የዓለም ዜና

የዓለም ዜና

Download on the App Store

የዓለም ዜና episodes

  • የመስከረም 7 ቀን 2018 ዓ.ም. የዓለም ዜና
    የመስከረም 7 ቀን 2018 ዓ.ም. አርዕስተ ዜና
    አቶ ክርስቲያን ታደለ እና አቶ ዮሐንስ ቧያለው መታመማቸውን ጠበቃቸው ተናገሩ። ሁለቱ የምክር ቤት አባላት በሀገር ውስጥ የተሻለ ህክምና ማግኘት እንደሚፈልጉም ለጠበቃቸው ነግረዋቸዋል።
    ወደ ግሪክ በመጓዝ ላይ በነበረች የበፕላስቲክ ጀልባ ሲጋዙ የነበሩ ቢያንስ 50 የሱዳን ስደተኞች በምሥራቅ ሊቢያ የባህር ጠረፍ ላይ መሞታቸውን IOM አስታወቀ።
    ትናንት ማምሻውን ከባለቤታቸውና ከአሜሪካ ባለሥልጣናት ጋር ብሪታንያ የገቡት የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ዛሬ በዊንድሶር ቤተ መንግስት በእንግሊዙ ንጉስ ሳልሳዊ ቻልርስ ዘውዳዊ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።
    9 min
  • የመስከረም 6 ቀን 2018 ዓ.ም. የዓለም ዜና
    የደቡብ ሱዳን ባለሥልጣናት ሀገሪቱ ነጻነቷን ካገኘችበት ጊዜ ጀምሮ በሚሊየኖች የሚቆጠር ዶላር መዝረፋቸውን የተመድ አስታወቀ። የጁባ መንግሥት ክሱን አስተባብሏል።
    እስራኤል ዛሬ በማለዳ ጋዛ ከተማ ላይ የተገመተውን የምድር ጥቃት ጀመረች። እርምጃዋ ከተመድ ጠንካራ ትችት አስከትሏል።
    ባለፈው ዓመት ጀርመን ውስጥ በተካሄደ የተቃውሞ ሰልፍ ላይ የፖሊስ መኮንን በስለት ወግቶ የገደለ የአፍጋኒስታን ዜጋ በዛሬው ዕለት የዕድሜ ልክ እስራት ተፈረደበት።
    የታሊባን መሪዎች በአንድ የአፍጋኒስታን ክፍለ ሀገር ውስጥ ገመድ አልባ የኢነርኔት አገልግሎት ወይም ዋይፋይ አገዱ። ምክንያቱ ኢስነምግባራዊነትን ለመከላከል የሚል ነው።
    12 min
  • የመስከረም 5 ቀን 2018 ዓ.ም. የዓለም ዜና
    የመስከረም 5 ቀን 2018 ዓ.ም. አርዕስተ ዜና
    እስራኤል ዛሬ በጋዛ ከተማ በፈጸመችው የአየር ድብደባ ቢያንስ 16 ፍልስጤማውያን መገደላቸውንና ህንጻዎችም መውደማቸውን የፍልስጤም ባለሥልጣናት አስታወቁ።
    እስራኤል በጋዛ ሲቲ የአየር ድብደባ ባካሄደችበት በዛሬው እለት የዩናይትድ ስቴትስ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩብዮ መንግስታቸው እስራኤልን እንደሚደግፍ ተናግረዋል። ሩብዮ ሀማስ እንደታጣቂ ቡድን ህልውናው ማክተም እንዳለበትም ተናግረዋል።
    ሩስያ ሀብቴን ለመውሰድ በሚቃጣ ማንኛውንም ሀገር ላይ እርምጃ እወስዳለሁ ስትል ዛሬ የአውሮፓ መንግስታትን አስጠነቀቀች።
    ዜናው በዝርዝር
    10 min
  • የመስከረም 4 ቀን 2018 ዓ/ም የዓለም ዜና
    • በኢትዮጵያ ባለፈው ዓመት የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ሀገር አቀፍ ፈተና ከወሰዱ ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ተማሪዎች መካከል 8.4 በመቶው ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚያስገባ ውጤት ማግኘታቸውን የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ።
    • የመሐመድ ሐምዳን ደጋሎ የሱዳን የፈጥኖ ደራሽ ኃይል በሀገሪቱ ደቡባዊ ክፍል የሚገኙ ቁልፍ የብሔራዊው ጦር ይዞታዎች እና የህዝብ መገልገያ የመሰረተ ልማቶችን በድሮን እንዳጠቃ አንድ ከፍተኛ የጦር መኮንን ተናገሩ።
    • እስራኤል በጋዛ ማዕከላዊ ክፍል የምትወስደውን ወታደራዊ እርምጃ ስታጠናክር የከተማዋ ነዋሪዎች ከዛሬ ማለዳ ጀምሮ ለቀው መውጣት ጀመሩ ።
    9 min
  • የመስከረም 3 ቀን 2018 ዓ/ም የዓለም ዜና
    • አሜሪካ ፣ ሳኡዲ አረቢያ ፣ የተባበሩት አረብ ኤሜሬቶች እና ግብጽ በሱዳን ለሶስት ወራት የሚቆይ የሰብአዊ ሽግግር እንዲደረስ ጥሪ አቀረቡ ።
    • የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የሰሜን አትላንቲክ የጦር ቃልኪዳን ድርጅት ወይም ኔቶ ቅድመ ሁኔታውን ከተወጣ ሩስያን በማዕቀብ ለመቅጣት መዘጋጀታቸውን አስታወቁ ።
    • እስራኤል ዛሬ በጋዛ ሰርጥ ባደረሰችው የአየር ጥቃት ከሰላሳ በላይ ሰዎች መገደላቸውን የፍልስጥኤማዉያን የህክምና ምንጮች አስታወቁ ።
    • እንግሊዝ ባህር አቋርጠው ግዛቷ የገቡትን ስደተኞች ከቀጣዩ ሳምን ት ጀምሮ ወደ ፈረንሳይ መመለስ ልትጀምር ነው።
    11 min
  • የመስከረም 2 ቀን 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና
    የዛሬው የዓለም ዜና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ውይይት ኮሚሽን በቀሪዎቹ ወራት ቀሪውን የኮሚሽኑ ስራዎች ማጠናቀቅ አይችልም መባሉን፤የደቡብ ሱዳን ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝዳንት በአገር ክህደት እና በነፍስ ግድያ መከሰሳቸውን፤አልሸባብ በማዕከላዊ ሶማሊያ የምትገኝ አንዲት ከተማ መቆጣጠሩን ማስታወቁ፤የአውሮፓ ህብረት ኮሚሽን በሩሲያ ላይ ተጨማሪ ማዕቀብ ለጥል ነው መባሉ፤ሩሲያ እና ቤላሩስ በጋራ የጦር ልምምድ መጀመራቸውን ተከትሎ በአውሮፓ እና በሩሲያ መካከል ውጥረት መንገሱን፤በአሜሪካዊዉ ቻርሊ ኪርክ ግድያ የተጠረጠረው ግለሰብ መያዙን ኢትዮጵያዊቷ የመካከለኛ ርቀት ሯጭ ድሪቤ ዌልቴጂ ከአለም የትራክ ሻምፒዮና መታገዷን ያስቃኛል።
    11 min
  • የመስከረም 1 ቀን 2018 የዓለም ዜና
    -ኢትዮጵያዉያን የዘመን መለወጪያ በዓልን ዛሬ አክብረዉ ዉለዋል።አዲሱ ዓመት ታላቁ የሕዳሴ ግድብ በተመረቀ ሳልስት በመዋሉ የድርብ በዓል ስሜት ተላብሷል።ይሁንና እስከ አምና ማብቂያ የቀጠሉት ግጭቶች፣ጥቃቶች፣ እገታና ዘረፋዎች ይቀጥላሉ የሚለዉ ሥጋት፣በዓሉን ስሜት በሥጋት አቃርጦታል።--የአፍሪቃ የአየር ንብረት ጉዳይ ጉባኤ አፍሪቃ የዓየር ንብረት ቀዉስን ለማስወገድ ለነደፈችዉ ዕቅድ በየዓመቱ 50 ቢሊዮን ዶላር እንደሚያስፈልጋት አስታወቀ።-የማሕበራዊ መገናኛ ዘዴዎች መዘጋት፣ የኑሮ ዉድነት፣ ሥራ አጥነትና ሙስና ያስመረራቸዉ የኔፓል ወጣቶች የጀመሩትን አመፅ እንደቀጠሉ ነዉ።
    12 min
  • የጳጉሜ 5 ቀን 2017 ዓ/ም ዓለም ዜና
    DW Amharic- የዛሬው የዓለም ዜና የዘንድሮው የበአል ገበያ ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ የታየበት ሲሉ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የሚገኑ ነዋሪዎች መግለፃቸውን፣ የውጭ ርዳታ መቀዛቀዝ የወባ በሽታ አደጋ እንዲጨምር ማድረጉን፣የአውሮፓ ህብረት ኮሚሽን በእስራኤል ላይ ከፊል የንግድ ማዕቀብ እንደሚያደርግ ማስታወቁን፣የጀርመን ፍርድ ቤት ግድያ በፈፀመ አንድ ሶሪያዊ ላይ የእድሜ ልክ እስራት መበየኑ፣ የኔፓል ጠቅላይ ሚኒስትር ከሥልጣን መልቀቃቸውን ተከትሎ ዋና ከተማዋን የሀገሪቱ ጦር መቆጣጠሩን የሚያስቃኙ ዘገባዎችን አካቷል።
    12 min
  • የጳጉሜ 4 ቀን 2017 ዓ/ም የዓለም ዜና
    • ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ የኢትዮጵያ የኅዳሴ ግድብ «የመላው ጥቁሮች ስኬት ነው » አሉ። • በምስራቃዊ ኮንጎ በደረሰ የታጣቂዎች ጥቃት በአንድ ምሽት ስልሳ ይህል ሰዎች ተገደሉ ። • የእስራኤል ጦር ኃይል በሃማስ ከፍተኛ አመራር ላይ ያነጣጠረ ነው ያለውን ጥቃት ቃጣር መዲና ዶሃ ውስጥ መፈጸሙን አስታወቀ። • ሩስያ በምስራቃዊ ዩክሬን ባደረሰችው ጥቃት ከ20 በላይ ሰዎች መገደላቸውን ዩክሬን አስታወቀች ።
    11 min
  • የጳጉሜ 3 ቀን 2017 ዓ.ም. የዓለም ዜና
    የጳጉሜ 3 ቀን 2017 ዓ.ም. የዓለም ዜና
    የአፍሪቃ መሪዎች የዓለም የአየር ንብረት ቀውስን በአረንጓዴ ኢንቬስትመንት በመቋቋም የዓለም አርአያ ለመሆን ማቀዳቸውን ዛሬ አስታወቁ።
    እስራኤል ሃማስ እጅ እንዲሰጥ አለበለዚያ 'መደምሰስ' እንደሚጠብቀው አስጠነቀቀች። የእስራኤል መከላከያ ሚኒስትር የመጨረሻ ባሉት ማስጠንቀቂያ «ታጋቾችን ልቀቁ የጦር መሣሪያዎቻችሁን አስቀምጡ አለያም ጋዛ እንድትጠፋ ትደረጋለች እናንተም ትደመሰሳላችሁ » ብለዋል።
    በመቶዎች የሚቆጠሩ ደቡብ ኮሪያውያን ሠራተኞች ጆርጅያ ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ በቁጥጥር ስር ከዋሉ በኋላ በደቡብ ኮርያውያን ግራ የሚያጋባ ድንጋጤንና መከዳትን የፈጠረ ስሜት አሳድሯል።
    11 min

About የዓለም ዜና

From the publisher's feed

ዶይቼ ቬለ የዕለቱን ዋና ዋና ዜናዎች ከኢትዮጵያ እና ከመላው ዓለም በየቀኑ ያቀርባል። የኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ፖለቲካዊ እና ኤኮኖሚያዊ ጉዳዮችን ጨምሮ የመላው ዓለምን ውሎ የተመለከቱ ጠቃሚ መረጃዎች በሰባቱም የሣምንቱ ቀናት ከምሽቱ አንድ ሰዓት ከዶይቼ ቬለ ያድምጡ። የዶይቼ ቬለን ዜናዎች በአፕል ፖድካስት…