የዓለም ዜና

የዓለም ዜና

Download on the App Store

የዓለም ዜና episodes

  • DW Amharic የሕዳር 6 ቀን 2018 የዓለም ዜና
    በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የተከሰተው የሔሞራጅ ትኩሳት በሽታ መንስዔ የማርበርግ ቫይረስ መሆኑን የጤና ሚኒስቴር አረጋገጠ። በኢትዮጵያ የሚካሔደው ሀገራዊ ምክክር ያጋጠሙት “አብዛኞቹ ተግዳሮቶች ፖለቲካዊ በመሆናቸው ፖለቲካዊ መፍትሔ” እንደሚያስፈልጋቸው ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ አሳሰቡ። ከሱዳን ሕዝብ ከግማሽ በላይ የሚሆነው ሰብአዊ ርዳታ ያስፈልገዋል ተባለ። ሱዳን እና ደቡብ ሱዳን በይገባኛል በሚወዛገቡባት አቢዬ ግዛት የሰፈረውን ሰላም አስከባሪ የሥራ ዘመን የተባበሩት መንግሥታት የጸጥታ ጥበቃ ምክር ቤት አራዘመ። ደቡብ አፍሪካ በኬንያ በኩል ወደ ጁሐንስበርግ የተጓዙ ፍልስጤማውያንን ጉዳይ እንደምትመረምር አስታወቀች።
    16 min
  • የሕዳር 5 ቀን 2018 የዓለም ዜና
    -ታንዛኒያ ዉስጥ ባለፈዉ መስከረም የተደረገዉን አወዛጋቢ ምርጫ በሚቃወሙ የሐገሪቱ ዜጎች ላይ የተፈፀመዉ ግድያ እንደሚጣራ የሐገሪቱ ፕሬዝደንት አስታወቁ።ፕሬዝደንት ሳሚያ ሱሉሑ ሐሰን ዛሬ እንዳሉት የምርጫዉን ሒደት በመቃወማቸዉ ለታሰሩ ሰዎችም መንግሥታቸዉ ምሕርት ያደርጋል።-አፍሪቃ ዉስጥ በተገባደደዉ የግሪጎሪያኑ 2025 ዓመት የተሰራጨዉ የኮሌራ በሽታ 7ሺሕ ሰዎች ገደለ፤ ከ300 ሺሕ በላይ ለከፈ።-የሩሲያና የዩክሬን ጦር ኃይላት ዛሬ አንዱ የሌላዉን ግዛት በሰዉ አልባ አዉሮፕላንና በሚሳዬል ሲደበድቡ አነጉ።
    13 min
  • የሕዳር 4 ቀን 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና
    በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጅንካ ከተማ የሄሞራጂክ ፊቨር በተባለ በሽታ 6 ሰዎች መሞታቸውን ተሰማ። የአፍሪካ ህብረት «በሰሜን ናይጄሪያ የተፈጸመ የዘር ማጥፋት ወንጀል የለም» ሲል አስተባበለ። እስራኤል በሐይል በያዘችው ምዕራባዊ የዮርዳኖስ ወንዝ ዳርቻ የሰፈሩና «ፅንፈኛ» የተባሉ እስራኤላዉያን አንድ መስጊድን በእሳት ማቃጠላቸዉንና በመስጊዱ ግድግዳዎች ላይም «አጸያፊ» የተባሉ ፅሑፎች መጻፋቸው የፍልስጤማ ዜና አገልግሎት ዘገበ። ፈረንሳይ ከ10 ዓመታት በፊት በሽብር ጥቃት የተገደሉ 130 ዜጎችዋን ዛሬ ስትዘክር ዋለች።
    12 min
  • የህዳር 3 ቀን 2018 ዓ.ም. የዓለም ዜና
    ዛሬ ያስቻለዉ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የልደታ ምድብ ችሎት የቀድሞው የኢትዮጵያ የሰላም ሚንስትር ዴታ አቶ ታዬ ደንደአን ከ2 የክስ ጭብጦች ነጻ ሲያደርጋቸው በአንዱ ደግሞ ጥፋተኛ ብሏቸዋል።
    ኢትዮጵያ ኮፕ 32ን ለማስተናገድ በዝግጅት ላይ መሆንዋን አስታወቀች። ጉባኤውን እንድታስተናግድ ያጸደቀውን የአፍሪቃ ተደራዳሪዎች ቡድንም አመሰገነች ።
    ስደተኞችን የጫነች አንዲት የፕላስቲክ ጀልባ በሊቢያ የባህር ዳርቻ ሰጥማ ቢያንስ 42 ስደተኞች ሳይሞቱ እንዳልቀረ ዓለም አቀፉ የፍልሰተኞች ጉዳይ ድርጅት በምህፃሩ IOM ዛሬ አስታወቀ። በግሪኳ ደሴት በጋቭዶስ አንዲት ስደተኞችን ያሳፈረች ጀልባ ሰጥማ ሦስት ሰዎች ሞቱ።
    12 min
  • የኅዳር 2 ቀን 2018 ዓ.ም. የዓለም ዜና
    ኢትዮጵያ በጎርጎሪዮሳዊ 2027 ዓ.ም. ዓለም አቀፍ የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤን ለማስተናገድ ያቀረበችው ጥያቄ የበርካታ ሃገራትን ድጋፍ ማግኘቱ ተገለጸ። ይፋዊ ውሳኔው ዛሬ ብራዚል ላይ ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል።
    የተርክዬ አቃብያነ ሕግ የኢስታንቡል ከተማ ከንቲባ ከሁለት ሺህ ዓመት በላይ እንዲታሠሩ ጠየቁ።
    በፓኪስታን ዋና ከተማ ኢዝላማባድ ላይ በደረሰ የአጥፍቶ ጠፊ ጥቃት 12 ሰዎች ተገደሉ። ሌሎች 27 ሰዎች ደግሞ ተጎዱ። ለድርጊቱ ኃላፊነት የወሰደ አካል የለም።
    ሩሲያ ሌሎች የኒኩሊየር ኃይል ባለቤት ሃገራት የሚያደርጉ ከሆነ የኒኩሊየር ሙከራ እንደምታደርግ አስታወቀች።
    10 min
  • የሕዳር 1 ቀን 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና
    ሕገወጥ የውጭ ምንዛሪ አሻጥሮችን ሲፈጽሙ ነበር ተብለው የተጠረጠሩ ከ100 በላይ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር ዋሉ።
    በበርካታ የታሪክ መፃህፍቶቻቸው የሚታወቁት አንጋፋው የታሪክ ምሁር ፕሮፌሰር ላጲሶ ጌታሁን ዴሌቦ በ87 አመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ።
    ኢራን ሜክሲኮ ውስጥ የሚገኙትን የእስራኤል አምባሳደርን ለመግደል አሲራለች በማለት ዩናይትድ ስቴትስ ያወጣችውን ውንጀላ «እርባና ቢስ» ስትል አጣጣለችው።
    የቢቢሲ ዋና ዳይሬክተርና የዜና ክፍል ሐላፊ በገዛ ፈቃዳቸው ስልጣናቸውን ለቀቁ። ሐላፊዎቹ ከሥልጣን የወረዱት የአሜሪካው ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕን በተመለከተ በጣቢያው በተሰራ ዘጋቢ ፊልም ምክንያት ነው ተብሏዋል።
    12 min
  • የጥቅምት 30 ቀን 2018 ዓ/ም የዓለም ዜና
    • ዩጋንዳ በቀጣዩ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ላይ አሲረዋል ብላ ከአንድ ወር በፊት ያሰረቻቸውን ሁለት ኬንያዉያን አክቲቪስቶች ከእስር ለቀቀች።
    • በስፔይኗ የቴኔሪፌ ደሴት የባህር ዳርቻ ትናንት ቅዳሜ በተነሳ ወጀብ የሶስት ሰዎች ህይወት አልፎ ሌሎች 15 ሰዎች መጎዳታቸውን የአስቸኳይ ጊዜ አገልግሎት አስታወቀ።
    • የአሜሪካ የሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን ለ14 ሰዎች ህልፈት ምክንያት ከሆነው የጭነት አውሮፕላን አደጋ በኋላ ተመሳሳይ ስሪት የሆኑ አውሮፕላኖች እንዳይበሩ አገደ።
    • ዩክሬን በሩስያ የኃይል መሰረተ ልማት ላይ ባደረሰችው የአየር ጥቃት በበርካታ የአዋሳኝ አካባቢ ክልሎች ኃይል መቋረጡን ባለስልጣናት አስታወቁ።
    9 min
  • የቅዳሜ ጥቅምት 29 ቀን 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና
    DW Amharic -የዛሬው የዓለም ዜና ህወሓት በትግራይ ኃይል አባላት ላይ የድሮን ጥቃት መፈጸሙን መግለፁ።ህወሓት በገለፀው ትራምፕ በደቡብ አፍሪካ በሚካሄደው በG20 ጉባኤ ላይ የአሜሪካ ባለስልጣናት እንደማይገኙ መግለፃቸው፤የታንዛንያ ፖሊስ በሐገሪቱ ከተከሰተው ሁከትና ብጥብጥ ጋር በተያያዘ 10 የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች ለማሰር ማቀዱን ፣ሩስያ አንድ ተጨማሪ በምስራቅ የዩክሬይ ግዛት የምትገኝ መንደር መያዟን ማስታወቋን እንዲሁም ደቡብ ብራዚልን የመታው «ቶርኒዶ» የተሰኘው አውሎ ንፋስ 5 ሰዎችን ሲገድል ከ430 በላይ መጉዳቱ ያስቃኛል።
    9 min
  • የጥቅምት 28 ቀን 2018 ዓ.ም. የዓለም ዜና
    የጥቅምት 28 ቀን 2018 ዓ.ም. አርዕስተ ዜና
    የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ዜጎች «የአካባቢያቸውን ልማት ማገዝ እንዲችሉ ሰላም ያስፈልጋል» ሲሉ ዛሬ ተናገሩ።
    የሱዳን ጦር፣የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይል ለሊቱን በሰሜን ምሥራቅ ሱዳን ሁለት ከተሞች ላይ የጣላቸውን የድሮኖች ጥቃቶች መመከቱን አስታወቀ። የጥቃት ዒላማ የአትባራ ከተማና ሪቨር ናይል ክፍለ ሀገር ናቸው።
    ከበርካታ የአፍሪቃ ሀገራት የመጡ ከ1400 በላይ አፍሪቃውያን ከሩስያ ኅይሎች ጎን ተሰልፈው ይዋጋሉ ስትል ኪቭ አስታወቀች።
    11 min
  • የጥቅምት 27 ቀን 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና
    DW Amharic -የዛሬው የዓለም ዜና፤ በአፋር ክልል በትግራይ ሀይሎች መካከል የተቀሰቀሰው ግጭት ለጥቂት ቀናት ሲካሄድ የቆየ ነው መባሉን፤የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት፣ ከ7ኛው አገር አቀፍ ምርጫ በፊት የሕገመንግሥት ማሻሻያ እንዲደረግ መጠየቃቸው፤አልፋሺር በሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ሀይል ከተያዘች ወዲህ ሰባት ጋዜጠኞች የደረሱበት አለመታወቁን፤ሱዳን፤ የፈጥኖ ደራሽ ሀይሉ በአሸባሪነት እንዲሰየም መጠየቋን፤ደቡብ አፍሪካ በሩሲያ ዩክሬን ጦርነት ውስጥ ተሳትፈው ከተያዙ ዜጎቿ የድረሱልኝ ጥሪ እንደደረሳት መግለጿን፤እስራኤል ከግብፅ ጋር በሚያዋስናት ድንበር ላይ የተዘጋ ወታደራዊ ቀጠና ማወጇን ያስቃኛል።
    11 min

About የዓለም ዜና

From the publisher's feed

ዶይቼ ቬለ የዕለቱን ዋና ዋና ዜናዎች ከኢትዮጵያ እና ከመላው ዓለም በየቀኑ ያቀርባል። የኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ፖለቲካዊ እና ኤኮኖሚያዊ ጉዳዮችን ጨምሮ የመላው ዓለምን ውሎ የተመለከቱ ጠቃሚ መረጃዎች በሰባቱም የሣምንቱ ቀናት ከምሽቱ አንድ ሰዓት ከዶይቼ ቬለ ያድምጡ። የዶይቼ ቬለን ዜናዎች በአፕል ፖድካስት…