Sign up to save your podcastsEmail addressPasswordRegisterOrContinue with GoogleAlready have an account? Log in here.
ዶይቼ ቬለ የዕለቱን ዋና ዋና ዜናዎች ከኢትዮጵያ እና ከመላው ዓለም በየቀኑ ያቀርባል። የኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ፖለቲካዊ እና ኤኮኖሚያዊ ጉዳዮችን ጨምሮ የመላው ዓለምን ውሎ የተመለከቱ ጠቃሚ መረጃዎች በሰባቱም የሣምንቱ ቀናት ከምሽቱ አንድ ሰዓት ከዶይቼ ቬለ ያድምጡ። የዶይቼ ቬለን ዜናዎች በአፕል ፖድካስት... more
FAQs about የዓለም ዜና:How many episodes does የዓለም ዜና have?The podcast currently has 2,937 episodes available.
November 08, 2024የጥቅምት 29 ቀን 2017 ዓ/ም የዓለም ዜናአርስተ ዜና፤ --በአማራ ክልል ሰሜን ጎጃም ዞን አቸፈር ወረዳ ባለፈው ማክሰኞ ጥቅምት 26/2017 በድሮን በተፈፀመ ጥቃት ከ40 በላይ ሰዎች መገደላቸውንና 9 መቁሰላቸውን ነዋሪዎች ተናገሩ። --የኢትዮጵያ የገንዘብ ሚኒስቴር በፍራንኮ ቫሉታ ሸቀጦችን ወደ ሃገር ውስጥ ማስገባት ከዛሬ ጀምሮ አገደ። --አቶ ዮሃንስ ቧያሌው 1ኛ ተከሳሽ በሆኑበት መዝገብ የተከሰሱና ጉዳያቸው በፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት እየታየ ያለው ግለሰቦች ለሕዳር 20 ቀን 2017 ዓ.ም ተቀጠሩ።--በጋዛ ጦርነት ከተገደሉት ውስጥ 70 በመቶ ያህሉ ሴቶች እና ህጻናት መሆናቸው መለየቱን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስታወቀ።ሙሉዉን ዜና ያድምጡ!...more12minPlay
November 07, 2024የጥቅምት 28 ቀን፣ 2017 ዓ.ም የዓለም ዜናኦሮሚያ ክልል ውስጥ የወረዳ ባለሥልጣናትን ጨምሮ 48 ሰዎች የተገደሉበትን ጥቃት እየመረመረ መሆኑን የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ዛሬ አስታወቀ። የባሕርዳር ከተማ አስተዳደር በእገታና በዘረፋ ተሰማርተው ነበር ያላቸውን ክ129 በላይ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ማዋሉን ገለጠ። የጀርመን የፋይናንስ ሚኒስትር ከሥልጣናቸው መነሳታቸውን ተከትሎ የሀገሪቱ ጥምር መንግሥት ቀውስ ውስጥ ገብቷል። ተቃዋሚዎች አስቸኳይ ምርጫ እንዲካሄድ ግፊት እያደረጉ ነው። ፕሬዝደንት ፍራንክ ቫልተር ሽታይን ማየር የጥምር መንግሥቱ ለገባበት ቀውስ መፍትሄ ለማምጣት ኃላፊነት የተሞላበት አካሄድ እንዲኖር ፖለቲከኞቹን አሳስበዋል።...more10minPlay
November 05, 2024የዓለም ዜና፤ ጥቅምት 26 ቀን 2017 ዓ.ም ማክሰኞDW Amharic አርስተ ዜናበአማራ ክልል እየተባባሰ የሄደው ግጭት እንዳሳሰባት አሜሪካ አስታወቀች። በኢትዮጵያ ግጭቶች እልባት ያገኙ ዘንድ የፖለቲካ ውይይቶች መደረግ አለባቸው፤ የሚል አቋም እንዳላትም ገልፃለች።--አሜሪካ 47 ኛዉን ፕሬዚዳንታዊ ምርጫን እያካሄደች ነዉ። ሁለቱ ፕሬዚዳንታዊ እጩዎች በየፊናቸዉ እንደሚያሸንፉ ተናግረዋል። በሌላ በኩል የአሜሪካ የደኅንነት ባለስልጣናት «የውጭ ኃይሎች» ያሏቸዉ የአሜሪካ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ እምነት እንዲያጣ ሙከራ እያደረጉ ነው ሲሉ እየከሰሱ ነዉ።--የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎዲሜር ዜሌንስኪ 11,000 የሰሜን ኮሪያ ወታደሮች ሩስያ ድንበር ኩርስክ ግዛት መግባታቸዉን በስጋት ገለፁ።...more12minPlay
November 04, 2024የጥቅምት 25 ቀን 2017 ዓ.ም የዓለም ዜናበሶማሊያ ዋና ከተማ መቅዲሹ ላይ አሸባብ ባደረሰው ጥቃት የተመድ ሠራተኞችን ጨምሮ በርካቶች መገደላቸው ተነገረ። ጥቃቱ የደረሰው ከመቃዲሹ አውሮፕላን ማረፊያ አቅራቢያ የሚገኝ ከፍተኛ ጥበቃ በሚደረግለት ስፍራ ነው።ስፔን ውስጥ የአደጋ ጊዜ ሠራተኞች ዛሬም የጎርፍ ሰለባዎችን መፈለግ ቀጥለዋል። ቫለንሲያ ግዛት በጎርፍ ከደረሰባት አደጋ ጋር እየታገለች ዛሬ ኃይለኛ ዝናብ የወረደባት ባርሴሎና ከተማ በተጠንቀቅ ላይ ትገኛለች። የሱዳን ጦር አዛዥ አብደልፈታህ አል ቡርሀን የባለሥልጣናት ሹም ሽር አደረጉ። አራት አዳዲስ ሚኒስትሮችንም ሰየሙ። የእስራኤል ጦር ሰሜን ጋዛ ውስጥ የሚገኘው የክትባት ማዕከል ላይ ጥቃት አላዳረስኩም አለ።...more10minPlay
November 02, 2024የጥቅምት 23 ቀን 2017 የዓለም ዜናየኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት በኦሮሚያ ክልል በተፈጸሙ ጥቃቶች 120 የመንግሥት ወታደሮች ገድያለሁ አለ። ህወሓት በፕሪቶሪያ ግጭት የማቆም ሥምምነት የገባቸውን ግዴታዎች እየፈጸመ አይደለም ሲል የኢትዮጵያ መንግሥትን ከሰሰ። አሜሪካ “ታሪካዊ“ ያለችው “የርስ በርስ ጦርነት ያቆመ ሥምምነት“ የተፈረመበትን ሁለተኛ ዓመት በማስመልከት በኢትዮጵያ ግጭት እንዲቆም ጥሪ አቅርባለች። የወባ ወረርሽኝ በኢትዮጵያ ዋንኛ የሕብረተሰብ ጤና ተግዳሮት እንደሆነ የዓለም ጤና ድርጅት አስጠነቀቀ። ከታኅሳስ 22 ቀን 2016 እስከ ጥቅምት 10 ቀን 2017 ብቻ 7.3 ሚሊዮን የወባ ሕሙማን መመዝገባቸውን፤ 1157 ሰዎች መሞታቸውን አስታውቋል።...more12minPlay
November 01, 2024የጥቅምት 22 ቀን 2017 ዓ.ም. የዓለም ዜና*በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሸዋ ዞን ዱግዳ ወረዳ በታጠቁ ኃይሎች በደረሰ ጥቃት ቢያንስ የ40 ንጹሃን ሰዎች ህይወት አለፈ።*በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ዛሬ ጠዋት በደረሰ የመሬት መንሸራተት አደጋ የ10 ሰዎች ሕይወት አለፈ ፡፡ *ሁለቱ የህወሓት ቡድኖች በልዩነታቸው ላይ ለመነጋገር እንደተስማሙ ተነገረ።*የጀርመን ፌደራል መንግስት በሀገሩ የሚገኙ የኢራን ቆንስላዎች በሙሉ እንዲዘጉ ወሰነ። * እስራኤል ሊባቦስ እና ጋዛ ውስጥ ጥቃት ሰነዘረች...more10minPlay
October 31, 2024የሐሙስ ጥቅምት 21 ቀን 2017 ዓ/ም የዓለም ዜናDW Amharic -በአማራ ክልል ያለውን ቀውስ ለመፍታት የሰላም ጥረት አለመሳካቱን ጠቅላይ ሚንስትሩ መግለፃቸው-ከአየር ንብረት እና ኢኮኖሚያዊ ችግር ጋር ተዳምሮ የግጭት መስፋፋት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን ለከፋ ችግር ዳርጓል መባሉ-ሶማሊያ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አዲስ የሽግግር ተልዕኮ ለማቋቋም መወሰኑን ማወደሷ-እስራኤል ሊባኖስ ውስጥ በፈፀመችው የአየር ጥቃት ሰላማዊ ሰዎች ተገደሉ መባሉ-ሰሜን ኮሪያ አህጉር አቋራጭ የባሊስቲክ ሚሳኤል መተኮሷን መግለጿ በዛሬው የዓለም ዜና የተካተቱ ርዕሶች ናቸው።...more12minPlay
October 30, 2024የጥቅምት 20 ቀን 2017 ዓ.ም የዓለም ዜናበዎላይታ ዞን እና በሲዳማ ክልል ውስጥ ትናንት በደረሰ መሬት መንሸራተት የዘጠኝ ሰዎች ሕይወት አለፈ። የአደጋው መንስኤ በሌሊት የጣለው ከባድ ዝናብ እንደሆነ ተገልጿል። በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጉራጌ ዞን በፀጥታ አባላት የጅምላ እሥር እየተፈጸመ መሆኑን የአካባቢው ነዋሪዎች አመለከቱ። መንስኤው ከሸኔ አለያም ከፋኖ ጋር ግንኙነት አላችሁ የሚል ነው ተብሏል። የሴኔጋል ባሕር ኃይል ባለፉት 10 ቀናት 600 የሚሆኑ ሕገወጥ ስደተኞችን ከባሕር ላይ መያዙን አስታወቀ። ኢራን በእስራኤል ጥቃት የሚሳኤል ማምረቻዎቼ አልተጎዱም አለች።...more9minPlay
FAQs about የዓለም ዜና:How many episodes does የዓለም ዜና have?The podcast currently has 2,937 episodes available.