የዓለም ዜና

የዓለም ዜና

Download on the App Store

የዓለም ዜና episodes

  • የዓለም ዜና፤ ሐምሌ 22 ቀን 2017 ማክሰኞ
    አርስተ ዜና፤--የጀርመኑ መራሔ መንግስት ፍሬድሪክ መርስ የጀርመን መንግስት ከዮርዳኖስ ጋር በመተባበር ለጋዛ የሰብአዊ ርዳታ በአየር ላይ ለማድረስ በዝግጅት ላይ መሆኑን ተናገሩ። በፍልስጤም ግዛት ውስጥ የሚታየዉ ከፍተኛ የምግብ እና የውኃ እጥረት ለአስከፊ ረሃብ እንዳይዳርግ ሲሉ የተባበሩት መንግስታት ድርጅቶች አስጠንቅቀዋል።--በአገሪቱ የሚገኙ ሁሉም የፖለቲካ ኃይሎችና ባለድርሻ አካላት አገራዊ መግባባትንና ዘላቂ መፍትሔዎችን እንዲያመጡ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ጠየቀ። ታይላንድ እና ካምቦጂያ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ የተኩስ አቁም ስምምነት ለማድረግ ስምምነት ላይ ከደረሱ በኋላ ስምምነቱ ተጥሶ ውጊያ ማገርሸቱ ተሰማ።
    12 min
  • የሐምሌ 20 ቀን 2017 ዓ/ም የዓለም ዜና
    DW Amharic-የዛሬው የዓለም ዜና ጥንቅር፤ የአልሸባብ ታጣቂዎች ማሃስ የተባለች ቁልፍ ከተማ መቆጣጠራቸውን፤በጋዛ እየተባባሰ ያለውን ሰብአዊ ቀውስ ለማቃለል የመጀመሪያወቹ የእርዳታ መኪኖች ፍልስጤም ግዛት መድረሳቸውን፤ በግሪክ ከባድ የሙቀት ያስከተለው የሰደድ እሳት አደጋው እየጨመረ መምጣቱን፤ ኢራን ሁለት በስደት ላይ ያለ የታጣቂ ቡድን አባላትን በሞት መቅጣቷን የሚያስቃኙ ዘገባዎችን አካቷል።
    9 min
  • የሐምሌ 19 ቀን 2017 ዓ/ም የዓለም ዜና
    DW amharic-የዛሬው የዓለም ዜና ጥንቅር፤ በአማራ ክልል በ2016/17 ዓም በግብርናው ዘርፍ ከፍተኛ ምርት ተገኝቷል መባሉ-የጋዛ ሰብዓዊ ቀውስ እንዲያቆም ሶስት የአውሮፓ ሀገራት መጠየቃቸው- ትራምፕ አውሮፓ በስደት ላይ ጠንካራ ርምጃ እንድትወስድ ማሳሰባቸው-በዩክሬን እውነተኛ የሰላም ድርድር ማድረግ የምዕራቡ ዓለም 'እውነተኛ አጀንዳ' ሆኖ አያውቅም ስትል ሩሲያ መግለጿን-ቻይና በሰው ሰራሽ አስተውሎት ደንብ ላይ ዓለም አቀፍ 'ስምምነት' እንዲደረግ መጠየቋ-«ኩራት»ወይም በእንግሊዝኛ አጠራሩ «ፕራይድ» እየተባለ የሚጠራው የግብረ ሰዶማውያን ዓመታዊ ፌስቲባል ዛሬ በበርሊን መጀመሩን የሚያስቃኙ ዘገባዎችን አካቷል።
    13 min
  • የሐምሌ 18 ቀን 2017 ዓ.ም. የዓለም ዜና
    50 የሚሆኑ የፓለቲካ ፓርቲዎች መንግሥት በነፍጥ ከሚፋለሙ ኃይላት ጋር ወደ ድርድር እንዲገባ ጠየቁ።
    ትናንት ሌሊት ጋምቤላ ከተማ የጣለው ከባድ ዝናብ በንብረት ላይ ጉዳት ማድረሱን የከተማዋ ነዋሪዎች አመለከቱ።
    ከሀገራቸው ጦርነት ሸሽተው ተሰድደው የነበሩ ሱዳናውያን ወደ ሀገራቸው መመለስ ቢጀምሩም ውጊያው አለማባራቱን የተመድ አመለከተ።
    ፈረንሳይ ለፍልስጤም ግዛት እውቅና ልትሰጥ መዘጋጀቷ ከእስራኤል እና የእስራኤል ደጋፊዎች ከፍተኛ ቁጣና ትችት አስከተለ።
    10 min
  • የሐምሌ 17 ቀን 2017 ዓ.ም. የዓለም ዜና
    የሐምሌ 17 ቀን 2017 ዓ.ም አርዕስተ ዜና
    ትናንት ከሰዓት በኋላ አዲስ አበባ ውስጥ የጣለው ከባድ ዝናብ ያስከተለዉ ጎርፍ በንብረትና በግንባታ ሥራ ላይ ጉዳት ማድረሱን ነዋሪዎችና የዓይን ምሥክሮች አስታወቁ። የአዲስ አበባ አስተዳደር መግለጫ ሥለደረሰዉ ጉዳት ምንም ያለዉ ነገር የለም።
    የኬንያ የሥርዓታዊ ጉዳይ ባለሥልጣን በቅርብ ጊዜው የኬንያው ተቃውሞ 65 ሰዎች መገደላቸውን አስታወቀ። መሥሪያ ቤቱ ፖሊስ በተቃውሞ ሰልፎች ከመጠን ያለፈ ኃይል ተጠቅሟል ብሏል።
    ሀማስ የመጨረሻ ያለውን የተኩስ አቁም ምክረ-ሀሳብ ዛሬ በአደራዳሪዎች በኩል ለእስራኤል መላኩን አረጋገጠ።
    11 min
  • የሐምሌ 15 ቀን፣ 2017 ዓ.ም የዓለም ዜና
    አአ፥ የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ከኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር ጋር ዛሬ በስልክ መነጋገራቸውን ተገለጠ፤ ማይጨው፣ ጀነራል ታደሰ ትግራይ ክልል ደቡባዊ ዞን ዛሬ ሹም ሽር አደረጉ፤ አ.አ፥ የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት ምላሽ ለዶናልድ ትራምፕ፤ ቤሮ፥ ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያና ጋምቤላ ክልል አዋሳኝ ማዕድን በማውጣት በተቀሰቀሰ ጠብ ሰዎች ተገደሉ፤ ጋሞ፥ የቀድሞው የኢትዮጵያ ብሔዊ እግር ኳስ ቡድን ተጫዋችን የገደሉ «16ና 15 ዓመት ተፈረደባቸው፤ ናይሮቢ፥ በተከለከለ ንጥረ ነገር የተጠረጠሩ የኬንያ አትሌቶች ላይ ምርመራ ተከፈተ
    13 min
  • የሐምሌ 14 ቀን 2017 ዓ.ም. የዓለም ዜና
    የሐምሌ 14 ቀን 2017 ዓ.ም. አርዕስተ ዜና
    በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ከ40 ሺህ በላይ የመንግሥት ሠራተኞች ያለመደብ መቀጠራቸውን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ በአርባ ምንጭ ከተማ በተካሄደው የክልሉ 6ኛ ዙር 5ኛ መደበኛ ጉባኤ ላይ ተናገሩ።
    የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎዶሚር ዜሌንስኪ፣ በኬቭ እና በሞስኮ መካከል የሚካሄደው ጦርነት እንዲቆም ባቀረቡት 3ተኛ ዙር የድርድር ሀሳብ እንደምትስማማ ክሬምሊን ዛሬ አረጋገጠች።
    የእስራኤል ጦር ወደ ጋዛው ዴር አልባላህ ዛሬ ታንኮቹን አሰማራ። ጦሩ ታንኮቹን ያሰማራባት ዴር አልባላህ የተቀሩት የእስራኤል ታጋቾች ይገኙበታል ብሎ በሚያምነበት የሚያምንበት አካባቢ ነው።
    12 min
  • የሐምሌ 13 ቀን 2017 የዓለም ዜና
    የኤርትራው ፕረዚደንት መግለጫ ፤ የግብፅ ፖሊስ የሐማስ ታጣቂ ቡድን አባላትመግደሉን፤በደቡብ ሶሪያ በተቀሰቀሰው ጎሳና ሐይማኖትን መሰረት ባደረገ ግጭት አንድ ሳምንት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ የሞቱ ሰዎች ቁጥር ከ1,000 በለጠ።
    9 min

About የዓለም ዜና

From the publisher's feed

ዶይቼ ቬለ የዕለቱን ዋና ዋና ዜናዎች ከኢትዮጵያ እና ከመላው ዓለም በየቀኑ ያቀርባል። የኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ፖለቲካዊ እና ኤኮኖሚያዊ ጉዳዮችን ጨምሮ የመላው ዓለምን ውሎ የተመለከቱ ጠቃሚ መረጃዎች በሰባቱም የሣምንቱ ቀናት ከምሽቱ አንድ ሰዓት ከዶይቼ ቬለ ያድምጡ። የዶይቼ ቬለን ዜናዎች በአፕል ፖድካስት…