የዓለም ዜና

የዓለም ዜና

Download on the App Store

የዓለም ዜና episodes

  • DW Amharic የሚያዝያ 12 ቀን 2017 የዓለም ዜና
    በዓለም ዙሪያ የክርስትና እምነት ተከታዮች የትንሳኤ በዓልን አከበሩ። ሩሲያ እና ዩክሬን የተኩስ አቁም በመጣስ እርስ በርስ ተወነጃጀሉ። የእስራኤል ጦር በጋዛ 15 የሕክምና ባለሙያዎች የተገደሉበት ባለፈው ወር የተፈጸመ ጥቃት ላይ በተደረገ ምርመራ በርካታ ሙያዊ ስሕተቶች እና የትዕዛዝ ጥሰቶች መገኘታቸውን ይፋ አደረገ። ከፍራንክፉርት አቅራቢያ ሁለት ሰዎች ከተገደሉ በኋላ የጀርመን ፖሊስ ተጠርጣሪ በቁጥጥር ሥር ለማዋል ከፍተኛ ዘመቻ እያካሔደ ነው። በሺሕዎች የሚቆጠሩ አሜሪካውያን ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ እና ፖሊሲዎቻቸውን በመቃወም ኒው ዮርክ እና ዋሽንግተንን ጨምሮ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች አደባባይ ወጡ።
    8 min
  • የሚያዝያ 11 ቀን 2017 የዓለም ዜና
    የኢትዮጵያ የጸጥታ አስከባሪዎች በአዲስ ስታንዳርድ ሚዲያ ቢሮ እና በተቋሙ ሠራተኛ የመኖሪያ ቤት ብርበራ ማካሔዳቸውን ጃኬን አሳታሚ አስታወቀ። ፍሬድሪሽ ሜርስ የጀርመንን ኢኮኖሚ ለማዘመን ቃል ገቡ። የሩሲያው ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን ፋሲካን ምክንያት በማድረግ በዩክሬን በሚካሔደው ጦርነት በተናጠል ተኩስ አቁም አወጁ። የዩክሬን ፕሬዝደንት ቮሎዶሚር ዜሌንስኪ ግን የሩሲያው ፕሬዝደንት "በሰዎች ሕይወት ለመጫወት እየሞከሩ ነው" ሲሉ በታወጀው የአጭር ጊዜ የተኩስ አቁም እምነት እንደሌላቸው የሚጠቁም አስተያየት ሰጥተዋል። ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ባሸነፉበት በቤጂንግ የተካሔደ የግማሽ ማራቶን ሩጫ ቻይና ሰው መሰል ሮቦቶች አወዳደረች።
    9 min
  • የሚያዚያ 10 ቀን 2017 የዓለም ዜና
    -በመላዉ ዓለም የሚገኙ የክርስትና እምነት ተከታዮች ዛሬ የሥቅለት በዓልን አክብረዉ ዋሉ።በአሉ ቫቲካን ዉስጥ በርዕሰ ሊቃነ-ጳጳሳቱ ሕመም፣ እየሩሳሌም ዉስጥ በጦርነት መሐል ግን የግሪጎሪያንና የዩሊዮስ የቀን አቀጣጠርን በሚከተለዉ ዓለም ሁሉ አንድ ቀን ተከብሯል።----የእስራኤል ጦር ጋዛ ሠርጥ፣ የዩናይትድ ስቴትስ ጦር ደግሞ የመን ዉስጥ በርካታ ሰዎችን ገደሉ።እስራኤል ታጋቾች እንዲለቀቁ ያቀረበችዉን ጥያቄ ሐማስ ዉድቅ አደረገዉ።---የዩክሬንና የሩሲያን ጦርነትን በድርድር ለማስቆም ዩናይትድ ስቴትስ የምታደርገዉ ጥረት ባጭር ጊዜ ዉጤት ካላመጣ ጥረቱን ልታቆም እንደምትችል ዉጪ ጉዳይ ሚንስትሯ አስታወቁ።
    12 min
  • የሚያዚያ 6 ቀን 2017 ዓም የዓለም ዜና
    የየካቲት 6 ቀን 2017 ዓ.ም. አርዕስተ ዜና
    በኢትዮጵያ ለከተማ ልማት ሲባል የሚካሄደው የሰዎች መፈናቀል እንዲቆም አምነስቲ ኢንተርናሽናል ጠየቀ ።
    ሩስያ ትንናት ዩክሬን ሰሚ በተባለው ከተማ የጣለችው ጥቃት ዒላማ የዩክሬን ወታደሮች ነበሩ ስትል ዛሬ አስታወቀች። የሩስያ መከላከያ ሚኒስቴር ድብደባው ያነጣጠረው የዩክሬን ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖች ስብሰባ ላይ መሆኑን ጠቅሶ ኪቭ ሲቭሎችን እንደ ሰብዓዊ ጋሻ በመጠቀም በከተማዋ ማዕከል ወታደራዊ ስብሰባ ማካሄዷን ኮንኗል።
    የጀርመን ፓርላማ ከሦስት ሳምንት በኋላ ፍሪድሪሽ ሜርስን በመራኄ መንግስትነት ይመርጣል ተብሎ ይጠበቃል።
    11 min
  • የሚያዚያ 9 ቀን 2017 ዓ.ም. የዓለም ዜና
    የሚያዚያ 9 ቀን 2017 ዓ.ም. አርዕስተ ዜና
    በዳፍሩርዋ ኤል ፋሸር በተካሄደ ግጭት ቢያንስ 57 ሰላማዊ ሰዎች መገደላቸው ተሰማ።ሰላማዊ ሰዎቹ የተገደሉት የመንግስት ጦርን የሚወጋው ፈጥኖ ደራሹ ኃይል ትናንት በከተማይቱ ባካሄደው ድብደባ ነው።
    የሶማሊያና የአሜሪካን ኃይሎች አሸባብ ጥቃት በከፈተበት በአዳን ያባል በጋራ ባካሄዱት የአየር ጥቃትና ውጊያ 12 የቡድኑን ሚሊሽያዎች መግደላቸውን የሶማሊያ መንግስት ዛሬ አስታወቀ።
    የዩክሬን ፕሬዝዳንት ቮሎዶሚር ዜሌንስኪ ከፍተኛ አማካሪዎቻቸው በፓሪስ ከአሜሪካና ከአውሮጳውያን ጋር በተነጋገሩበት በዛሬው እለት የዩክሬኑ ጦርነት እንዲቆም ሩስያ ላይ ግፊት እንዲደረግ ጠየቁ።
    12 min
  • የሚያዝያ 8 ቀን 2017 የዓለም ዜና
    የኢትዮጵያ “የመምህራን የኅብረት ሥራ ባንክ” በ2018 ሥራ ሊጀምር እንደሚችል የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሀኑ ነጋ ፍንጭ ሰጡ። ሚኒስትሩ ከትምህርት የቀሩ 7.2 ሚሊዮን ተማሪዎች ጉዳይ በጣም ሊያሳስብ እንደሚገባ ተናግረዋል። አልሸባብ በማዕከላዊ ሶማሊያ አዳን ያባል የተባለች ወታደራዊ ማዕከል ላይ ጥቃት ከፈተ። የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይል አዛዥ መሐመድ ሐምዳን ደጋሎ ትይዩ መንግሥት መመሥረታቸውን ይፋ አደረጉ። አሜሪካ በኤርትራ እና በደቡብ ሱዳን ኤምባሲዎቿን ልትዘጋ ነው። ዶናልድ ትራምፕ "ማስፈራራት እና ሥም ማጥፋት እንዲያቆሙ" ቻይና ጠየቀች። እስራኤል ወደ ጋዛ ሰብአዊ ርዳታ እንዳይገባ መከልከሏን እንደምትቀጥል አስታወቀች።
    13 min
  • DW Amharic የሚያዝያ 7 ቀን 2017 የዓለም ዜና
    በአማራ ክልል ከመንግሥት የሚዋጉ ታጣቂ ኃይሎች “ችግሮችን ለመፍታት ወደ ውይይት እንዲመጡ” የአማራ ክልል የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ጥሪ አቀረበ። በደቡብ ሱዳን እየተባባሰ በመጣው ግጭት ካለፈው መጋቢት ወዲህ ከ200 በላይ ሰዎች መገደላቸውን እና ከ125,000 በላይ የሚገመቱ ሰዎች መፈናቀላቸውን የተመድ አስታወቀ። ሶማሊያ ከ56 ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ለምርጫ ድምጽ ሰጪዎችን መመዝገብ ጀመረች።በሱዳን አስገድዶ መድፈር እንደ ጦር ሥልት ጥቅም ላይ እየዋለ ነው ተባለ። እስራኤል በጋዛ ሠርጥ በሚገኘው የኩዌት የመስክ ሆፒታል ደጃፍ በፈጸመችው የአየር ጥቃት አንድ የሕክምና ባለሙያ ሲገደሉ በርካቶች ቆሰሉ።
    12 min
  • DW Amharic የሚያዝያ 5 ቀን 2017 የዓለም ዜና
    ሩሲያ በሰሜናዊ ዩክሬን በምትገኘው ሱሚ የተባለች ከተማ ላይ በባልስቲክ ሚሳይል ዛሬ እሁድ ጠዋት በፈጸመችው ጥቃት ሁለት ሕጻናትን ጨምሮ በትንሹ 32 ሰዎች መገደላቸውን ዩክሬን አስታወቀች። የተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ቢሮ (OCHA) በ60 ሀገራት የሚገኙ 2,600 ሠራተኞቹን ሊቀንስ ነው። በጋዛ በሥራ ላይ ከሚገኙ ጥቂት ሆስፒታሎች አንዱ ዛሬ እሁድ በተፈጸመ የእስራኤል የአየር ጥቃት ከፍተኛ ጉዳት እንደደረሰበት የጋዛ የሲቪል ጥበቃ ኤጀንሲ አስታወቀ። በፓሪስ ማራቶን ኢትዮጵያውያኑ በዳቱ ሒርጳ እና ደራ ዲዳ ተከታትለው በመግባት አሸነፉ።
    8 min

About የዓለም ዜና

From the publisher's feed

ዶይቼ ቬለ የዕለቱን ዋና ዋና ዜናዎች ከኢትዮጵያ እና ከመላው ዓለም በየቀኑ ያቀርባል። የኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ፖለቲካዊ እና ኤኮኖሚያዊ ጉዳዮችን ጨምሮ የመላው ዓለምን ውሎ የተመለከቱ ጠቃሚ መረጃዎች በሰባቱም የሣምንቱ ቀናት ከምሽቱ አንድ ሰዓት ከዶይቼ ቬለ ያድምጡ። የዶይቼ ቬለን ዜናዎች በአፕል ፖድካስት…