የዓለም ዜና

የዓለም ዜና

Download on the App Store

የዓለም ዜና episodes

  • የረቡዕ ሐምሌ 2 ቀን፣ 2017 ዓ.ም የዓለም ዜና
    አርዕስተ ዜና፦
    ኢትዮጵያ ዉስጥ በአማራ ክልል የቀጠለው ግጭት የክልሉን የጤና አገልግሎት በብርቱ ማወኩን ድንበር የለሽ ሐኪሞች (MSF-በፈረንሳይኛ ምሕጻሩ) የተሰኘዉ ግብረ-ሠናይ ድርጅት ዐሳወቀ ።
    የኬንያ ፕሬዚደንት ዊሊያም ሩቶ፦ «ኢ-ሕገመንግሥታዊ በሆነ መልኩ» መንግሥትን «ለመገልበጥ» የሚያሴሩ ያሏቸው ሰልፈኞችን እግር ፖሊስ በጥይት እንዲመታ ዛሬ ትእዛዝ አስተላለፉ ።
    ሩስያ ምሽቱን በ728 ድሮኖች እና 13 ሚሳይሎች ምዕራብ ዩክሬንን ደበደበች ። ይህ የሩስያ ጥቃት በሦስት ዓመታቱ የዩክሬን ጦርነት ከፍተኛው ነው ተብሏል ። የዩክሬን መከላከያ 711 ድሮኖችን እና ሰባት ሚሳይሎችን ዐየር ላይ ማክሸፉን ገልጧል ።
    8 min
  • የረቡዕ ሐምሌ 2 ቀን፣ 2017 ዓ.ም የዓለም ዜና
    አርዕስተ ዜና፦
    ኢትዮጵያ ዉስጥ በአማራ ክልል የቀጠለው ግጭት የክልሉን የጤና አገልግሎት በብርቱ ማወኩን ድንበር የለሽ ሐኪሞች (MSF-በፈረንሳይኛ ምሕጻሩ) የተሰኘዉ ግብረ-ሠናይ ድርጅት ዐሳወቀ ።
    የኬንያ ፕሬዚደንት ዊሊያም ሩቶ፦ «ኢ-ሕገመንግሥታዊ በሆነ መልኩ» መንግሥትን «ለመገልበጥ» የሚያሴሩ ያሏቸው ሰልፈኞችን እግር ፖሊስ በጥይት እንዲመታ ዛሬ ትእዛዝ አስተላለፉ ።
    ሩስያ ምሽቱን በ728 ድሮኖች እና 13 ሚሳይሎች ምዕራብ ዩክሬንን ደበደበች ። ይህ የሩስያ ጥቃት በሦስት ዓመታቱ የዩክሬን ጦርነት ከፍተኛው ነው ተብሏል ። የዩክሬን መከላከያ 711 ድሮኖችን እና ሰባት ሚሳይሎችን ዐየር ላይ ማክሸፉን ገልጧል ።
    9 min
  • የሐምሌ 1 ቀን 2017 የዓለም ዜና
    -በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የዎላይታ ዞን ምክር ቤት የዞኑን ከፍተኛ ባለሥልጣናት ሽሮ አዳዲስ ሾሟል።በዞኑ የሚንቀሳቀሱ ተቃዋሚ ፖለቲከኞች ሹም ሽሩን የሕዝቡን ጥያቄ ለመሸፈን ያለመ በማለት ተችተዉታል።-ሰሜናዊ ጋዛ ዉስጥ የሸመቁ የፍልስጤም ደፈጣ ተዋጊዎች አምስት የእስራኤል ወታደሮችን ገደሉ፤ ሌሎች ሁለት አቆሰሉ።የእስራኤል ጦር በበኩሉ ሊባኖስ ዉስጥ አንድ የሐማስ ከፍተኛ ባለሥልጣን መግደሉን አስታዉቋል።-ኢራን የኑኩሌር መርሐ ግብሯን በተመለከተ ከዩናይትድ ስቴትስ ጋር የጀመረችዉን ድርድር ለመቀጠል ጥያቄ አለማቅረቧን አስታወቀች።የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ትናንት ኢራን ድርድሩ እንዲቀጥል ጠይቃለች ብለዉ ነበር
    10 min
  • የሰኔ 30 ቀን 2017 ዓ.ም. የዓለም ዜና
    የሰኔ 30 ቀን 2017 ዓ.ም. አርዕስተ ዜና
    የኬንያ ፖሊስ ዛሬ ከፀረ-መንግስት ተቃዋሚ ሰልፈኞች ጋር ተጋጨ። ሰልፈኞቹ እሳት አቃጥለዋል ፖሊስ ላይም ድንጋይ ወርውረዋል። ፖሊስም በሰልፈኞቹ ላይ አስለቃሽ ጢስ ተኩሷል።
    እስራኤልና ሀማስ የተኩስ አቁም ላይ ለመድረስ ዶሀ ኳታር ውስጥ ቀጥተኛ ያልሆነ ድርድር ቢጀምሩም በቅድመ ሁኔታዎችዎቻቸው ሰበብ በተደጋጋሚ እየተቋረጠ ነው።
    የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የብሪክስ ቡድን አባል ለመሆን የሚፈልጉ ሀገራትን በታሪፍ እንደሚቀጡ አሳወቁ ። የብሪክስ አባል ሀገራት የታሪፍ ጭማሪው ለዓለም አቀፉ ንግድ አደጋ ነው ሲሉ አስጠንቅቀዋል።
    11 min
  • የዓለም ዜና፤ ሰኔ 27 ቀን 2017 ዓ.ም አርብ
    አርስተ ዜና፤
    --ፕሬዚዳንት ትራምፕ ከሩስያዉ ፕሬዚዳንት ጋር በስልክ ከተነጋገሩ በኋላ "ፑቲን ከዩክሪን ጋር የጀመረዉን ጦርነት የማቆም ፍላጎት የለዉም አሉ"። ሩሲያ 550 ድሮን እና ሚሳኤሎችን ተጠቅማ ዩክሬይን ላይ ከፍተኛ የተባለ ድብደባ ፈጽማለች።
    --የኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዐብይ አሕመድ በህዳሴ ግድብ ምረቃ ላይ የሱዳን፣ የግብፅና የሌሎች የዓባይ ተፋሰስ ሐገራት መሪዎች እንዲገኙ ያቀረቡትን ግብዣ ግብፅ ዉድቅ አደረገችዉ።
    --የፍልስጤሙ ሽምቅ ተዋጊ ቡድን ሃማስ ከእስራኤል ጋር ጋዛ ላይ የሚያካሂደዉን ጦርነት በተመለከተ አንድ የስምምነት ሐሳብ ላይ ለመድረስ ከሌሎች የፍልስጤም ቡድኖች ጋር ውይይት እያደረገ መሆኑን አስታወቀ።
    11 min
  • የሰኔ 26 ቀን 2017 ዓ.ም. የዓለም ዜና
    የሰኔ 26 ቀን 2017 ዓ.ም. አርዕስተ ዜና
    የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ስራ ማለቁንና የፊታችን መስከረም በይፋ ሊመረቅ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ዛሬ ተናግረዋል።
    የእስራኤል ኃይሎች ዛሬ በጋዛ ባካሄዱት ድብደባ ቢያንስ 69 ሰዎች ተገድለዋል ሲል የጋዛ የሲቪል መከላከያ ኤጀንሲ አስታወቀ። እንደ ኤጀንሲው 5ቱ በአንድ ትምሕርት ቤት ውስጥ ተጠልለው የነበሩ የጋዛው ጦርነት ተፈናቃዮች ናቸው። ከሞቱት ውስጥ እርዳታ በመጠበቅ ላይ የነበሩ 38 ሰዎችም ይገኙበታል።
    የሩስያ ባህር ኃይል ምክትል ሃላፊ ሜጀር ጀነራል ሚኻኤል ጉዳኮቭ ከዩክሬን ጋር በተካሄደ ውጊያ ረቡዕ ተገደሉ።
    10 min
  • የሰኔ 24 ቀን 2017 ዓ.ም. የዓለም ዜና
    በያዝነው ዓመት የዩናይትድ ስቴትስ እርዳታ መቋረጥ ከሀገራቸው የሚሰደዱ ሰዎች ቁጥር በእጥፍ እንዲጨምር ያደርጋል ሲል አንድ የረድኤት ድርጅት አስጠነቀቀ።
    ጋዛ ውስጥ እርዳታ ለማከፋፈል የተዘረጋው በዩናይትድ ስቴትስ እና እስራኤል የሚደገፈው ተቋም ሲቪሎችን ለሞትና ጉዳት እያጋለጠነው በማለት 171 የረድኤት ድርጅቶች እንዲቋረጥ ጠየቁ።
    በጀርመኗ ሜልሪች ሽታት ከተማ አንድ የኤሌክትሪክ አቅራቢ ኩባንያ ሠራተኛ ባልደረቦቹ ላይ በባደረሰው ጥቃት የአንድ ሰው ሕይወት ሲያልፍ ሌሎች ሁለቱ ላይ ከባድ ጉዳት ደረሰ።
    ሩሲያ ከዩክሬን ጋር የገባችበትን ጦርነት ለማስቆም የሚደረገውን የሰላም ውይይት በማጓተት የቀረበባትን ወቀሳ ውድቅ አደረገች።
    10 min

About የዓለም ዜና

From the publisher's feed

ዶይቼ ቬለ የዕለቱን ዋና ዋና ዜናዎች ከኢትዮጵያ እና ከመላው ዓለም በየቀኑ ያቀርባል። የኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ፖለቲካዊ እና ኤኮኖሚያዊ ጉዳዮችን ጨምሮ የመላው ዓለምን ውሎ የተመለከቱ ጠቃሚ መረጃዎች በሰባቱም የሣምንቱ ቀናት ከምሽቱ አንድ ሰዓት ከዶይቼ ቬለ ያድምጡ። የዶይቼ ቬለን ዜናዎች በአፕል ፖድካስት…