የዓለም ዜና

የዓለም ዜና

Download on the App Store

የዓለም ዜና episodes

  • የዓለም ዜና፤ መጋቢት 25 ቀን 2017 ሃሙስ
    አርስተ ዜና--የግሪክ ባህር ድንበር ላይ አንዲት ስደተኞችን የጫነች ጀልባ ተገልብጣ ሁለት ህጻናትን ጨምሮ የሰባት ሰዎች ህይወት አለፈ።--በአማራ ክልል አንዳንድ አካባቢዎች የኮሌራ በሽታ መከሰቱን የአማራ ክልል ህብረተሰብ ጤና ተቋም አስታወቀ። በቋራና በባህር ዳር ዙሪያ ወረዳዎች 1000 የሚጠጉ ሠዎች በበሽታው ተይጠዋል እስካሁን ዘጠኝ ሰዎች ሞተዋል።-- ትራምፕ ትዮጵያም ወደ አሜሪካ በምትልከዉ ሸቀጦች ላይ የ 10 በመቶ የቀረጥ ጭማሪ ጣሉ።--ዓለምአቀፉ የጦር ወንጀለኞች መዳኛ ፍርድ ቤት የእስር ማዘዣ የቆረጠባቸዉ፣ የእስራኤሉ ጠ/ሚ ቤንያሚን ኔታንያሁ ያለምንም ችግር ቡዳፔስት ገቡ።
    10 min
  • የመጋቢት 24 ቀን 2017 የዓለም ዜና
    -የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አሕመድ ሥልጣን በያዙበት ወቅት የነበረዉ የሠላም፣የዲሞክራሲና የመልካም አስተዳደር ቃልና ተስፋ እየሟሸሸ መምጣቱ በሰፊዉ እየተነገረ ነዉ።ጠቅላይ ሚንስትሩ ሥልጣን ከያዙ ዛሬ 7ኛ ዓመታቸዉን ደፈኑ።ኢትዮጵያ ዉስጥ የጋዜጠኞች የመሥራት ነፃነትና ደሕንነት አሁንም አስጊ ነዉ።-የእስራኤል ጦርጋዛ ሰርጥ ላይ በከፈተዉ የዓየር ጥቃት በትንሹ 40 ፍልስጤማዉያን ተገደሉ።ጀርመን ደቡባዊ ጋዛ ራፋሕ ዉስጥ ሰሞኑን የተገደሉት የሕክምና ባለሙያዎች አሟሟት እንዲጣራ ጠየቀች።-ምያንማርን በመታዉ የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ የሞቱት ሰዎች ቁጥር ከ3000 በለጠ።
    12 min
  • የማክሰኞ መጋቢት 23 ቀን 2017 ዓ.ም. የዓለም ዜና
    የመጋቢት 23 ቀን 2017 ዓ.ም.ዐርእስተ ዜና
    የኢትዮጵያ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፌደራል መንግሥት በክልል ጣልቃ የሚገባበትን ሥርዓት የሚደነግገውን አዋጅ ዛሬ አሻሻለ ። የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የሥልጣን ዘመን ለተጨማሪ ዓመት እንዲራዘም የሚያስችለው አዋጅ በ2 ድምጸ ተዐቅቦ በአብላጫ ድምጽ ነው የፀደቀው።
    ዩናናይትድ ስቴትስ በየመን የጀመረችውን የአየር ጥቃት አጠናክራ በቀጠለችበት በአሁኑ ጊዜ የየመን ሁቲዎች አማጺ ቡድን ሌላ የአሜሪካን ድሮን ጥለናል ሲል ዛሬ አስታወቀ።
    በምያንማሩ የመሬት መንቀጥቀጥ የሞቱት ሰዎች ቁጥር የሀገሪቱ ወታደራዊ መሪዎች ዛሬ እንደተናገሩት ወደ 2ሺህ 719 ከፍ ብሏል።
    10 min
  • የዓለም ዜና፤ መጋቢት 22 ቀን 2017 ዓ.ም ሰኞ
    አርስተ ዜና፤
    -ፈረንሳዊትዋ የቀኝ አክራሪ ፓርቲ መሪ ማሪን ለ ፔን «ራሊ ናሽናል» በተባለዉ ፓርቲያቸዉ በኩል የአውሮፓ ፓርላማ ገንዘብን አላግባብ በመጠቀም ጥፋተኛ ተባሉ። አራት ዓመት እስር የተፈረደባቸዉ ላፔን ሁለት ዓመት እግራቸዉ ላይ መቆጣጠርያ ታስሮ የቁም እስረኛ እንደሚሆኑ ተነገረ።-በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን አበዶንጎሮ ወረዳ ውስጥ ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት ጸጥታ ሐይሎችን ጨምሮ የ 21 ሰዎች ህይወት ጠፋ።-የአሜሪካዉ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በሩስያዉ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን አቋም እጅግ መበሳጨታቸዉን ገለፁ። ፑቲን በበኩላቸዉ በጽ/ቤታቸዉ በኩል ለትራምፕ በሬ ክፍት ነዉ ብለዋል።
    16 min
  • የመጋቢት 19 ቀን 2017 ዓ.ም. የዓለም ዜና
    በአዲስ አበባ፣ በድሬዳዋ፣ በሀዋሳ እና በሆሳዕና ከተሞች «እርስ በርሱ የሚቀናቀን፣ ብሔር እና ሃይማኖት ተኮር የሆኑ እንቅስቃሴዎች መጨመር» ለውዝግብ ምክንያት እንደሆነ አንድ ጥናት አመለከተ።
    የአውሮጳ ሕብረት የደቡብ ሱዳን ፕሬዝደንት በሀገሪቱ ውስጥ የተፈጠረውን የፖለቲካ ውጥረት እንዲያረግቡ ጠየቀ። ፕሬዝደንት ሳል ቫኪር ምክትል ፕሬዝደንት ሪክ ማቻርን ማሰራቸው በሀገሪቱ ፍርሃትና ውጥረት አስከትሏል።
    በሬክተር 7,7 በተለካው ምያንማር ውስጥ በደረሰው የመሬት መንቀጥቀጥ የሞቱት ሰዎች 144 ደረሱ። 732 ሰዎችም ተጎድተዋል። ለ12 ጊዜ በተደጋጋሚ የደረሰው የመሬት መንቀጥቀጥ ታይላንድንም አናግቷል።
    9 min
  • የዓለም ዜና፤ መጋቢት 18 ቀን 2017 ዓ.ም ሃሙስ
    አርስተ ዜና
    -የዩክሬን ፕሬዚዳንት የሰሜን ጦር ቃል ኪዳን ድርጅት /ኔቶ/ የአገራቸው ምርጥ የደህንነት ዋስትና ነው ሲሉ ተናገሩ። ዜሌንስኪ ዩናይትድ ስቴትስ ግን ይህን ለመቀላቀል እና ለዩክሬን ለመቆም "ዝግጁ አይደለችም" ብለዋል።
    -የኢትዮጵያ መንግስት በተደጋጋሚ የፕሪቶርያው የሰላም ስምምነትን እየጣሰ ነው ሲል ህወሓት ከሰሰ። በዶክተር ደብረፅዮን የሚመራው ህወሓት በመግለጫዉ የጊዚያዊ አስተዳደርን በተመለከተ “የተናጠል” ውሳኔ ማስተላለፍ አይቻልም ሲል ትላንት ጠ/ሚ አብይ ለትግራይ ህዝብ ያስተላለፉትን የፕሬዚደንት ጥቆማ ጥሪ ተችቷል።
    11 min
  • የመጋቢት 17 ቀን 2017 ዓ.ም. የዓለም ዜና
    የመጋቢት 17 ቀን 2017 ዓም ዐርእስተ ዜና
    የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የትግራይ ሕዝብ ለሚቀጥለው አንድ አመት የክልሉ ጊዚያዊ አስተዳድር ፕሬዝዳንት ሊሆን የሚችል ሰው እንዲጠቁም ጥሪ አቀረቡ።
    የጀርመን ፖሊስ ፣ የኤርትራን መንግስት የመገልበጥ ዓላማ አለው የተባለውን እና የዓለም አቀፍ መረብ አካል መሆኑ የተገለጸ ብርጌድ ንህመዱ የተባለው ቡድን የጀርመን ቅርንጫ ላይ ፣ዛሬ በስድስት የጀርመን ፌደራዊ ግዛቶች ልዩ ፍተሻ ማድረጉን አስታወቀ።
    የሱዳን ጦር ፤ፈጥኖ ደራሹ ኃይል ተቆጣጥሮት የነበረውን የኻርቱምን አውሮፕላን ማረፊያ መልሶ መያዙን አስታወቀ።
    11 min
  • የመጋቢት 16 ቀን 2017 የዓለም ዜና
    -ከአዲስ አበባ ወደ ደብረ ማርቆስ በአዉቶቡስ ሲጓዙ ኦሮሚያ ክልል ካንድ ሳምንት በፊት የታገቱት መንገደኞች ያሉበት ሥፍራና ሁኔታ እስካሁን አለመታወቁ ተነገረ።መንገደኞቹ ሲታገቱ ያዩ እንደሚሉት የመንግሥት ፀጥታ አስከባሪዎች በአጋቾቹ ላይ ተኩስ ቢከፍቱም ታጋቾቹን ማስጣል ግን አልቻሉም።-አዲስ አበባ ዉስጥ በልማዱ ሰባራ ባቡር በተባለዉ አካባቢ ዛሬ ጠዋት የተነሳ የእሳት ቃጠሎ ሁለት የእሳት አደጋ መከላከያ ሠራተኞችን አቆሰለ።ሶስት መደብሮችንም አጋየ።-በሩዋንዳ የሚደገፈዉ የኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ አማፂ ቡድንና የሐገሪቱ መንግስት ጦር የገጠሙት ዉጊያ መዘዝ ለአካባቢዉ ሐገራት ሊተርፍ እንደሚችል የኬንያ ፕሬዝደንት አስታወቁ።
    11 min

About የዓለም ዜና

From the publisher's feed

ዶይቼ ቬለ የዕለቱን ዋና ዋና ዜናዎች ከኢትዮጵያ እና ከመላው ዓለም በየቀኑ ያቀርባል። የኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ፖለቲካዊ እና ኤኮኖሚያዊ ጉዳዮችን ጨምሮ የመላው ዓለምን ውሎ የተመለከቱ ጠቃሚ መረጃዎች በሰባቱም የሣምንቱ ቀናት ከምሽቱ አንድ ሰዓት ከዶይቼ ቬለ ያድምጡ። የዶይቼ ቬለን ዜናዎች በአፕል ፖድካስት…