የዓለም ዜና

የዓለም ዜና

Download on the App Store

የዓለም ዜና episodes

  • የግንቦት አንድ ቀን 2017 ዓ.ም. የዓለም ዜና
    የግንቦት አንድ ቀን አርዕስተ ዜና
    ምያንማር ውስጥ ለዘጠኝ ወራት "በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ" የቆዩ 82 ኢትዮጵያውያን ዛሬ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ። ሌሎች 41 ኢትዮጵያውያን ደግሞ በዚህ ሳምንት ረቡዕ ሀገራቸው ገብተዋል።
    የሱዳን የወደብ ከተማ ፖርት ሱዳን ዛሬ ለ6ተኛ ተከታታይ ቀን በድሮን መመታትዋን የሱዳን ጦር ምንጮች አስታወቁ። ምንጮቹ ለጥቃቱ ከሚያዚያ 2015 ዓ.ም. አንስቶ ከሱዳን ጦር ጋር ውጊያ የሚያካሂደውን የፈጥኖ ደራሹን ኃይል ተጠያቂ አድርገዋል።
    የእስራኤል ጦር ከየመን የተወነጨፈ ሚሳይል ዛሬ መትቶ መጣሉን አሳወቀ። ሚሳይሉን አስወንጭፊያለሁ ሲል ወዲያውኑ ኃላፊነቱን የወሰደ ግን የለም።
    11 min
  • DW Amharic የሚያዝያ 30 ቀን 2017 የዓለም ዜና
    የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለሥልጣን አቶ ኤርሚያስ አመልጋን ጨምሮ “በሕገ-ወጥ መንገድ ሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ለሕዝብ ሽያጭ በማቅረብ ገንዘብ ሲያሰባስቡ ነበር” ተብለው በተጠረጠሩ ግለሰቦች እና ድርጅቶች ላይ ምርመራ ጀመረ። የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች ቻይና ሠራሽ የጦር መሣሪያዎች ለሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይል ማቅረቧን እንዳረጋገጠ አምስነቲ ኢንተርናሽናል አስታወቀ። የጀርመን ፕሬዝደንት ፍራንክ ቫልተር ሽታይንማየር በዩክሬን ጦርነት የምትነዛውን ታሪካዊ ውሸት ነቀፉ። ሩሲያ የድል ቀንን ለመዘከር ስትዘጋጅ ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን እና የቻይና አቻቸው ሺ ጂን ፒንግ ለምዕራቡ ያላቸውን እምቢተኝነት በግልጽ አሳይተዋል።
    12 min
  • የሚያዚያ 29 ቀን 2017 የዓለም ዜና
    -የኢትዮጵያ የጤና ባለሙያዎች የደሞዝ ጭማሪ እንዲደረግላቸዉና ጥቅማጥቅሞች እንዲከበሩላቸዉ በየሚሰሩበት ተቋማት በመሠለፍ ጠየቁ።በተለያዩ ሆስፒታሎችና የጤና ተቋማት የሚያገለግሉ የጤና ባለሙያዎች ጥያቄያቸዉ ተገቢ መልስ ካላገኘ የሥራ ማቆም አድማ እንደሚመቱ አስጠንቅቀዋል።---ሕንድና ፓኪስታን አዲስ የገጠሙትን ግጭት እንዲያቆሙ የተለያዩ መንግሥታት ጠየቁ።ሁለቱ ኑክሌር የታጠቁ ተጎራባች መንግስታት ግን አንዳቸዉ ሌላቸዉን ለማጥቃት እየተዛዛቱ ነዉ።-ፈረንሳይና ጀርመን ፍራንኮ-ጀርመን የተባለ የመከላከያና የፀጥታ የጋራ ምክር ቤት ለመመሥረት ተስማሙ።
    12 min
  • የዓለም ዜና ፤ ሚያዝያ 28 ቀን 2017 ዓ.ም ማክሰኞ
    አርስተ ዜና፤--የክርስቲያን ዴሞክራቶች ኅብረት ፓርቲ መሪ ፍሪድሬሽ ሜርስ አዲሱ የጀርመን መራኄ መንግሥት ሆኑ። ከሁለተኛዉ የዓለም ጦርነት ወዲህ 10ኛዉ የጀርመን ቻንስለር ሜርስ ቃለ-መሃላ ፈፅመዉ ሥልጣኑን በይፋ ተረክበዋል።--በአማራ ክልል ከመተማ ጎንደር ያለው መንገድ ከተዘጋ አንድ ወር በማስቆጠሩ በአካባቢው ነዋሪዎች የማህበራዊና ኢኮኒሚያዊ እንቅስቃሴ ላይ ጫና ማሳደሩን ነዋሪዎች ተናገሩ።--ለሃገራት የሚሰጠዉ ሰብዓዊ እርዳታ መቀነስ በዓለም አቀፍ ደረጃ እድገት እንዲቀዛቀዝ ምክንያት ሆኗል ሲል የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አስታወቀ።
    13 min
  • DW Amharic ሚያዝያ 27 ቀን 2017 የዓለም ዜና
    የእስራኤል ውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ሳር ለሥራ ጉብኝት ኢትዮጵያ ገቡ። በአማራ ክልል ደሴ እና ወልድያ ከተሞች የአጭር ርቀት አሽከርካሪዎች ከዛሬ ጀምሮ የሥራ ማቆም አድማ አደረጉ።
    የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች በሱዳን በተፈጸመ የጅምላ ፍጅት ተባባሪ ሆናለች በሚል የሱዳን መንግሥት ያቀረበውን ክስ የተመ ፍርድ ቤት ውድቅ አደረገ።
    የኬንያው ፕሬዝደንት ዊሊያም ሩቶ በጫማ ተመቱ። የጀርመን ክርስቲያን ዴሞክራቶች ኅብረት ፣ ክርስቲያን ሶሻል ኅብረት እና ሶሻል ዴሞክራት ፓርቲ (SPD) ጥምር መንግሥት የመሠረቱበትን ሥምምነት ተፈራረሙ። እስራኤል ጋዛን ሙሉ በሙሉ ለመያዝ የሚያስችል ዕቅድ ማጽደቋን ባለሥልጣናት ተናገሩ።
    12 min
  • የሚያዝያ 26 ቀን 2017 ዓ.ም የዓለም ዜና
    *የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይል ዛሬ እሁድ በፖርት ሱዳን ከተማ ላይ የድሮን ጥቃት መሰንዘሩን የሱዳን ብሔራዊ ጦር ቃል አቀባይ ተናገሩ።
    *የየመን ሁቲ አማጺያን በዓለም አቀፉ የቴል አቪቭ አውሮፕላን ማረፊያ ላይ ያነጣጠረ የሚሳኤል ጥቃት መሰንዘራቸውን ተከትሎ እስራኤል ከፍተኛ የአፀፋ እርምጃ እንደምትወስድ ገለፀች።
    *የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ምን ያህል የሀገሪቱን ህገ መንግሥት የማክበር ግዴታ እንዳለባቸው ርግጠኛ እንዳልሆኑ ተናገሩ።
    *ኢትዮጵያውያኑ ለሚ ብርሃኑ እና ብርቱካን ወልዴ በቼክ ሪፑብሊክ ዋና ከተማ ፕራግ ዛሬ የተካሄደውን የማራቶን ውድድር በየዘርፋቸው አሸነፉ
    8 min
  • የሚያዝያ 25 ቀን 2017 የዓለም ዜና
    የአስራ አራት ሀገራት ኤምባሲዎች “በኢትዮጵያ ሐሳብን የመግለጽ ነጻነት ብርቱ ጫና ውስጥ ሆኖ መቀጠሉ” እንደሚያሳስባቸው ገለጹ። በደቡብ ሱዳን በድሮን ጥቃት ቢያንስ ሰባት ሰዎች መገደላቸውን እና ሌሎች 20 መቁሰላቸውን ድንበር የለሽ የሐኪሞች ቡድን አስታወቀ። የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይል ድሮኖች ከኤርትራ ድንበር አቅራቢያ የምትገኘው የከሰላ ከተማ ላይ ጥቃት መፈጸማቸውን ወታደራዊ የመረጃ ምንጮች ተናገሩ። ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን ለሦስት ቀናት ተኩስ ለማቆም ላቀረቡት ምክረ-ሐሳብ ዩክሬን ግልጽ ምላሽ እንድትሰጥ ክሬምሊን ጠየቀ። በሻንጋይ ዳይመንድ ሊግ ኢትዮጵያውያኑ ጽጌ ዱጉማ፣ በሪሁ አረጋዊ እና አብርሀም ስሜ አሸናፊ ሆኑ።
    10 min
  • የዐርብ ሚያዝያ 24 ቀን፣ 2017 ዓ.ም የዓለም ዜና
    ካርቱም፥ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች በሱዳን ጦር ሠራዊት አባላት በደል እየደረሰባቸው መሆኑ ተገለጠ፣ አአ፥ የፕሬስ ነጻነት በኢትዮጵያ ዘንድሮም ማሽቆልቆሉ ተገለጠ፣ ካርቱም፥ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች በሱዳን ጦር ሠራዊት አባላት በደል እየደረሰባቸው መሆኑ ተገለጠ፣ ጆሐንስበርግ፥ የደቡብ አፍሪቃ ፖሊስ 44 ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን ጆሐንስበርግ ውስጥ ከተቆለፈባቸው ቤት አስለቀቀ፣ ዋሽንግተን፥ የኋይት ሐውስ ብሔራዊ የፀጥታ አማካሪ ማይክ ዋልትስ ከኃላፊነታቸው ተነሱ፤ቤርሊን፥ መጤ ጠሉ አማራጭ ለጀርመ ፓርቲ (AFD)ዛሬ በቀኝ አክራሪነት ተፈረጀ
    11 min

About የዓለም ዜና

From the publisher's feed

ዶይቼ ቬለ የዕለቱን ዋና ዋና ዜናዎች ከኢትዮጵያ እና ከመላው ዓለም በየቀኑ ያቀርባል። የኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ፖለቲካዊ እና ኤኮኖሚያዊ ጉዳዮችን ጨምሮ የመላው ዓለምን ውሎ የተመለከቱ ጠቃሚ መረጃዎች በሰባቱም የሣምንቱ ቀናት ከምሽቱ አንድ ሰዓት ከዶይቼ ቬለ ያድምጡ። የዶይቼ ቬለን ዜናዎች በአፕል ፖድካስት…