የዓለም ዜና

የዓለም ዜና

Download on the App Store

የዓለም ዜና episodes

  • የነሐሴ 12 ቀን 2017 ዓ.ም. የዓለም ዜና
    መንግሥት ከመስከረም 2018 ዓ.ም. ጀምሮ ለመንግሥት ሠራተኞች «ተጨማሪ የደመወዝ ማሻሻያ» እንደሚያደርግ አስታወቀ።
    በአማራ ክልል ደቡብ ወሎ ዞን ተንታ ወረዳ በተከሰተ የተፈጥሮ አደጋ የአራት ሰዎች ሕይወት አለፈ።
    ትናንት አመሻሹን በጋምቤላ ክልል በኑዌር ብሔረሰብ ዞን ኝነ ኛንግ በተባለ ከተማ ከባድ ዝናብ ባስከተለው ጎርፍ ከሁለት ሺህ በላይ ቤቶች መዉደማቸው ተሰማ። ሰብል እንስሳትም ላይ ጉዳት ደርሷል።
    እስራኤል ለደቡብ ሱዳን አስቸኳይ የሰብአዊ እርዳታ እንደምታቀርብ አስታወቀች።
    የአንጋፋው አርቲስት ደበበ እሸቱ የቀብር ስርዓት ነገ ነሐሴ 13 ቀን 2017 ዓ.ም በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ይፈጸማል።
    12 min
  • የነሐሴ 11 ቀን 2017 ዓ.ም የዓለም ዜና
    የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ሃይሎች በሰሜን ዳርፉር በሚገኝ አንድ የተፈናቃዮች መጠለያ ጣቢያ በፈጸሙት ጥቃት ቢያንስ 31 ስቪሎች መገደላቸውንና 13 መቁሰላቸውን የሕክምና ምንጮች አስታወቁ። እስራኤል የየመን ሁቲ ዓማፅያን ይጠቀሙበት ነበር ያለችውን የሃይል መሰረተ ልማት ማውደሟን አስታወቀች። የተለያዩ የአውሮፓ ሐገራት መሪዎች፣ የአሜሪካው ፕረዚደንት ዶናልድ ትራምፕና የዩክሬይኑ ፕረዚደንት ቮሎደሚር ዘለንስኪ በዋሽንግተን ዲሲ ነገ በሚያካሂዱት ውይይት ለመሳተፍ እንደሚጓዙ ገለጹ።
    9 min
  • የነሐሴ 10 ቀን 2017 ዓ.ም የዓለም ዜና
    የቀድሞው የኢትዮጵያ ራድዮ የዜና ፋይል ባልደረባ የነበረው በአሁኑ ሰዓት ደግሞ በአሃዱ ራድዮና በተለያዩ የዩቱብ ቻናሎች የተረክ ሚዛንና ቅዳሜ ገበያ የመሳሰሉ ፕሮግራሞችን በማዘጋጀትና በማቅረብ ላይ የነበረው ጋዜጠኛ አብዱልሰመድ መሀመድና የሪፖርተር ጋዜጣ ባልደረባ ጋዜጠኛ ዮናስ አማረ በጸጥታ ሃይሎች መታሰራቸውን ተዘገበ። እስራኤል በዮርዳኖስ ምዕራባዊ ዳርቻ በሺዎች የሚቆጠሩ ቤቶችን ለመገንባት የያዘችውን ዕቅድ እንድትሰርዝ ፈረንሳይ አሳሰሰበች። የአሜሪካው ፕረዚደንት ዶናልድ ትራምፕና የሩስያው ፕረዚደንት ቭላድሚር ፑቲን የአላስካው ውይይት ያለውጤት መጠናቀቁን ተነገረ።
    12 min
  • DW Amharic የነሐሴ 09 ቀን 2017 የዓለም ዜና
    በኢትዮጵያ ባለፈው ዓመት በ71 ልጃገረዶች፣ 29 ሴቶች እና 2 ወንዶች ልጆች ላይ ከግጭት ጋር የተያያዘ ወሲባዊ ጥቃት መፈጸማቸውን የተባበሩት መንግሥታት እንዳረጋገጠ የዋና ጸሀፊው አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ሪፖርት አሳየ። በሁለት ወራት 15,000 ገደማ ኢትዮጵያውያን ከጅቡቲ ተመለሱ። ከሶማሊያ መገንጠሏን ላወጀችው ሶማሌላንድ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ እውቅና እንዲሰጡ አሜሪካዊ ሴናተር ጥያቄ አቀረቡ። በፓኪስታን እና በሕንድ የጣለ ከባድ ዝናብ ያስከተለው ጎርፍ 260 ገደማ ሰዎች ገደለ። የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ እና የሩሲያው አቻቸው ቭላድሚር ፑቲን በአላስካ ይገናኛሉ ተብሎ እየተጠበቀ ነው።
    12 min
  • የነሐሴ 8 ቀን 2017 ዓ.ም የዓለም ዜና
    የነሐሴ 8 ቀን 2017 ዓ.ም አርዕስተ ዜና
    ስደተኞችን የጫኑ ሁለት ጀልባዎች ትናንት የኢጣልያዋ ደሴት ላምፔዱዛ አቅራቢያ ከሰጠሙ በኋላ የደረሱበት ያልታወቀ ቢያንስ አስር ስደተኞች ፍለጋ ዛሬም እንደቀጠለ ነው።
    የእስራኤል ምክትል ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሻረን ሀስክል የደቡብ ሱዳንን ጉብኝት ፍልስጤማውያንን ከጋዛ ሰርጥ ወደ ሌሎች ስፍራዎች የማስፈር እቅድን የተመለከተ አይደለም ሲሉ ሁለቱም ወገኖች ተናግረዋል።
    የአሜሪካን ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የዩክሬኑን ጦርነት የሚያስቆም ስምምነት ላይ የሚደረሰው፣ ነገ አርብ ከፑቲን ጋር በአላስካ በሚያካሂዱት ጉባኤ ሳይሆን በቀጣዩ ሁለተኛው ጉባኤ ላይ መሆኑን አስታወቁ።
    11 min
  • የነሐሴ 7 ቀን 2017 የዓለም ዜና
    -ከኦሮሚያ ክልል ከተለያዩ የወለጋ ዞኖች ተፈናቅለዉ አማራ ክልል የሰፈሩ ሰዎች ለተቃጠለ ቤትና ለማያርሱት መሬት ግብር እንዲከፍሉ መጠየቃቸዉን አስታወቁ።---የሱዳን ወታደራዊ መሪ ጄኔራል አብዱልፈታሕ አል-ቡርሐን ከዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንት የአፍሪቃ ጉዳይ ልዩ አማካሪ ማሳድ ቦዉሎስ ጋር ሥለሱዳን ሰላም በድብቅ ተነጋገሩ።-የአዉሮጳ፣ የዩክሬንና የዩናይትድ ስቴትስ መሪዎች ዛሬ በቪዲዮ ያደረጉት ጉባኤ አግባቢ እንደነበር የአዉሮጳ መሪዎች አስታወቁ።ጉባኤዉ የዩናይትድ ስቴትስና የሩሲያ መሪዎች የፊታችን አርብ በሚያደርጉት ጉባኤ የአዉሮጳና የዩክሬን ፍላጎት እንዳይዘነጋ ለማሳሰብ ያለመ ነበር
    12 min
  • የነሐሴ 6 ቀን 2017 ዓ/ም የዓለም ዜና
    DW Amharic-በዛሬው የዓለም ዜና ፤በኦሮሚያ ክልል ጉጂ ዞን ሰባቦሩ ወረዳ አንዲት ነፍሰ ጡር እናት በታጣቂዎች መገደላቸውን።የሲቪክ ማኅበረሰብ ድርጅቶች ረቂቅ ማሻሻያ አዋጅ ላይ ማስተካከያ እንዲደረግ ያቀረበው ምክረ ሀሳብ ውጤት ማምጣቱን ኢሰመኮ መግለፁን፣የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ሀይሎች በሰሜን ዳርፉር በተፈቃዮች መጠለያ ጣቢያ ባደረሱት ጥቃት 40 ሰላማዊ ሰዎች መገደላቸውን፣ የአውሮፓ ሕብረት፣ብሪታንያ እና ጃፓን በጋዛ «እየተከሰተ» ነው ባሉት ረሀብ ላይ እርምጃ እንዲወሰድ ማሳሰቡን እና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በጋዛ በአልጀዚራ ጋዜጠኞች ላይ የተፈጸመውን ግድያ ማውገዙን።ያስቃኛል።
    12 min
  • የነሐሴ 5 ቀን 2017 የዓለም ዜና
    የኢትዮጵያ አየርመንገድ ኦሮሚያ ክልል ቢሾፍቱ ከተማ አቅራቢያ ለሚገነባው ግዙፍ የአቡሴራ አየርማረፊያ ግንባታ የፋይናንስ እንቅስቃሴዎች ውክልና ሰነድ ከአፍሪካ ልማት ባንክ ጋር ዛሬ ተፈራረመ፡፡ የናይጄሪያ ጦር ከ100 በላይ «ዓመጸኛ ወንጀለኞች» ያላቸውን መግደሉን አስታወቀ። እስራኤል በጋዛ በሚገኙ የአልጀዚራ ጋዜጠኞች ላይ በፈጸመችው የአየር ጥቃት 5 የአልጀዚራና 1 የፍልስጤም የግል መገናኛ ብዙኀን ዘጋቢ መገደላቸውን የጋዛ የስቪል መከላከያ ተቋም እና አልጀዚራ አስታወቁ።
    12 min
  • DW Amharic የነሐሴ 04 ቀን 2017 የዓለም ዜና
    በሰሜን ኮርዶፋን 18 ሰዎች በሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይል ጥቃት፤ በኤል ፋሽር 63 ሰዎች በተመጣጠነ ምግብ እጦት ሕይወታቸውን አጥተዋል ተባለ። ኤርትራውያን ከፈረንሳይ ወደ ብሪታኒያ የቀዘቀዙ አትክልቶች ጭኖ በመጓዝ ላይ በነበረ ተሽከርካሪ ውስጥ ተገኙ። በናይጄሪያ ወሮበሎች 13 ጸጥታ አስከባሪዎች ገደሉ። እስራኤል ጋዛን ብትቆጣጠር "ሌላ ጥፋት" እንደሚከተል የተመ ባለሥልጣን አስጠነቀቁ። ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ሀገራቸው ጋዛን የምትቆጣጠረው ለአጭር ጊዜ እንደሚሆን ተናግረዋል። የዩክሬን እና የሩሲያን ጦርነት ለማብቃት የሚፈጸም ሥምምነት ኪየቭን ሊያካትት እንደሚገባ የአውሮፓ ኅብረት የውጪ ጉዳይ ኃላፊ አሳሰቡ።
    9 min
  • የነሐሴ 3 ቀን 2017 ዓ.ም የዓለም ዜና
    በመተከል ዞን ድባጢ ወረዳ ባጋጠመ የመኪና አደጋ የ12 ሰዎች ሕይወት ማለፉን የወረዳው አስተዳደር አስታወቀ። 67 ሰዎችን ከሃገር በሕገወጥ መንገድ ሊያስወጣ ሞክሯል ተብሎ የተጠረጠረ ግለሰብ በቁጥጥር ሥራ ማዋሉን በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የጋሞ ዞን ፖሊስ መምሪያ አስታወቀ ፡፡ በደቡብ ጃፓን የምትገኘዋ የናጋሳኪ ከተማ በዩናይትድ ስቴትስ በአቶሚክ ቦምብ የተደበደበችበት 80ኛ አመት ዛሬ ዘክራ ውላለች።
    11 min

About የዓለም ዜና

From the publisher's feed

ዶይቼ ቬለ የዕለቱን ዋና ዋና ዜናዎች ከኢትዮጵያ እና ከመላው ዓለም በየቀኑ ያቀርባል። የኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ፖለቲካዊ እና ኤኮኖሚያዊ ጉዳዮችን ጨምሮ የመላው ዓለምን ውሎ የተመለከቱ ጠቃሚ መረጃዎች በሰባቱም የሣምንቱ ቀናት ከምሽቱ አንድ ሰዓት ከዶይቼ ቬለ ያድምጡ። የዶይቼ ቬለን ዜናዎች በአፕል ፖድካስት…