የዓለም ዜና

የዓለም ዜና

Download on the App Store

የዓለም ዜና episodes

  • የሰኔ 3 ቀን 2017 ዓ.ም የዓለም ዜና
    ሀይማኖትን መሠረት ያደረገ ጥቃት በሃድያ ዞን ፤ከፍተኛ የረሃብ አደጋ በሱዳን፤የእስራኤል ወታደሮች ፈጸሙት በተባለ የተኩስ እሩምታ 17 ፍልስጤማውያን መገደላቸውን፤በኦስትሪያ አንድ ታጣቂ በተማሪዎች ላይ በከፈተው ተኩስ 9 ተማሪዎች መገደላቸውን
    11 min
  • የሰኔ 2 ቀን፣ 2017 ዓ.ም የዓለም ዜና
    መቐለ፥ ሕወሓት የፌዴራል መንግሥቱን በበርካታ ጉዳዮች ከሰሰ፤ ባሕርዳር፥ የማዳበሪያ ዋጋ ማሻቀብ በዋና ዋና ሰብሎች ላይ ተፅዕኖ ሊያሳድር ይችላል፤ ዋሽንግተን፥ 12 አገራት ላይ የተጣለው የጉዞ እገዳ መተግበር ጀመረ፤ የሎስ አንጀለስ አመጽ የተቀላቀለበት የተቃውሞ ሰልፍ፤ ሩስያ ሌሊቱን ዩክሬንን በመጠነ ሰፊ የድሮን ጥቃት ደበደበች፤ ጋዛ፥ የእስራኤል ጦር የርዳታ ቁሳቁሶችን በጋዛ ሰርጥ ላሉ ነዋሪዎች የጫነች የተባለች መርከብን አስቆመ
    11 min
  • DW Amharic የግንቦት 30 ቀን 2017 የዓለም ዜና
    የኢትዮጵያ ፖለቲከኞች እና አክቲቪስቶች “ጦርነት ይቁም፣ ግፋዊ አገዛዝ ይብቃ፣ ሰላም ይምጣ” የሚል ጥሪ ያቀረቡበትን ትዕይንተ-ሕዝብ በበይነ-መረብ አካሔዱ። በኦሮሚያ እና ቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልሎች አዋሳኝ አካባቢዎች “በፖለቲካዊ እና የብሔር ልዩነት ምክንያት የተቀሰቀሰ የትጥቅ ግጭት እየተባባሰ” መሔዱን የአውሮፓ የሲቪል ጥበቃ እና የሰብአዊ ርዳታ ሥራ ክፍል አስታወቀ። በደቡብ ኦሞ ዞን ዳሰነች ወረዳ በጎርፍ 1,753 አባወራዎች ከቀያቸው ተፈናቀሉ። የእስራኤል ጦር በሰሜናዊ ጋዛ የሚገኙ ነዋሪዎች መንደራቸውን ለቀው እንዲወጡ ትዕዛዝ ሰጠ። በዩክሬን ኻርካይቭ ላይ ሩሲያ በድሮኖች እና ሚሳይሎች በፈጸመችው ጥቃት ሦስት ሰዎች ተገደሉ።
    10 min
  • የግንቦት 29 ቀን 2017 የዓለም ዜና
    አርዕሥተ ዜና
    -የኢድ አል አድሐ በዓል ዛሬ በአብዛኛዉ ዓለም በሙሊሞች ዘንድ መከበር ጀመረ።ከሱዳን እስከ ምያንማር፣ ከጋዛ እስከ ካሽሚር የሚደረጉ ጦርነት፣ ግጭትና የመብት ረገጣዎች የመንፈሳዊዉን በዓል ድባብ አጥልተዉበታል።የሐጂ ሥርዓት ግን እስከ ዛሬ ብዙ መጨናነቅና አደጋ አልታየበትም ተብሏል።
    -የሩሲያ ጦር በዩክሬን ላይ መጠነ ሰፊ ጥቃት ከፈተ።የዩክሬኑ ፕሬዝደንት ቮልድሚየር ዘለንስኪ እንዳሉት አብዛኞቹ የየኩሬን ከተሞች «አረመኒያዊ» ባሉት ጥቃት ክፉኛ ተደብድበዋል።-ዩናይትድ ስቴትስ በዓለም አቀፉ የጦር ወንጀለኞች መዳኛ ፍርድ ቤት (ICC) ዳኞች ላይ ማዕቀብ መጣልዋን ፍርድ ቤቱ አወገዘ። ድርጅቶች አጥብቀዉ ተቃወሙት።
    13 min
  • የግንቦት 28 ቀን 2017 ዓ. ም. የዓለም ዜና
    *ኢትዮጵያ ከኤርትራ ጋር "የቃላት ጦርነት ውስጥ አልገባችም"
    *የሚኒስትሮች ምክር ቤት ለ 2018 ዓ ም ሁለት ትሪሊዮን የሚጠጋ በጀት አጸደቀ
    *ትራምፕ የኤርትራን ጨምሮ የ12 ሀገራት ዜጎች ዩናይትድ ስቴትስ እንዳይገቡ አገዱ
    *ከ1.5 ሚሊዮን በላይ የውጭ ዜጎች በዘንድሮ ሀጅ ተካፍለዋል
    *የዩናይትድ ስቴትስ ውሳኔ በፀጥታው ምክር ቤት ውጣ አጭሯል
    *የጀርመን መራኄ-መንግሥት ሜርዝ ለመጀመሪያ ጊዜ ከፕሬዝዳንት ትራምፕ ጋር ተገናኙ
    9 min
  • የግንቦት 27 ቀን 2017 ዓ.ም. የዓለም ዜና
    የግንቦት 27 ቀን 2017 ዓ.ም. አርዕስተ ዜና
    አንድ የዕቃ ማጓጓዣ አውሮፕላን ዛሬ በሱዳንዋ ምዕራብ ዳርፉር ግዛት ውስጥ በሚገኝ አውሮፕላን ማረፊያ እንደደረሰ በቦምብ መመታቱን የዓይን ምስክሮች ተናገሩ።
    ጋዛ ሰርጥ ውስጥ እርዳታ የሚያከፋፈልባቸው ማዕከላት ለጊዜው መዘጋታቸውን በዩናይትድ ስቴትስና በእስራኤል የሚደገፈው የጋዛ ሰብዓዊ ድርጅት የተባለው ቡድን አስታወቀ።
    የአውሮፓ ኅብረት ዋነኛ የንግድ ተደራዳሪ ማሮስ ስፌሶቪክ ዩናይትድ ስቴትስ ዛሬ በብረታ ብረቶች ላይ በእጥፍ የታሪፍ ጭማሪ ማድረጓ ድርድሩን የሚያግዝ እንደማይሆን ተናግረዋል።
    11 min
  • የግንቦት 26 ቀን 2017 የዓለም ዜና
    የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ ፖለቲከኞች ክልሉን ለዳግም ጦርነት ከሚዳርግ እንቅስቃሴ እንዲታቀቡ የሚደረገዉ ጥሪና ማሳሰቢያ እንደቀጠለ ነዉ።የኢትዮጵያና የኤርትራ መንግሥታት የገጠሙት የፕሮፓጋንዳ ዘመቻና የሚያደርጉት ዝግጅት ዳግም ጦርነት ሊገጥሙ ነዉ የሚለዉን ሥጋት እያናረዉ ነዉ።---ለምዕራባዊ ሱዳን ግዛት ለዳፋር ሕዝብ የሚከፋፈል ርዳታ የጫኑ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ካሚዮኖች መደብደባቸዉን ድርጅቱ አስታወቀ።በጥቃቱ ሰዎች ተጎድተዋል።የሱዳን ጦርነት ያሰደደዉ ሕዝብ ቁጥር ደግሞ ከአራት ሚሊዮን በልጧል።-የሩሲያና የዩክሬን ጦር ኃይላት አንዳቸዉ የሌላቸዉን ይዞታ ማጥቃታቸዉን ዛሬም እንደመሰንበቻዉ ቀጥለዉ ዉለዋል።
    12 min
  • የዓለም ዜና፤ ግንቦት 25 ቀን 2017 ሰኞ
    አርስተ ዜና---
    አቶ ታዬ ደንደዓ ከዚህ በፊት ነጻ የተባሉባቸውን የክስ ጭብጦች በመሻር እንዲከላከሉ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዛሬ አዘዘ፡፡ በሌላ በኩል አቶ ታየ ከፍርድ ቤት መልስ መታሰራቸዉ ተሰምቷል።--የቀድሞዋ የጀርመን የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር አናሌና ቤርቦክ በኒውዮርክ የሚገኘው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጠቅላላ ጉባኤ ፕሬዚዳንት ሆነዉ ተሾሙ።--ሳዑዲ አረቢያ ላልተወሰነ ጊዜ ለኢትዮጵያና ለሌሎች ስድስት የአፍሪቃ ሃገራት ዜጎች የሥራ ቪዛ መስጠት ማቋረጥዋን አስታወቀች።--በሚልዮን የሚቆጠሩ ሙስሊም ምዕመናን ከዓመታዊው የሐጅ መንፈሳዊ ጉዞ በፊት ወደ ቅድስት ከተማ መካ እየገቡ ነዉ።
    13 min
  • የግንቦት 24 ቀን 2017 ዓ ም የዓለም ዜና
    *ናይጄሪያ ውስጥ 22 አትሉቶች በአውቶቢስ አደጋ ሞቱ
    *ህገ ወጥ አፍሪካውያን ስደተኞች ከቲኒዚያ መመለስ ይሻሉ
    *ዩክሬን ከ 40 በላይ የሩሲያ አይሮፕኖችን አወደምኩ አለች
    *ኢራን ከአውሮፓ ማዕቀብ ቢጣልባት አጸፋ እንደምትወስድ ዛተች
    *ከቻምፒየንስ ሊግ ፍፃሜ በኋላ በፈረንሳይ ሁለት ሰዎች ተገደሉ፣ በመቶዎች ታሰሩ
    9 min

About የዓለም ዜና

From the publisher's feed

ዶይቼ ቬለ የዕለቱን ዋና ዋና ዜናዎች ከኢትዮጵያ እና ከመላው ዓለም በየቀኑ ያቀርባል። የኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ፖለቲካዊ እና ኤኮኖሚያዊ ጉዳዮችን ጨምሮ የመላው ዓለምን ውሎ የተመለከቱ ጠቃሚ መረጃዎች በሰባቱም የሣምንቱ ቀናት ከምሽቱ አንድ ሰዓት ከዶይቼ ቬለ ያድምጡ። የዶይቼ ቬለን ዜናዎች በአፕል ፖድካስት…