የዓለም ዜና

የዓለም ዜና

Download on the App Store

የዓለም ዜና episodes

  • የግንቦት 13 ቀን 2017 የዓለም ዜና
    -በኦሮሚያ ክልል ደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዉስጥ የኤሌክትሪክ ኃይልና ዉኃ ለተከታታይ ሳምንታት በመቋረጡ ሕዝብ ለችግር መጋለጡን ነዋሪዎች አስታወቁ።ዉኃና መብራቱ የተቋረጠዉ አንድ የኤሌክትሪክ ኃይል ማከፋፈያ በመቃጠሉ እንደሆነ ባለሥልጣናት አስታዉቀዋል።---የእስራኤል መንግሥት የጋዛ ፍልስጤሞችን መግደል፣ማሰቃየትና ማስራቡን እንዲያቆም የሚደረግበት ግፊት እንደቀጠለ ነዉ።የእስራኤል ወታደሮች የምዕራባዊ ዮርዳኖስ ወንዝ ዳርቻን በሚጎበኙ ዲፕሎማቶች ላይ ተኩስ መክፈታቸዉን አዉሮጶች አዉግዘዉታል።---የሩሲያዉ ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን ጦራቸዉ በቅርቡ መልሶ የተቆጣጠራትን የኩርስክ ግዛትን ጎበኙ።
    12 min
  • የግንቦት 11 ቀን 2017 ዓ.ም. የዓለም ዜና
    የግንቦት 11 ቀን 2017 ዓ.ም አርዕስተ ዜና
    የጤና ባለሞያዎች የሥራ ማቆም አድማ ዛሬም በአንዳንድ ሆስፒታሎች መቀጠሉን የንቅናቄው አስተባባሪዎች ለዶቼቬለ ተናግረዋል። አንዳንዶቹ ደግሞ በከፊል ሥራ ላይ እንደሆኑ ገልጸዋል።
    የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ነታንያሁ እስራኤል መላ ጋዛን እንደምትቆጣጠር አስታወቁ። ነታንያሁ በዘመቻው ሀማስ እስካሁን ጋዛ ውስጥ የያዛቸውን 58 ታጋቾችን ማስለቀቅና በሚሊሽያዎች ላይ ሙሉ ድል መቀዳጀትን እናሳካለን ብለዋል።
    ብሪታንያ ከአውሮፓ ኅብረት አባልነት ከወጣች ከአምስት ዓመት በኋላ ከኅብረቱ ጋር አዲስ የአጋርነት ስምምነት ዛሬ ተፈራረመች።
    11 min
  • የግንቦት 09 ቀን 2017 የዓለም ዜና
    የኢትዮጵያ መንግሥት በሥራቸው ምክንያት በቁጥጥር ሥር ያዋላቸውን ጋዜጠኞች እንዲፈታ የዓለም አቀፉ የጋዜጠኞች መብቶች ተሟጋች የአፍሪካ ፕሮግራም አስተባባሪ ጥሪ አቀረቡ። የተባበሩት መንግሥታት በገንዘብ እጥረት ምክንያት በሶማሊያ እና በየመን ለመስጠት ያቀደውን የሰብአዊ ርዳታ ግብ ቀነሰ። በናይጄሪያ ቦርኖ ግዛት ታጣቂዎች 23 ገበሬዎች እና አሳ አጥማጆች ገደሉ። የእስራኤል ጦር ሐማስ ታጋቾችን እንዲለቅ ለማስገደድ በጋዛ ሠርጥ ከፍተኛ ወታደራዊ ዘመቻ ከፈተ። የሩሲያው ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን እና የዩክሬን አቻቸው ቮሎዶሚር ዜሌንስኪ ሊገናኙ የሚችሉት ሁለቱ ሀገራት ሥምምነት ላይ ከደረሱ በኋላ ብቻ እንደሆነ ክሬምሊን አስታወቀ።
    11 min
  • የግንቦት 8 ቀን 2017 ዓ.ም. የዓለም ዜና
    የግንቦት 8 ቀን 2017 ዓ.ም. አርዕስተ ዜና
    በተለያዩ መጋዘኖች ውስጥ የተከማቸ ከ60 ሺህ ሜትሪክ ቶን በላይ የዩናይትድ ስቴትስ የምግብ እርዳታ እየተበላሸ ነው ሲሉ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ተናገሩ።
    የዩክሬንና ሩስያ ተወካዮች ዛሬ ኢስታንቡል ቱርክ ውስጥ ያካሄዱት ቀጥተኛ ንግግር በሁለቱ ወገኖች መካከል ያለውን ልዩነት ለማጥበብ ከፍተኛ የሚባል ውጤት አለማምጣቱን የዩክሬን ምንጮች አስታውቀዋል።ሩስያ ግን በሰላም ንግግሩ ረክቻለው አለች።
    እስራኤል ዛሬ በጋዛ ሰርጥ ባካሄደችው የአየር ድብደባ ቢያንስ 100 ሰዎች ተገድለዋል ሲል የፍልስጤም ዜና አገልግሎት አስታወቀ ። በርካቶች በፍርስራሾች ስር ተቀብረዋል ብሏል።
    11 min
  • የረቡዕ ግንቦት 6 ቀን፣ 2017 ዓ.ም የዓለም ዜና
    የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሕወሓትን ከፖለቲካ ፓርቲነት ሠረዘ፣ ጋሞ፥ ጋሞ ዞን በተከሰተ ግጭት አንድ የፀጥታ አባልን ጨምሮ የአራት ሰዎች ሕወት ማለፉ ተዘገበ፣ እየሩሣሌም፥ የጀርመን ፕሬዚደንት ፍራንክ ቫልተር ሽታየንማየር ሐማስ ጥቃት ያደረሰበት ሥፍራ ጎበኙ፣ ቤርሊን፥ የጀርመን ጠንካራ ጦር ሠራዊት መገንባት ይገባታል፦ ሜርትስ፣ ዶሐ፥ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ በመካከለኛው ምሥራቅ ጉብኝታቸውን ቀጥለዋል፣ ዶሐ፥ ካታር ከዩናይትድ ስቴትስ ቦይንግ 160 ጄቶች በ200 ቢሊዮን ዶላር ልትገዛ ነው
    10 min
  • የግንቦት 5 ቀን 2017 ዓ.ም. የዓለም ዜና
    የግንቦት 5 ቀን 2017 ዓ.ም. አርዕስተ ዜና
    የትግራይ ክልል ባህል እና ቱሪዝም ቢሮ ወደ ትግራይ ለጉብኝት የሚጓዙ ቱሪስቶችን ጨምሮ በተለያየ ስራ የተሰማሩ የውጭ ዜጎች ወደ ክልሉ እንዳይጓዙ በኤርፖርቶች ክልከላ እየተደረገባቸው ነው ሲል አስታወቀ ።
    የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የአራት ቀናት የመካከለኛው ምሥራቅ ጉብኝታቸውን ዛሬ በሳዑዲ አረብያ ጀመሩ።
    የጀርመን የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር የጀርመን ንጉሳዊ አገዛዝ «Kingdom of Germany» የተባለውን ቀኝ ጽንፈኛ ቡድን ዛሬ አገዱ። የቡድኑ መሪ የተባሉ 4 ሰዎች መያዛቸውንም አስታውቀዋል።
    10 min
  • የዓለም ዜና፤ ግንቦት 4 ቀን 2017 ሰኞ
    አርስተ ዜና፤
    --የኩርድ የሠራተኞች ፓርቲ (ፒኬኬ)ቱርክ ዉስጥ ለ 41 ዓመታት ያካሔደውን ደም አፋሳሽ የትጥቅ ትግል ማብቃቱና ቡድኑንም እንደበተነ ፓርቲዉ ዛሬ አስታወቀ።--ኢትዮጵያ ዉስጥ የሚከፈለን ደመወዝ ተመጣጣኝ አይደለም ሲሉ ሰልፍ የወጡ የጤና ባለሙያዎች ታሰሩ።--በትራምፕ አስተዳደር ፕሮግራም አማካኝነት አሜሪካ ዉስጥ የጥገኝነት መብት የተሰጣቸው ነጭ ደቡብ አፍሪቃውያን የመጀመሪያ ቡድን ደቡብ አፍሪቃን ለቀቁ።--ሀማስ አንድ አሜሪካዊ ታጋችን እንደሚለቅ አስታወቀ።--ጀርመንና እስራኤል የዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የጀመሩበት 60ኛ ዓመት ዛሬ በርሊን ላይ ታሰበ።
    12 min

About የዓለም ዜና

From the publisher's feed

ዶይቼ ቬለ የዕለቱን ዋና ዋና ዜናዎች ከኢትዮጵያ እና ከመላው ዓለም በየቀኑ ያቀርባል። የኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ፖለቲካዊ እና ኤኮኖሚያዊ ጉዳዮችን ጨምሮ የመላው ዓለምን ውሎ የተመለከቱ ጠቃሚ መረጃዎች በሰባቱም የሣምንቱ ቀናት ከምሽቱ አንድ ሰዓት ከዶይቼ ቬለ ያድምጡ። የዶይቼ ቬለን ዜናዎች በአፕል ፖድካስት…