የዓለም ዜና

የዓለም ዜና

Download on the App Store

የዓለም ዜና episodes

  • የመስከረም 16 ቀን 2018 የዓለም ዜና
    የመስቀል ደመራ ክብረ በዓል ፣ ኢትዮጵያ እና ሩሲያ የኒውክሌር ኃይል ማመንጫ ጣቢያ ለመገንባት ተፈራረሙ ፣ በደቡብ ሱዳን የተጠናከፈው አመፅ፣ ዩናይትድ ስቴትስ የላይቤሪያ የቀድሞ የአማፂያን አዛዥን በግዳጅ መለሰች፣ የትራምፕ አስተዳደር ለውጭ ሀገር ዜጎች የንግድ መንጃ ፈቃድ እንዳያገኙ ገደብ ጣለ
    10 min
  • የሐሙስ መስከረም 15 ቀን፣ 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና
    ሙጃ፥ ሰሜን ወሎ በመንግሥት ጦር እና በፋኖ ታጣቂዎች ውጊዪያ እየተደረገ ነው፤ መቐለ፥ ስምንት የሲቪል ማኅበራት ለሰላም ጥሪያቸው በጎ ምላሽ አለማግኘታቸውን ዐሳወቁ፤ ፓሪስ፥ የፈረንሳይ የቀድሞ ፕሬዚደንት አምስት ዓመት ተፈረደባቸው፤ ሮም፥ ጣሊያን እና ስፔን ለጋዛ ሠርጥ ነዋሪዎች ርዳታ የጫነች መርከብን ለማገዝ የጦር መርከቦችን አሰማሩ፤ ጋዛ፥ በእሥራኤል ጦር ጄቶች ጥቃት ቢያንስ 17 ሰዎች ተገደሉ፤ ዴልሂ፥ ሕንድ ሕይወት ያጠፋ ነውጥ በተቀሰቀሰባት ላዳክህ ውስጥ አስቸኳይ ጊዜ አወጀች
    11 min
  • የመስከረም 14 ቀን 2018 የዓለም ዜና
    የኢትዮጵያ ፀጥታ አስከባሪዎች ከሶስት ሳምንት በፊት ያሰሯቸዉ ሁለት የሸገር ኤፍ ኤም ጋዜጠኞች ዛሬ በዋስ ተለቀቁ።ጋዜጠኞቹ እንዲለቀቁ የተለያዩ መገናኛ ዘዴዎችና የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ተቋማት ሲጠይቁ ነበር።-ለጋዛ ሕዝብ ርዳታ ጭነዉ የነበሩ ጀልባዎችን የእስራኤል ጦር በሰዉ አልባ አዉሮፕላን ደብድቧል መባሉ እንዲጣራ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጠየቀ---።የእስራኤል ጦር ዛሬ ጋዛ ዉስጥ 40 ሰዎችን ገድሏል።---የሩሲያና የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃል ኪዳን ድርጅት (ኔቶ) አባል ሐገራት ጠብና ፍጥጫ እየከረረ ነዉ።ትንሺቱ የቀድሞ የሶቭየት ሕብረት ሪፐብሊክ ኢስቶኒያ ከሩሲያ ጋር የሚያዋስናትን ድንበር እያጠረች ነዉ።
    11 min
  • የማክሰኞ መስከረም 13 ቀን፣ 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና
    ቦን፥ የደኅንነት ስጋት እንዳሳሰባቸው የጃራ ተፈናቃዮች መጠለያ ነዋሪዎች ገለጡ፤ ለንደን፥ ኢትዮጵያዊው ተገን ጠያቂ በወሲባዊ ጥቃት 12 ወራት ተበየነበት፤ ናይሮቢ፥ የኬንያ አየር ማረፊያ ሠራተኞች አድማ ለመምታት የሰባት ቀናት ገደብ ሰጡ፤ ርፉር፥ ሱዳን ውስጥ በኮሌራ የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር ከ3,000 መብለጡ ተገለጠ፤ ባማኮ፥ በወታደራዊ ኹንታ የሚመሩ ሦስት የምዕራብ አፍሪቃ አገራት ከ(ICC)መውጣታቸውን በይፋ ዐሳወቁ፤ ዋሽንግተን፥ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ አንቲፋን አሸባሪ ሲሉ ፈረጁ፤ ብራስልስ፥ ኔቶ የአየር ክልል እየጣሰች ነው ያላትን ሩስያን አስጠነቀቀ
    12 min
  • የመስከረም 12 ቀን 2018 ዓ.ም. የዓለም ዜና
    የመስከረም 12 ቀን 2018 ዓ.ም. አርዕስተ ዜና
    የኢትዮጵያ መንግሥት ባለሥልጣናት ፣ነጻ ጋዜጠኞችን ማዋከብን እንዲያቆሙ ተጠየቁ። ሂዩመን ራይትስ ዋች ዛሬ ባወጣው መግለጫ ፣ሀሳባቸውንና አመለካከታቸውን በነጻነት የመግለጽ መብታቸውን በመጠቀማቸው የታሰሩትን በሙሉም በአስቸኳይ እንዲለቁ ጥሪ አቅርቧል።
    ባሕር ዳር ከተማ አቅራቢያ በደረሰ የመኪና አደጋ 3 የአንድ ቤተሰብ አባላትን ጨምሮ 11 ሰዎች ሞቱ ። 10 ሰዎችም ቆሰሉ
    ለፍልስጤም መንግስት እውቅና የሚሰጡ ሀገራት ቁጥር እየጨመረ ነው። ዛሬ ኒውዮርክ በሚካሄድ ጉባኤ ተጨማሪ ሀገራት ለፍልስጤም መንግሥት እውቅና ይሰጣሉ ተብሎ እየተጠበቀ ነው።
    12 min
  • የመስከረም 11 ቀን 2018 የዓለም ዜና
    የዛሬው የዓለም ዜና በካፋ ዞን በህዝብ ማመላለሻ አውቶብስ ላይ በደረሰ አደጋ በ27 ሰዎች ላይ ጉዳት መድረሱ ፣ብሪታንያ፣ ካናዳ እና አውስትራሊያ በዛሬው ዕለት ለፍልስጤም መንግስትነት በይፋ እውቅና መስጠታቸውን እና ርምጃው በእስራኤል እና በዩናይትድ ስቴትስ ዘንድ ውግዘት ማስከተሉን፤በቁጥጥር ስር የዋሉት የደቡብ ሱዳን የቀድሞ ምክትል ፕሬዝዳንት ነገ ፍርድ ቤት ይቀርባሉ መባሉን እንዲሁም የኬንያ አትሌቶች ዛሬ በተካሄደው የበርሊን ማራቶን በሁለቱም ፆታዎች ማሸነፋቸውን ያስቃኛል።
    9 min
  • DW Amharic የመስከረም 10 ቀን 2018 የዓለም ዜና
    የኢትዮጵያ መንግሥት አራት ጄኔራልነትን ጨምሮ ለ66 ከፍተኛ ወታደራዊ የጦር መኮንኖች ማዕረጎች ሰጠ። ኢትዮጵያ የአፍሪካ ቀንድን ቀጠና “ሰላም ለማጠናከር ባላት ቁርጠኝነት” እንደተበረታቱ በአሜሪካ ውጪ ጉዳይ መሥሪያ ቤት የአፍሪካ ጉዳዮች ከፍተኛ አማካሪ ማሳድ ቡሎስ ተናገሩ። እስራኤል በጋዛ በፈጸመቻቸው ጥቃቶች 34 ፍልስጤማውያን መገደላቸውን የጤና ባለሥልጣናት አስታወቁ። የዩክሬን ፕሬዝዳንት ቮሎዶሚር ዜሌንስኪ ከአሜሪካ አቻቸው ዶናልድ ትራምፕ እንደሚገናኙ አስታወቁ። የአሜሪካ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ የኤች-ዋን ቢ (H-1B) ቪዛ አመልካቾች በዓመት 100,000 ዶላር እንዲከፍሉ የሚያስገድድ ትዕዛዝ አጸደቁ።
    11 min
  • የመስከረም 9 ቀን 2018 የዓለም ዜና
    አርዕሥተ ዜና፣
    -ከሁለት ሳምንት በፊት አዲስ አበባ ዉስጥ የታሰሩ ሁለት ኢትዮጵያዉያን ጋዜጠኞች ፍርድ ቤት በዋስ እንዲለቀቁ ቢወስንም አለመለቀቃቸዉን ባልደረቦቻቸዉ አስታወቁ።የጋዜጠኞች መብት ተሟጋቾች ጋዜጠኞቹ እንዲለቀቁ እየጠየቁ ነዉ።---የጋዛ ጦርነት ለዛላቂዉ እንዲቆም፣እስራኤል ለጋዛ ሕዝብር ርዳታ እንዳይደርስ የጣለችዉ እገዳ እንዲነሳና ሐማስ ያገታቸዉ እስራኤላዉን እንዲለቀቁ ለፀጥታዉ ጥበቃ ምክር ቤት የቀረበዉን ረቂቅ ዉሳኔ ዩናይትድ ስቴትስ ዉድቅ አደረገችዉ።----ሳዑዲ አረቢያ የሚደርስባትን ጥቃት ለመከላከል የፓኪስታንን የኑክሌር መሳሪያና ዕዉቀት ልትጠቀም እንደምትችል ኢስላምአባድ አስታወቀች።
    12 min
  • የመስከረም 8 ቀን 2018 ዓ/ም የዓለም ዜና
    የአፍሪካ ኅብረት በሱዳን የተኩስ አቁም ላይ እንዲደረስ እና በሀገሪቱ የሚመራ ውይይት ለማስጀመር ጥረቱን እንደቀጠለ የኅብረቱ ኮሚሽን ሊቀ-መንበር ማሕሙድ አሊ ይሱፍ ተናገሩ። ኮንጎ ውስጥ በድጋሚ የተከሰተው የኢቦላ ወረርሽኝ በአጭር ጊዜ ውስጥ የበርካቶች ህይወት መቅጠፉን የዓለም የጤና ድርጅት አስታወቀ። ሳዑዲ አረቢያ እና የኑኩልየር የጦር መሳሪያ የታጠቀችው ፓኪስታን አንዱ ሌላውን ካልታሰበ ጥቃት ለመከላከል የሚያስችል ነው የተባለለት ስምምነት ደረሱ ።
    12 min
  • የመስከረም 7 ቀን 2018 ዓ.ም. የዓለም ዜና
    የመስከረም 7 ቀን 2018 ዓ.ም. አርዕስተ ዜና
    አቶ ክርስቲያን ታደለ እና አቶ ዮሐንስ ቧያለው መታመማቸውን ጠበቃቸው ተናገሩ። ሁለቱ የምክር ቤት አባላት በሀገር ውስጥ የተሻለ ህክምና ማግኘት እንደሚፈልጉም ለጠበቃቸው ነግረዋቸዋል።
    ወደ ግሪክ በመጓዝ ላይ በነበረች የበፕላስቲክ ጀልባ ሲጋዙ የነበሩ ቢያንስ 50 የሱዳን ስደተኞች በምሥራቅ ሊቢያ የባህር ጠረፍ ላይ መሞታቸውን IOM አስታወቀ።
    ትናንት ማምሻውን ከባለቤታቸውና ከአሜሪካ ባለሥልጣናት ጋር ብሪታንያ የገቡት የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ዛሬ በዊንድሶር ቤተ መንግስት በእንግሊዙ ንጉስ ሳልሳዊ ቻልርስ ዘውዳዊ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።
    9 min

About የዓለም ዜና

From the publisher's feed

ዶይቼ ቬለ የዕለቱን ዋና ዋና ዜናዎች ከኢትዮጵያ እና ከመላው ዓለም በየቀኑ ያቀርባል። የኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ፖለቲካዊ እና ኤኮኖሚያዊ ጉዳዮችን ጨምሮ የመላው ዓለምን ውሎ የተመለከቱ ጠቃሚ መረጃዎች በሰባቱም የሣምንቱ ቀናት ከምሽቱ አንድ ሰዓት ከዶይቼ ቬለ ያድምጡ። የዶይቼ ቬለን ዜናዎች በአፕል ፖድካስት…