የዓለም ዜና

የዓለም ዜና

Download on the App Store

የዓለም ዜና episodes

  • የጥቅምት 6 ቀን 2018 ዓ.ም. የዜና መጽሔት
    በዜና መጽሔት
    -IOM የኢትዮጵያን የ5 ዓመታት የሥራ ፍኖተ ካርታ ይፋ ማድረጉ፤
    -የትግራይ ኃይሎች ተቃውሞን ማኅበረሰቡም እንዲቀላቀል ተቃዋሚዎች ጥሪ ማስተላለፋቸው፤
    -የፓርቲዎች የመንቀሳቀሻ ሜዳ ጠበበ ወይስ ሠፋ? እንዲሁም
    -የኦሮሚያ እና ሶማሊ አዋሳኞች ግጭት ላይ ያተኮሩ ዘገባዎች ይቀርባሉ።
    19 min
  • የጥቅምት 5 ቀን 2018 ዓ.ም. የዓለም ዜና
    በደቡብ ኢትዮጵያ 11 ተቃዋሚ ፓርቲዎች የተሰባሰቡበት «የሰላም ጥምረት» የፓርቲ አመራሮችና አባላት ላይ ድብደባና እሥር እየተፈጸመ ነው አለ። የአርባምንጭ ከተማ ፖሊስ በበኩሉ አባላቱ የተያዙት በፓርቲ አባልነታቸው ሳይሆን በወንጀል በመጠርጠራቸው እንደሆነ ይገልጻል።
    የሱዳን ዋና ከተማ ኻርቱም በዛሬው ዕለት በተከታታይ የሰው አልባ አውሮፕላን ጥቃት ተፈጸመባት።
    አንጋፋው የኬንያ የተቃውሞ ፖለቲካ መሪ ራይላ ኦዲንጋ አረፉ።
    ጀርመን ዮሮ ተዋጊ ጀቶችን በፖላንድ ወታደራዊ የአየር ጦር ሰፈር ልታሰፍር ነው።
    10 min
  • የጥቅምት 4 ቀን 2018 የዓለም ዜና
    -የትግራይ መከላከያ ኃይል የሚባለዉ ወታደራዊ ሥብስብ አባላት የደሞዝና ሌሎች ጥቅማ ጥቅሞች እንዲከበሩላቸዉ በመጠየቅ የጀመሩት ተቃዉሞ ተጠናክሮ ቀጥሏል።ትናንት የመቀሌን ዛሬ ደግሞ ከመቀሌ-አድግራት መንገድን ዘግተዉ ዉለዋል።---የማዳጋስካር ጦር ኃይል የሐገሪቱን የመንግሥትነት ሥልጣን መቆጣጠሩን አስታወቀ።ጦሩ ሥልጣን መያዙን ያስታወቀዉ የተደበቁት ፕሬዝደንት የማዳጋስካርን ፓርላማ መበተናቸዉን ካስታወቁ ከሰዓታት በኋላ ነዉ።---በእስራኤል ጦር ድብደባና በምግብ እጦት ለረሐብ ለተጋለጠ,ዉ የጋዛ ሕዝብ ሰብአዊ ርዳታ ለማቅረብ ሁሉም መተላለፊያዎች እንዲከፈቱ ለጋሽ ድርጅቶች ጠየቁ
    12 min
  • የጥቅምት 3 ቀን 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና
    በትራፊክ አደጋ የ13 ሠዎች ህይወት አለፈ፡፡የማዳጋስካር ፕረዚደንት ከሐገር ወጡ። የማዳጋስካር ፕረዚደንት ከሐገር ወጡ። የትራምፕ የእስራኤል ጉብኝት፤ 1,400 ለሳይበር ጥቃት ሲውሉ የነበሩ ድረ ገጻች መዘጋታቸውን ፤ሩስያ የኔቶ አባል ሐገራት ልታጠቃ ትችላለች መባሉን
    11 min
  • የጥቅምት 2 ቀን 2018 ዓ/ም የዓለም ዜና
    • ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ ከሶማሊያው ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼክ መሐሙድ ጋር መወያየታቸውን አስታወቁ ። የማዳጋስካሩ ፕሬዚዳንት በሀገሪቱ «ስልጣኑን በኃይል ለመቆጣጠር ሙከራ » እየተደረገብኝ ነው አሉ።እስራኤል በጋዛ ሰርጥ በሃማስ እጅ ታግተው የሚገኙ 20 ታጋቾችን ለመቀበል መዘጋጀቷን አስታወቀች።ጀርመን ወጣት ሶሪያዉያንን ወደ ሃገራቸው ለመመለስ ዝግጅት ማድረግ መጀመሯን አስታወቀች ።• ፍልስጥኤማዊው የፎቶ ጋዜጠኛ ሳሄር አልግሆራ የባዩ የጦርነት ዘጋቢ ሽልማት አሸነፈ።
    9 min
  • የጥቅምት 1 ቀን 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና
    የሰዎች ከቦታ ቦታ የመንቀሳቀስ መብት አሳሳቢ በሆነ ሁኔታ እየተጣሰ ነው ሲል የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) አመለከተ፡፡ እስራኤል ዛሬ በደቡብ ሊባኖስ በፈጸመችው «መጠነ ሰፊ» የተባለለት የአየር ጥቃት 1 ሰው ሲገደል 7 መቁሰላቸውን የሐገሪቱ የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ። ጓቲማላ ከዩናይትድ ስቴትስ የተባረሩ የመጀመሪያው ዙር ስደተኞች ተቀበለች። ስደተኞቹ የራሷ እና የሁንድራስ መሆናቸውን ታውቋል። የሰብአዊ መብት ተከራካሪዎች ድርጊቱን አውግዘዋል።
    16 min
  • የዐርብ መስከረም 30 ቀን፣ 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና
    ሶዶ፥ ከኦሮሚያ ክልል የተነሱ ታጣቂዎች ምሥራቅ ጉራጌ ዞን ውስጥ ጥቃት ፈጽመው ሰዎች ገደሉ፤ አ.አ፥ የዓለም ምግብ ድርጅት ኢትዮጳያ ለተጠለሉ ስደተኞች የሚሰጠውን ርዳታ ሊያቆም ጫፍ መድረሱን ገለጠ፤ ጋዛ፥ ጋዜጠኛ ተስፋለም ወልደየስ ተሸለላሚ ሆነ፤ ዖስሎ፥የቬኔዙኤላ ተቃዋሚ መሪ ማሪያ ኮሪና ማቻዶ የሰላም ኖቤል አሸነፉ፤ ዋሽንግተን፥ ዋሕይትሐዋስ ትራምፕ ከኖቤል ሽልማት ውጪ መደረጋቸውን «ፖለቲካን ከሰላም ያስቀደመ» አለ፤ ሞስኮ፥ትራምፕ ለሰላም ብዙ መልፋታቸውን ፑቲን ተናገሩ፤ ጋዛ፥ የእሥራኤል ጦር ከተወሰኑ የጋዛ አካባቢዎች መውጣት ጀመረ
    11 min
  • የዓለም ዜና፤ መስከረም 29 ቀን 2018 ሐሙስ
    አርስተ ዜና-እስራኤልና ሀማስ በዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ «የመጀመሪያው ምዕራፍ» የሰላም እቅድ ተስማሙ። ስምምነቱ ሲበሰር ፍልስጤማውያንም ከተጠለሉባቸው የመጠለያ ጣቢያዎች በመውጣት ደስታቸውን በሆታ ገልጸዋል። በሺህዎች የሚቆጠሩ እስራኤላውያን ደስታቸዉን ለመግለፅ አደባባይ ወተዋል። ኢራን በበኩልዋ የዘር ጭፍጨፋን የሚያቆም ስምምነትን ሁሉ በደስታ እንደምትቀበል ገልፃለች።-ልትወጋኝ እየተዘጋጀት ነው ስትል ኢትዮጵያ የከሰሰቻት ኤርትራ ክሱን ወታደራዊ ፀብ አጫሪነት ስትል ውድቅ አደረገች። -አፍጋኒስታን ውስጥ የማህበራዊ ሚዲያ መድረኮችን መጠቀም የተከለከለ መሆኑ ተሰማ። ቲክቶክ ከታገደ ሁለት ዓመት ሆኖታል።
    12 min
  • የመስከረም 28 ቀን 2018 የዓለም ዜና
    -ኤርትራና ህወሓት ኢትዮጵያን ለመዉጋት እየተዘጋጁ ነዉ በማለት የኢትዮጵያ መንግሥት ከሰሰ።የኢትዮጵያ ዉጪ ጉዳይ ሚንስቴር ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በፃፈዉ ደብዳቤ እንዳለዉ የኤርትራ መንግሥትና «አክራሪ» ያለዉ የህወሓት አንጃ ፋኖን ይረዳሉ፣ ኢትዮጵያን ለመዉረርም እየተዘጋጁ ነዉ።---የእስራኤል ጦር ሁለት ሳምንት ሳይሞላ ለሁለተኛ ጊዜ ለጋዛ ሕዝብ ርዳታ የጫኑ የጀርልባዎች ቅፍለትን አገደ።145 በጎ አድራጊዎችን ያዘ።-የሩሲያና የ,ዩናይትድ ስቴትስ ዉዝግብ እየተካረረ ነዉ።ዩናይትድ ስቴትስ የኑክሌር ቦምብ ለመሞከር፣ ለዩክሬን ኑክሌር ማወንጨፍ የሚችል ሚሳዬል ለማስታጠቅም ተዘጋጅታለች በማለት ሩሲያ ወቅሳለች።
    12 min
  • የማክሰኞ መስከረም 27 ቀን፣ 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና
    አ.አ፥ ስለ 7ኛው ዙር ምርጫ የፓርቲዎች አስተያየት፤ ለጎፋ ተፈናቃዮች የተዋጣ 60 ሚሊዮን ብር ሊዘርፉ የሞከሩ ተያዙ፤ ካይሮ፥ የጀርመን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በጋዛ ሰላም ለማስፈን የትራምፕ ሐሳብ መስመር እየያዘ መሆኑን ገለጡ፤ ቤርሊን፥ ሐማስ እሥራኤል ውስጥ በድንገት የፈጸመው የሽብር ጥቃት መታሰቢያ በመላው ጀርመን ተካሄዷል፤ ሩር፥ ምዕራብ ጀርመን ውስጥ አዲስ የተመረጡ ከንቲባ በርካታ ቦታ በጩቤ ተወግተው ተገኙ፤ ካሊፎርኒያ፥ በህክምና ሔሊኮፕተር መከስከስ ሦስት ሰዎች ተጎዱ፤ በፊዚክስ ዘርፍ ሦስት የአሜሪካ ሳይንቲስቶች የኖቤል አሸናፊ ሆኑ
    11 min

About የዓለም ዜና

From the publisher's feed

ዶይቼ ቬለ የዕለቱን ዋና ዋና ዜናዎች ከኢትዮጵያ እና ከመላው ዓለም በየቀኑ ያቀርባል። የኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ፖለቲካዊ እና ኤኮኖሚያዊ ጉዳዮችን ጨምሮ የመላው ዓለምን ውሎ የተመለከቱ ጠቃሚ መረጃዎች በሰባቱም የሣምንቱ ቀናት ከምሽቱ አንድ ሰዓት ከዶይቼ ቬለ ያድምጡ። የዶይቼ ቬለን ዜናዎች በአፕል ፖድካስት…