የዓለም ዜና

የዓለም ዜና

Download on the App Store

የዓለም ዜና episodes

  • የጥቅምት 26 ቀን 2018 ዓ.ም. የዓለም ዜና
    የጀርመን ፍርድ ቤት በዛሬው ዕለት 10 ታማሚዎችን በመግደል ጥፋተኛ በተባለች ነርስ ላይ የእድሜ ልክ እስራት ፈረደ። ግለሰቧ 27 ሰዎች ላይም የመግደል ሙከራ በማድረግ ጥፋተኛ ተብላለች።
    ፈረንሳይ ውስጥ በዛሬው ዕለት አንድ ግለሰብ በመኪና ሆን ብሎ በሰዎች ላይ ባደረሰው ጥቃት ዘጠኝ ሰዎች ተጎዱ። ግለሰቡ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውሏል።
    የጋዛ ባለሥልጣናት እስራኤል በዛሬው ዕለት የ15 ፍልስጤማውያንን አስከሬን መመለሷን አስታወቁ። ሀማስም ከሁለት ሳምንት በፊት 20 ታጋቾችን እና 21 አስከሬኖችን ለእስራኤል አስረክቧል።
    የሩሲያ ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን ሀገራቸው የኒኩሊየር የጦር መሣሪያ ሙከራ እንደምትጀምር ዛሬ አስታወቁ።
    10 min
  • የጥቅምት 24 ቀን 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና
    በውዝግብ እና ዓመፅ ያታጀበው የታንዛንያ ምርጫ ማሸነፋቸውን ያወጁት ሳምያ ሱሉሑ ሐሰን በዛሬው ዕለት የፕረዚደንትነት ቃለ መሐላ ፈጸሙ። የጀርመን ፕረዚደንት ፍራንክ ቫልተር ሽታይን ማየር በጋና የ3 ቀናት ጉብኝት ለማድረግ አክራ ገብተዋል። እስራኤል በሊባኖስ በሁለት ቦታዎች በፈጸመችው የአየር ጥቃት 2 ሰዎች መገደላቸውንና 7 መቁሰላቸውን የሀገሪቱ የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።
    12 min
  • የእሁድ ጥቅምት 23 ቀን 2018 ዓ. ም የዓለም ዜና
    የዛሬው የዓለም ዜና የጂቡቲ ፓርላማ ለፕሬዚዳንቶች ያስቀመጠውን የዕድሜ ገደብ ማንሳቱን፤ናይጄሪያ፤ አሜሪካ እስላማዊ አማፅያንን ለመዋጋት የምታደርገው ድጋፍ ሉዓላዊነትን ያከበረ መሆን እንዳለበት መግለጿን፤የጀርመኑ ፕሬዚዳንት ጋዛን መልሶ በመገንባት ረገድ ሁሉም ሊተባበር እንደሚገባ መግለፃቸውን፤የብሪታኒያ ፖሊስ በባቡር ውስጥ ከደረሰው የስለት ጥቃት ጋር ተያይዞ 2 ሰዎችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን የሚያስቃኙ ዘገባዎችን አካቷል።
    7 min
  • የጥቅምት 22 ቀን 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና
    በኬንያ ምስራቃዊ የስምጥ ሸለቆ ዛሬ ባጋጠመ የመሬት መንሸራተት ቢያንስ 13 ሰዎች መሞታቸውን ተሰማ። ግብጽ በአይነቱ ግዙፍ የተባለለትን ብሔራዊ ሙዝየም ዛሬ አስመረቀች። የዩክሬይን ድሮኖች ወደ ሩስያ ግዛት ሰርገው በመግባት ከዋና ከተማዋ በስተ ደቡብ ምስራቅ በሚገኙ ወታደራዊ ይዞታዎች ላይ ጥቃት መፈጸማቸውን ተሰማ። በኤርላንድ ፅንፈኛ መጤ ጠል የተባሉ ወጣቶች በአካባቢው በሚገኝ የተገን ጠያቂዎች ላይ ጥቃት መሰንዘራቸውን የሐገሪቱ የመንግስት ባለስልጣናት አስታወቁ።
    13 min
  • የጥቅምት 21 ቀን 2018 ዓ.ም. የዓለም ዜና
    የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ በኦሮምያ ክልል በምሥራቅ አርሲ ዞን አስተዳደር በሚገኙ አራት ወረዳዎች በኡትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋኅዶ ቤተ ክርስቲያን እምነት ተከታዮች ላይ ማንነታቸው ባልታወቀ ታጣቂዎች ተፈጸሙ ያላቸውን ግድያዎች አወገዘ
    በታንዛንያ የተካሄደውን ምርጫ ተቃውመው ሰልፍ ከወጡት ውስጥ ፣ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ተገድለዋል ሲል፣ የታንዛኒያ ዋነኛ ተቃዋሚ ፓርቲ አስታወቀ። የተመድ ቢያንስ 10 ሰዎች መገደላቸውን ማወቁን ተናግሯል።
    የትራምፕ አስተዳደር ዩናይትድ ስቴትስ በየዓመቱ የምትቀበላቸውን ስደተኞች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ እንደምትቀንስ አስታወቀ
    11 min
  • የዓለም ዜና፤ ጥቅምት 20 ቀን 2018 ሐሙስ
    አርስተ ዜና፤ -የኤርትራ ፕሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂ ግብፅን ለ5 ቀናት ለመጎብኘት ዛሬ ከአስመራ ወደ ካይሮ ተጓዙ። ኢሳያስ ግብፅን የሚጎበኙት የግብጹ ፕሬዝደንት አብዱልፈታሕ አል ሲሲ ባደረጉላቸዉ ግብዣ ነዉ።-በኢትዮጵያ ከመንግሥት ጋር ይሰራል የሚል ትችት የሚቀርብበት የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ ፤ ኢዜማ ፓርቲ፤ ገዥዉ ብልፅግና የመንግሥት ሠራተኞችን በግዳጅ የፓርቲ አባል የማድረግ እርምጃን እንዲያቆም ጠየቀ።-የተመድ በሱዳን ዳርፉር የምትገኘውን ኤል-ፋሸር ከተማን የተቆጣጠረዉን በሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ጦር ርምጃ በጥብቅ አወገዘ።
    13 min
  • የጥቅምት 19 ቀን 2018 የዓለም ዜና
    -የዩናይትድ ስቴትስ ጦር ባለፈዉ ሚዚያ የመን እስር ቤት ዉስጥ የነበሩ ስደተኞችን መግደሉ የጦር ወንጀል ሊሆን እንደሚችል የመብት ተሟጋቾች አስታወቁ።በጥቃቱ የተገደሉት አብዛኞቹ ኢትዮጵያዉያን ሳይሆኑ እንዳልቀረ ተነግሯል።---የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ጦር ኤል ፋሻር በተባለችዉ ከተማ የሚኖሩ ሰላማዊ ሰዎችን መግደሉ ዓለም አቀፍ ተቃዉሞና ዉግዘት አስከትሏል።----ሩሲያ በሁለት ቀናት ልዩነት ዉስጥ የኑክሌር አረር መሸከም የሚችሉ አዳዲስ ሚሳዬልና የዉሐ ዉስጥ ሰዉ አዉልባ አዉሮፕላን ሞከረች።የመሳሪያዎቹን ሙከ,ራ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ተቃዉመዉታል።
    12 min
  • የጥቅምት 18 ቀን 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና
    የሕዝብ ተወካዮች ምክርቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 5ተኛው የሥራ ዘመን 2ኛው መደበኛ ስብሰባው ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ ያቀረቡትን የ2018 ዓ.ም የመንግሥት የትኩረት አቅጣጫ በአንድ ድምጸ ተአቅቦ በአብላጫ ድምጽ አጸደቀ። በኬንያ አንድ አነስተኛ አውሮፕላን በመስከሱ ቢያንስ 11 ሰዎች መሞታቸውን የሐገሪቱ የስቢል አቭዬሽን ባለሥልጣን አስታወቀ። የሕዝብ ዓመፅ ተገን አድርገው የሐገሪቱን ፕሬዝደንት ያስወገዱት የማዳጋስካር ወታደራዊ ሁንታ በዛሬው ዕለት በአብዛኛው ስቪሎችን ያካተተ የካቢኔ አባላት መሰየማቸውን አስታወቁ።
    12 min
  • የጥቅምት 17 ቀን 2018 ዓ/ም የዓለም ዜና
    • በምዕራብ ዳርፉር ኤልፋሽር ቀውሱ ተባብሶ ሊቀጥል ይችላል የሚል ስጋት እንደገባው የመንግሥታቱ ድርጅት አስጠነቀቀ። • ሁለቱ ምዕራብ አፍሪቃዉያን አዛውንቶች ፕሬዚዳንታዊ ምርጫውን አሸነፉ ። • የማሊ ፍርድ ቤት በቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር ላይ እስራት ፈረደ። • የአሜሪካው ምክትል ፕሬዚዳንት ጄዲ ቫንስ ምስራቅ አፍሪቃዊቷን ሀገር ኬንያን ሊጎበኙ ነው። • በሊባኖስ የተሰማራው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰላም አስከባሪ ኃይል «ከእስራኤል ሳይቃጣብኝ አይቀርም» ያለውን የሰው አልባ አውሮፕላን ማለትም ድሮን መትቶ መጣሉን አስታወቀ።
    12 min
  • DW Amharic የጥቅምት 16 ቀን 2018 የዓለም ዜና
    የጅቡቲ ምክር ቤት በሀገሪቱ ሕገ-መንግሥት ለፕሬዝደንትነት የሚወዳደሩ ዕጩዎች ላይ የተጣለው የዕድሜ ገደብ እንዲነሳ የቀረበ የውሳኔ-ሐሳብ በሙሉ ድምጽ አጸደቀ። የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይል የአል-ፋሺር ከተማን ሙሉ በሙሉ መቆጣጠሩን አስታወቀ። ቀይ መስቀል እና የግብጽ ባለሙያዎች በጋዛ ሠርጥ የታጋቾችን አስከሬኖች የእስራኤል ጦር ከሚቆጣጠራቸው አካባቢዎች አልፈው እንዲያፈላልጉ ተፈቀደላቸው። ሩሲያ “ቢሮቬስኒክ” የተባለ አዲስ ኑክሌር ተሸካሚ ተወንጫፊ ሚሳይል የመጨረሻ ሙከራ በስኬት ማጠናቀቋን አስታወቀች።
    የፈረንሳይ ባለሥልጣናት ባለፈው ሣምንት ከሉቭ ሙዚየም ውድ ጌጣ ጌጦች ሰርቀዋል የተባሉ ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ሥር አዋሉ።
    8 min

About የዓለም ዜና

From the publisher's feed

ዶይቼ ቬለ የዕለቱን ዋና ዋና ዜናዎች ከኢትዮጵያ እና ከመላው ዓለም በየቀኑ ያቀርባል። የኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ፖለቲካዊ እና ኤኮኖሚያዊ ጉዳዮችን ጨምሮ የመላው ዓለምን ውሎ የተመለከቱ ጠቃሚ መረጃዎች በሰባቱም የሣምንቱ ቀናት ከምሽቱ አንድ ሰዓት ከዶይቼ ቬለ ያድምጡ። የዶይቼ ቬለን ዜናዎች በአፕል ፖድካስት…