ማክሰኞ
    -የሩስያ እና የዩክሬን ባለስልጣናት ከፍተኛ የሆነ ሰው አልባ አውሮፕላኖች ጥቃት መፈጸማቸውን በየበኩላቸዉ ገለፁ። ሩስያ መዲና ኪይቭ ላይ የድሮን ጥቃት አድርሳለች።
    -የቦሮ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ከገዢው የብልጽግና ፓርቲ ጋር ለመዋሃድ የሚያስችለውን ውሳኔ አሳለፈ።
    -አፋር ክልል የፈነዳዉ እሳተ ገሞራ የሚተፋዉ አመድ በሕንድ የሚደረግን የአዉሮፕላን በረራን አቋረጠ።
    -የትራምፕ አስተዳደር ዩናይትድ ስቴትስ ወደ 235,000 የሚሆኑ ስደተኞችን የመኖርያ ፈቃድና ሁኔታቸዉን ሊፈትሽ መሆኑ ተሰማ።
    12 min
  • የኅዳር 15 ቀን፣ 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና
    የዛሬው የዓለም ዜና በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከሰላሳ በላይ ንጹሃን በታጣቂዎች መገደላቸውን፤ የሱዳን ጦር ኃይሎች አዛዥ የአሜሪካንን የእርቅ ሃሳብ ውድቅ አድርገዋል በሚል የተባበሩት አረብ ኢምሬቶች መውቀሷን፤የቀድሞ የደቡብ አፍሪቃ ፕሬዚዳንት ጃኮብ ዙማ ሴት ልጅ ያለፍላጎታቸው በዶንባስ እንዲዋጉ ሰዎችን ቀጥራለች በሚል መከሰሷን፤በጋዛ ሰርጥ አራት ፍልስጤማውያን መገደላቸውን የህክምና ባለሙያዎች መግለፃቸውን፤እስራኤል በጥቅምት 7ቱ የሀማስ ጥቃት ሀላፊነታቸውን አልተወጡም ያለቻቸውን ከፍተኛ የጦር አዛዦቿን ማባረሯን እንዲሁም ዝነኛው የሬጌ ሙዚቃ አቀንቃኝ ጂሚ ክሊፍ ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱን የሚያስቃኙ ዘገባዎችን አካቷል።
    13 min
  • የኅዳር 14 ቀን 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና
    ከናይጄሪያ የካቶሊክ ትምህርት ቤት ታግተው የተወሰዱ 50 ተማሪዎች ከአጋቾቻቸው ማምለጥ ቻሉ፤ የጀርመን መራሔ መንግሥት ሜርስ በቡድን 20 ጉባኤ ላይ ዩናይትድ ስቴትስ አለመሳተፏን ተቹ፤ ህንድ እና አጋሮቿ የኮፕ 30ን ውጤት አወደሱ፤የዩክሬን ጦርነት ለማቆም በቀረበው ምክረ ሐሳብ አሜሪካ እና የአውሮፓ መንግሥታት እየተወያዩ ነው
    10 min
  • የኅዳር 13 ቀን 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና
    የዛሬው የዓለም ዜና ትግራይ ተጨማሪ ጥቃቶችን ለመከላከል መንግስታት እርምጃ መውሰድ አለባቸው ሲል ሂውማን ራይትስ ዎች ማሳሳቡን፤የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ ዓለም አቀፍ ችግሮችን ለመፍታት በጋራ መተባበር እንደሚያስፈልግ ማሳሰባቸው፤ናይጄሪያ ውስጥ ከአንድ የካቶሊክ ትምህርት ቤት ከ300 በላይ ተማሪዎች በታጣቂዎች ታፍነው መወሰዳቸውን፤ዩክሬን ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘለንስኪ በአሜሪካ የቀረበውን የሰላም እቅድ ላይ ከአውሮፓ አጋሮቻቸው ጋር መወያየታቸውን እንዲሁም አሜሪካ በኩባ ላይ የጣለችው ለአስርት አመታት የዘለቀ ማዕቀብ እንዲነሳ መጠየቁን ያስቃኛል።
    10 min
  • የኅዳር 12 ቀን፣ 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና
    በአማራ ክልል የባሕር ዳርና አካባቢው ከፍተኛ ፍ/ቤት፤ የጥበበ ጊዮን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ሐኪም በነበሩት ዶ/ር አንዷለም ዳኘ ገዳይ ላይ የ25 ዓመት ጽኑ እስራት መወሰኑ፤ዩናይትድ ስቴትስ በG20 ስብሰባ ላይ እንደምትገኝ ደቡብ አፍሪቃ ማሳወቋ፤በናይጄሪያ ታጣቂዎች ከአንድ የከካቶሊክ ትምህርት ቤት ተማሪዎችን አፍነው መውሰዳቸውን፤ የአውሮፓ ህብረት መሪዎች ዶናልድ ትራምፕ የሩሲያ ዩክሬን ጦርነትን ለማስቆም ያቀዱትን የሰላም ሀሳብ እስካሁን በይፋ እንዳልደረሳቸው መግለፃቸው እንዲሁም ዶናልድ ትራምፕ እርሳቸውን የሚፃረር መልዕክት ባሰራጩ ዲሞክራቶች ላይ ሞት ቅጣት ለመቅጣት መዛታቸውን የሚያስቃኙ ዘገባዎችን አካቷል።
    12 min
  • የሕዳር 11 ቀን 2018 የዓለም ዜና
    -የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ)ና የኦሮሞ ፌደራሊስ ኮንግረሰ (ኦፌኮ) በኦሮሚያ ክልል ያለዉን የፀጥታ፣ የሕግና ሥርዓት መደፍረስና መፋለሥ ለማቃለል ከክልሉ መሪዎች ጋር መነጋገር እንደሚሹ አስታወቁ።---የጀርመን መንግሥት ለአፍሪቃ ሕብረት አጀንዳ 2063 መርሐ-ግብር ማስፈፀሚያ ተጨማሪ 88 ሚሊዮን ዩሮ ለመርዳት ቃል ገባ።ተጨማሪዉ ገንዘብ አፍሪቃ ዉስጥ ዘላቂ ልማትን፣የአ,ረንጓዴ ኃይልን፣ሠላምና ፀጥታ ለማጠናከርና ለ,ጤና አገልግሎት እንደሚዉል በአዲስ አበባ የጀርመን ኤምባሲ አስታዉቋል።---ሕንድና ፓኪስታን ባለፈዉ ግንቦት የገጠሙት ዉጊያ የፈረንሳይና የቻይናን የጦር መሳሪያ ጥራትና አቅም ለመፈተሽ የዋለ እንደነበር ተነገረ
    12 min
  • የህዳር10 ቀን 2018 ዓ.ም. የዓለም ዜና
    የህዳር 10 ቀን 2018 ዓ.ም. አርዕስተ ዜና
    «ትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት» በሚል መጠሪያ የተቀናጁት 5 ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች የኢትዮጵያ መንግስት ከምርጫው በፊት በሀገሪቱ ሰላም እና መረጋጋት እንዲያሰፍን ጠየቁ።
    ከኤርትራ መሆንዋ ተነገረ የአንዲት እናት የተቆረጡ እጆችን አውራ ጎዳና ላይ ማግኘቱን የጀርመን ፖሊስ ዐሳወቀ። በቦንየተገን ጠያቂዎች ማቆያ የትኖር የነበረው ይህች እናት፣ የት እንዳለች እስከ ትናንት ድረስ እንደማያውቅ ፖሊስ ገልጿል።
    በሱዳን ጦርነት ጣልቃ በመግባት የምትጠረጠረው የተባበሩት አረብ ኤሜሬቶች በማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች የሚደርስባት ወርጂብኝ ተጠናክሮ ቀጥሏል። ሰ
    12 min
  • የዓለም ዜና፤ ኅዳር 9 ቀን 2018 ማክሰኞ
    አርስተ ዜናዎች፤
    -ኢሕአፓ ባለፉት 7 ዓመታት በትግራይ ክልል ፣ በአፋር ክልልና በአማራ ክልል፣ አሁን ደግሞ በመላው የአማራ ክልልና በበርካታ የኦሮሚያ ክልል ቀጠናዎች ውስጥ፣ እየደረሱ ያሉ ያላቸውን የወገን ዕልቂትና የመሠረተ ልማት አውታሮች ብሎም የሌሎች ቋሚና ተንቀሳቃሽ ንብረት ውድመት እንዲቆም ዛሬ ባወጣዉ መግለጫ ጠየቀ።-የሩሲያ ጦር በስድስት የአፍሪቃ ሀገራት እየተንቀሳቀሰ መሆኑን የሩሲያ ቴሌቪዥን ዘገበ።-የጀርመን መንግስት የእስራኤል በከፊል አቋርጦት የነበረዉን የጦር መሳርያ አቅርቦት ዉሳኔ እንደሚያነሳ አሳወቀ። በሌላ በኩል የጀርመን ለዓለም አቀፍ የአየር ንብረት ጥበቃ ተጨማሪ 60 ሚሊዮን ዩሮ ሰጠች።
    11 min

About የዓለም ዜና

From the publisher's feed

ዶይቼ ቬለ የዕለቱን ዋና ዋና ዜናዎች ከኢትዮጵያ እና ከመላው ዓለም በየቀኑ ያቀርባል። የኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ፖለቲካዊ እና ኤኮኖሚያዊ ጉዳዮችን ጨምሮ የመላው ዓለምን ውሎ የተመለከቱ ጠቃሚ መረጃዎች በሰባቱም የሣምንቱ ቀናት ከምሽቱ አንድ ሰዓት ከዶይቼ ቬለ ያድምጡ። የዶይቼ ቬለን ዜናዎች በአፕል ፖድካስት…