የዓለም ዜና

የዓለም ዜና

Download on the App Store

የዓለም ዜና episodes

  • የዓለም ዜና፤ ሰኔ 23 ቀን 2017 ዓ.ም ሰኞ
    አርስተ ዜና፤
    --የጀርመኑ ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ዛሬ ዩክሪን መዲና ኪይቭን ሲጎበኙ ሃገራቸዉ ጀርመን ከዩክሬን ጎን በመቆም ዩክሬን እራሷን መከላከል እንድትችል በዘመናዊ የአየር መከላከያን ጨምሮ የሰብአዊ እና ኢኮኖሚያዊ ዕርዳታ እንደምታደር ገለፁ። --እስራኤል በሰሜናዊ ጋዛ እጅግ አስከፊ የቦንብ ድብደባ መፈፀሟ ተገለፀ ። የተኩስ አቁም ይደረጋል ተብሎ እየተጠበቀ ባለበት በአሁኑ ወቅት፤ እስራኤል ፍልስጤማዉያን ሰሜናዊ ጋዛን ለቀዉ እንዲወጡ ጠይቃለች። --በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን ግዳን ወረዳ ትናንት በደረሰ ጥቃት ህጻናትን ጨምሮ የሰዎች ህይወት ጠፋ።--በተለያዩ የአዉሮጳ ክፍሎች ከፍተኛ የአየር ሙቀት ተከሰተ።
    14 min
  • DW Amharic የሰኔ 22 ቀን 2017 የዓለም ዜና
    በአማራ ክልል ከተሞች በሺሕዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች የተሳተፉባቸው መንግሥትን የሚደግፉ ሰልፎች ተካሔዱ። የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ “ቁልፍ የዴሞክራሲ ተቋማት ገለልተኛ አለመሆን” እና “በተቃዋሚ ፓርቲዎች ላይ የሚደርሰውን ጫና” አወገዘ። የዩጋንዳ ፕሬዝደንት ዮዌሪ ሙሴቬኒ በሚቀጥለው ዓመት በሚካሔደው ምርጫ የመሳተፍ ፍላጎት እንዳላቸው አስታወቁ። እስራኤል 12 ቀናት የዘለቀውን ውጊያ የገታውን የተኩስ አቁም ታከብራለች የሚል ዕምነት እንደሌላት ኢራን ሥጋቷን ገለጸች። የኢየሩሳሌም ፍርድ ቤት በእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታንያሁ ላይ የቀረበውን የሙስና ክስ ለመመልከት ይዞት የነበረውን ቀጠሮ ሰረዘ።
    9 min
  • DW Amharic የሰኔ 21 ቀን 2017 የዓለም ዜና
    በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኮሬ ዞን ታጣቂዎች ሁለት አርሶ አደሮችን በጥይት ደብድበው መግደላቸውን የዞኑ ፖሊስ መምሪያ አስታወቀ። ኢትዮጵያን ጨምሮ በ39 ኢኮኖሚዎች ግጭት እና አለመረጋጋት ከየትኛውም የዓለም ክፍል በባሰ ሁኔታ ድሕነት እና አስከፊ ረሐብ ማባባሱን ዓለም ባንክ ይፋ አደረገ። አዲስ የተሾሙት የሱዳን መከላከያ ሚኒስትር እና የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር ቃለ መሐላ ፈጸሙ። የኑክሌር ሳይንቲስቶች እና ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖችን ጨምሮ ኢራን ከእስራኤል ባደረገችው ውጊያ የተገደሉ 60 ሰዎች ብሔራዊ ሥርዓተ ቀብር ተፈጸመ። በጋዛ ሠርጥ በተፈጸሙ የእስራኤል ጥቃቶች ቢያንስ 81 ተገደሉ
    12 min
  • የሰኔ 20 ቀን 2017 ዓ.ም.የዓለም ዜና
    የሰኔ 20 ቀን 2017 ዓ.ም. አርዕስተ ዜና
    ከመላ ኢትዮጵያ፣ በሕገወጥ መንገድ በመተማ ዮሐንስ በኩል፣ ወደ ሱዳን የሚሰደዱ ወጣቶችና ህፃናት ቁጥር በእጅጉ እየጨመረ መሆኑን የምዕራብ ጎንደር ዞን አስታወቀ። በዞኑ የሴቶች፣ ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ መምሪያ እንዳለውበተለይ ከትግራይ ክልል የሚሰደዱት ቁጥር ከፈተኛ ነው።
    ምያንማር ውስጥ አሁንም በአጋቾች እንደተያዙ ነው የተባሉ 42 ኢትዮጵያውን እጣ ፈንታ አለመታወቁን በምያንማር የተጎጂ ወጣቶች ቤተሰቦች አስተባባሪ ለዶቼቬለ ተናገሩ።
    ዋሽንግተን ያሸማገለቻቸው የኮንጎ ዴሞክራሲያዊት ሪፐብሊክና ሩዋንዳ ዛሬ ዋሽንግተን ውስጥ የሰላም ስምምነት ይፈራረማሉ ተብሎ እየተጠበቀ ነው።
    11 min
  • የሰኔ 19 ቀን 2017 የዓለም ዜና
    -የኢትዮጵያ መንግስት የሥራ ሁኔታ እንዲሻሻልላቸዉ የጠየቁ የሕክምና ባለሙያዎችን ማሠርና ማዋካቡን እንዲያቆም ሑዩማን ራይትስ ዋች ጠየቀ።ዓለም አቀፉ የሠብአዊ መብት ተሟጋች እንድርጅት እንደሚለዉ የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት ለጥያቄዉ ተገቢ መልስ ከመስጠት ይልቅ ጠያቂዎቹን ያስራሉ፣ያዋክባሉ፣ ማሕበራቸዉን ያግዳሉም።---የኬንያ ፀጥታ አስከባሪዎች ትናንት አደባባይ በወጡ ተቃዉሞ ሰልፈኞች ላይ በወሰዱት የኃይል ርምጃ የሞቱት ሰዎች ቁጥር 16 ደረሰ።ከ400 በላይ ቆስለዋል።--የእስራኤል-የዩናይትድ ስቴትስ ባለሥልጣናትና የኢራን ጠላቶቻቸዉ የገጠሙት የቃላት ዉዝግብ እንቀጠለ ነዉ።ሶሥቱም በየፊናቸዉ ድል እድርገናል ይላሉ።
    11 min
  • የረቡዕ ሰኔ 18 ቀን፣ 2017 ዓ.ም የዓለም ዜና
    ድሬዳዋ፥ በኢትዮጵያ ምሥራቃዊ አካባቢዎች ብርቱ ዝናብ ይጠበቃል፤ ጄኔቫ፦ ኤርትራ ተመድ የመብት ጥሰት ጥርጣሬ ላይ የሚያደርገው ምርመራ እንዲቋረጥ መሻቷ ተገለጠ፤ ኖዋክቾት፥ ዩክሬን ሩስያን ለመገዳደር አፍሪቃ ውስጥ ተጨማሪ ኤምባሲ መክፈቷ ተገለጠ፤ ናይሮቢ፥ በኬንያ የአደባባይ ተቃውሞ ቢያንስ ሁለት ተገደሉ፤ ዘ ሔግ፥ የኢራን እና እሥራኤል የተኩስ አቁም ስምምነት በቀላሉ የመጣስ ሥጋት ያጠላበት ነው፤ ዘ ሔግ፦ ዩናይትድ ስቴትስ ለኔቶ መከላከያ ቄቁርጠኛ አቋም አላት ተባለ
    9 min
  • የዓለም ዜና፤ ሰኔ 17 ቀን፣ 2017 ማክሰኞ
    --ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ እስራኤልና ኢራን የተኩስ አቁም ስምምነቱን ጥሰዋል ሲሉ ወቀሱ። በሌላ በኩል ኢራን የኒኩሊየር ተቋሞችዋን ለማደስ ቅድመ ዝግጅት ላይ መሆንዋን አስታዉቃለች።--የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃል ኪዳን ድርጅት የ(ኔቶ) መሪዎች ኔዘርላንድስ ላይ ታሪካዊ የተባለዉን የሁለት ቀናት ጉባኤ ጀመሩ። 32 የዓለም ሃገራት አባላት የሆኑበት የዓለም ትልቁ የደህንነት ድርጅት ለደህንነት ተጨማሪ ወጭ ለማዉጣት ይስማማሉ አልያም ያለስምምነት ይበተናሉ ተብሎ ይጠበቃል።--በዝቋላ ደብረ ከዋክብት አቡኔ ገብረመንፈስ ቅዱስ ገዳም በሚኖሩ መነኮሳት ላይ በተፈጸመ ጥቃት የአንድ መናኝ ህይወት ጠፋ፤ አንድ አባት ጉዳት ደርሰባቸዉ።
    14 min
  • የሰኔ 16 ቀን 2017 ዓ.ም. የዓለም ዜና
    ኢራን ትናንት እሑድ በአሜሪካ ለደረሰባት ጥቃት አጸፋዋ የከፋ ሊሆን እንደሚችል ዛተች። አሜሪካ ኢራን ላይ ያደረሰችውን ጥቃት ተከትሎ የኢራን እስራኤል ፍጥጫ በዲፕሎማሲ መፍትሄ እንዲያገኝ የተለያዩ ሃገራት ጥሪ አቀረቡ። ቴህራን በበኩሏ በዩናይትድ ስቴትስ የተፈጸመባት ጥቃት የዲፕሎማሲ እና ውይይት መርሆዎችን መካድ ነው ብላለች።
    የሶማሊያ ጦር ኃይላት በትናንትናው ዕለት በሀገሪቱ ማዕከላዊ አካባቢዎች ቢያንስ 20 የሚሆኑ የአሸባብ ተዋጊዎችን ገደሉ። በርካቶችንም አቆሰሉ።
    የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይል መሪ ሌተናል ጀነራል መሀመድ ሀምዳን ዳጋሎ ቡድናቸው ከግብጽ ጋር ያለውን ያለመግባባት በውይይት ለመፍታት እንደሚፈልግ አስታወቁ።
    12 min
  • የሰኔ 14 ቀን 2017 ዓ.ም የዓለም ዜና
    በናይጄሪያ አንዲት ሴት አጥፍቶ ጠፊ በፈጸመችው የቦምብ ጥቃት 20 የጸረ እስላማዊ ጀሃድ ታጣቂዎች መገደላቸውን ተሰማ።እስራኤል ኢስፋሃን የሚገኘውን የኢራን የኒኩሌር ማብለያ ተቋም ላይ ጥቃት መፈጸሟን የኢራን መገናኛ ብዙሃን ዘገቡ። እስራኤል በተቋሙ ጥቃት ብትፈፅምም ምንም አይነት ሰዎችን ሊጎዳ የሚችል ኬሚካል አለመፍሰሱን አክለዋል። የሩስያው ፕረዚደንት ቭላድሚር ፑቲን ኢራን የኒኩሌር የጦር መሳሪያ ስለማምረቷ ምንም አይነት ተጨባጭ ማስረጃ እንደሌለ ለእስራኤል ደጋግመን ነግረናታል አሉ።
    11 min

About የዓለም ዜና

From the publisher's feed

ዶይቼ ቬለ የዕለቱን ዋና ዋና ዜናዎች ከኢትዮጵያ እና ከመላው ዓለም በየቀኑ ያቀርባል። የኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ፖለቲካዊ እና ኤኮኖሚያዊ ጉዳዮችን ጨምሮ የመላው ዓለምን ውሎ የተመለከቱ ጠቃሚ መረጃዎች በሰባቱም የሣምንቱ ቀናት ከምሽቱ አንድ ሰዓት ከዶይቼ ቬለ ያድምጡ። የዶይቼ ቬለን ዜናዎች በአፕል ፖድካስት…