የዓለም ዜና

የዓለም ዜና

Download on the App Store

የዓለም ዜና episodes

  • DW Amharic የጳጉሜን 2 ቀን 2017 የዓለም ዜና
    የኬንያው ፕሬዝደንት ዊሊያም ሩቶ ታላቁ የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ ሲመረቅ “የክብር እንግዳ” እንደሚሆኑ ጽህፈት ቤታቸው አስታወቀ። የቦኮ ሐራም ታጣቂዎች በሰሜን ምሥራቅ ናይጄሪያ በምሽት በፈጸሙት ጥቃት በርካታ ሰዎች መግደላቸውን የሀገሪቱ ባለሥልጣናት ገለጹ። ከቱርክ የባሕር ዳርቻ ስደተኞች የጫነ ጀልባ ዛሬ እሁድ ከሀገሪቱ የባሕር በር ጠባቂ መርከብ ጋር ተጋጭቶ አምስት ሰዎች ሕይወታቸውን አጡ። የእስራኤል ውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ሀገራት ለፍልስጤም ሀገርነት እውቅና ቢሰጡ ስህተት እንደሚሆን ተናገሩ። ሩሲያ በዩክሬን ባደረሰችው እጅግ ግዙፍ ጥቃት በመዲናዋ ኪዬቭ እምብርት የሚገኘውን የመንግሥት መቀመጫ መሥሪያ ቤት አጠቃች።
    8 min
  • የጳጉሜ 1 ቀን 2017 ዓ/ም የዓለም ዜና
    DW Amharic የዛሬው የዓለም ዜና፤ ለሕዳሴ ግድብ ግንባታ እስካሁን 233 ቢሊየን ብር ወጪ ተደርጓል መባሉ፤በሰሜን ጎንደር ጠለምት ወረዳ በድርቅ ሳቢያ 21 ሺህ አባዎራዎች ከ100ሺህ ቤተሰቦቻችው ጋር ችግር መሆናቸው፤እስራኤል ደቡባዊ ጋዛ ውስጥ 'ሰብዓዊ ቀጠና' መሰየሟ እና በሰሜናዊ ጋዛ ከተማ የሚገኙ ነዋሪዎችም ወደዚህ አካባቢ እንዲሸሹ በራሪ ወረቀት እየተበተነ መሆኑን፤በጀርመን የባቫሪያን ግዛት ጠቅላይ ሚንስትር የሀገሪቱን ወታደሮች ወደ ዩክሬን መላክን መቃወማቸውን እንዲሁም ዘለንስኪ፤ ፑቲን ሞስኮ ውስጥ ለመገናኘት ያቀረቡትን ሀሳብ ውድቅ ማድረጋቸውን ያስቃኛል።
    11 min
  • የነሐሴ 30 ቀን 2017 ዓ.ም. የዓለም ዜና
    የነሐሴ 30 ቀን 2017 ዓ.ም. አርዕስተ ዜና
    በአማራ ክልል፣ ኦሮሞ ብሔረሰብ ዞን ፣ የባቲ ከተማ አስተዳደር የፀጥታ ምክር ቤት፣ በአካባቢዉ ይንቀሳቀሳሉ ያላቸውን ታጣቂዎች ለመቆጣጠር ፣ የሰዓት እላፊ ገደብ መጣሉን አስታወቀ። የ
    አንድ የብሪታንያ ፍርድ ቤት በአንዲት ሴትና በአንዲት የ14 ዓመት ልጃገረድ ላይ ወሲባዊ ጥቃት በመፈጸም በተጠረጠረው አንድ ኢትዮጵያዊ ተገን ጠያቂ ላይ የጥፋተኝነት ብይን አሳለፈ። ዳኛው ተገን ጠያቂው ኢትዮጵያዊ ላይ በመጪው መስከረም 19 ቀን 2018 ዓም ብይን እንደሚሰጡ ተናግረዋል።
    ጀርመን ለአፍጋኒስታን የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ ሰለባዎች የ2.1 ሚሊዮን ዩሮ እርዳታ ልትሰጥ ነው።
    10 min
  • የዓለም ዜና፤ ነሐሴ 28 ቀን 2017 ዓ.ም ሐሙስ
    አርስተ ዜና፤
    --የኢትዮጵያ የገነባችዉ አጨቃጫቂ ያሉት ግዙፍ የሕዳሴ ግድብ ቀጣይነት ያለው "የመረጋጋት ስጋት" መሆኑን ግብፅና ሱዳን አስታወቁ። ሁለቱ ሃገራት፤ ኢትዮጵያ ከሃገራቱ ጋር ትብብርን ለመመስረት ፖሊሲዋን ማስተካከል ያስፈልጋታል ብለዋል።--1 ሺህ 500ኛው የመውሊድ በዓል ዛሬ በአዲስ አበባ በታላቁ አንዋር መስጅድ እና በተለያዩ የኢትዮጵያ ከተሞች በሚገኙ መስጂዶች በድምቀት ተከበረ።--በሰሜናዊ ሕንድ በተከሰተ የማያቋርጥ ዝናብ ምክንያት የዕለት ተዕለት ሕይወት መስተጓጎሉ ተሰማ።--በአፍጋኒስታን የተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ ከ 2,200 በላይ ሰዎችን ሕይወት አጠፋ። የሟቾች ቁጥር በእጥፍ ሊጨምር ይችላል ተብሏል።
    10 min
  • የነሐሴ 28 ቀን 2017 ዓ.ም. የዓለም ዜና
    በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ድባጢ ወረዳ በሚገኝ ገጠራማ ስፍራ በዛሬው ዕለት በታጣቂዎች እና መንግሥት ኃይሎች መካከል በተከሰተ ግጭት አራት ታጣቂዎች ሲገደሉ፤ የአንድ ጸጥታ ኃይል ሕይወት ማለፉ ተሰማ።
    የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዢ የነበሩት አቶ ማሞ ምሕረቱ ሥራቸውን መልቀቃቸውን አመለከቱ።
    ሱዳን ዳርፉር ግዛት ውስጥ በደረሰው የመሬት መንሸራተት አደጋ የሞቱት ከአንድ ሺህ በላይ ሰዎች እንደሚሆኑ ተነገረ።
    የቀድሞው የዴሞክራቲክ ኮንጎ የፍትህ ሚኒስትር የግንባታ ፕሮጀክት ገንዘብ በማጭበርበር የሦስት ዓመት እስራት ተፈረደባቸው።
    10 min
  • የማክሰኞ ነሐሴ 27 ቀን፣ 2017 ዓ.ም የዓለም ዜና
    አርዕስተ ዜና
    «ዓረና ትግራይ ለሉአላዊነት እና ዴሞክራሲ» ፓርቲ ትግራይ ክልል የሽግግር መንግሥት በአስቸኳይ እንዲመሰረት ጥሪ አቀረበ ።
    በአማራ ክልል፤ በዋግ ኸምራ ዞን አስተዳደር በረዶ እና ጎርፍ ብርቱ ጥፋት ማድረሱ ተገለጠ ።
    የርስ በርስ ጦርነት ባዳቀቃት ሱዳን ውስጥ በደረሰ የመሬት መንሸራተት አደጋ በርካታ የጦርነት ተፈናቃዮችን ጨምሮ ከ1,000 በላይ ሰዎች ሕይወት አለፈ ።
    አፍጋኒስታንን አናውጦ ከ1,400 በላይ ሰዎችን ሕይወት የቀጠፈው ብርቱ ርእደ-መሬት «በመቶ ሺህዎች ላይ» ተጽእኖውን እንደሚያሳርፍ ተጠቀሰ ። እስካሁን ቢያንስ 3251 ሰዎች ላይ የመቁሰል አደጋ መድረሱ ተዘግቧል ።
    11 min
  • የነሐሴ 26 ቀን 2017 ዓ.ም. የዓለም ዜና
    የነሐሴ 26 ቀን 2017 ዓ.ም.አርዕስተ ዜና
    የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለኢንቨስትመንት፣ ለቤትና ለመኪና ግዥ የሚውል 50 ቢሊዮን ብር በውጭ ሀገራት ለማኖሩ ኢትዮጵያውያን ለዳያስፖራ በመጪው 2018 ዓ.ም. ለማበደር መዘጋጀቱን አስታወቀ።
    ምሥራቅ አፍጋኒስታንን በመታው የመሬት መንቀጥቀጥ የሞቱት ሰዎች ቁጥር ወደ 812 መድረሱን የአፍጋኒስታን መንግሥት አስታወቀ። መንግሥት እንዳለው በአደጋው 2,817 ሰዎችም ቆስለዋል።
    የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ፣ ዩናይትድ ስቴትስ የጋዛ ሰርጥን እንድትቆጣጠርና ህዝቡንም ወደ ሌላ ቦታ ለማስፈር የወጣውን እቅድ እያጤኑ ነው መባሉን ሀማስ ተቃወመ።
    11 min
  • DW Amharic የነሐሴ 25 ቀን 2017 የዓለም ዜና
    መሐመድ ሐምዳን ደጋሎ የሱዳን ትይዩ መንግሥት መሪ ሆነው መሐላ ፈጸሙ። የሐማስ ወታደራዊ ክንፍ ቃል አቀባይ አቡ ኡቤይዳ በጋዛ መገደላቸውን የእስራኤል መከላከያ ሚኒስትር ገለጹ። ፕሬዝደንት ቮሎዶሚር ዜሌንስኪ ዩክሬን በሩሲያ ውስጥ ጥቃት ለመፈጸም ዕቅድ እንዳላት ተናገሩ። የሩሲያ መከላከያ ሚኒስትር ቫለሪ ጌራሲሞቭ ሀገራቸው ከመስከረም እስከ ሕዳር ተግባራዊ የሚሆን የጥቃት ዕቅድ ማዘጋጀቷን አስታውቀዋል። የቻይና እና የሕንድ መሪዎች በድንበር ይገባኛል የገቡበትን እሰጥ አገባ በመፍታት ትብብራቸውን ለማጠናከር ተስማሙ። ኢትዮጵያዊው ኃይለማርያም ኪሮስና ኔዘርላንዳዊቷ ሲፋን ሐሰን በሲድኒ ማራቶን የቦታውን ክብረ-ወሰን በማሻሻል አሸነፉ።
    9 min
  • የሐምሌ 24 ቀን 2017 የዓለም ዜና
    በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች ከባድ ዝናብ ያስከተለው ጎርፍ ከሐምሌ ወዲህ ቢያንስ በ125,000 ሰዎች ላይ ጉዳት አደረሰ። የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀ-መንበር ማሕሙድ አሊ ይሱፍ የሊቢያን ቀውስ ለማብቃት የተባበሩት መንግሥታት ላዘጋጀው ፍኖተ-ካርታ ድጋፋቸውን ገለጹ። የየመን ጠቅላይ ሚኒስትር እና ሌሎች ከፍተኛ ባለሥልጣናት በዚህ ሣምንት እስራኤል በፈጸመችው ጥቃት ተገደሉ። አሜሪካ በመስከረም በሚካሔደው የተባበሩት መንግሥታት ጠቅላላ ጉባኤ የፍልስጤም አስተዳደር ፕሬዝደንት ማሕሙድ አባስ እንዲሳተፉ እንደማትፈቅድ አስታወቀች። የዩክሬን ምክር ቤት የቀድሞ አፈ-ጉባኤ አንድሬ ፓሩቢ በልቪቭ ከተማ በጥይት ተመተው ተገደሉ።
    12 min

About የዓለም ዜና

From the publisher's feed

ዶይቼ ቬለ የዕለቱን ዋና ዋና ዜናዎች ከኢትዮጵያ እና ከመላው ዓለም በየቀኑ ያቀርባል። የኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ፖለቲካዊ እና ኤኮኖሚያዊ ጉዳዮችን ጨምሮ የመላው ዓለምን ውሎ የተመለከቱ ጠቃሚ መረጃዎች በሰባቱም የሣምንቱ ቀናት ከምሽቱ አንድ ሰዓት ከዶይቼ ቬለ ያድምጡ። የዶይቼ ቬለን ዜናዎች በአፕል ፖድካስት…