የዓለም ዜና

የዓለም ዜና

Download on the App Store

የዓለም ዜና episodes

  • የዐርብ መጋቢት 5 ቀን፣ 2017 ዓ.ም የዓለም ዜና
    መቐለ፥ የነገሠው ውጥረት ነዋሪዎችን ሥጋት ላይ ጥሏል፤ አ.አ፥ የትግራይ ክልል ወቅታዊ ሁኔታ «እጅግ እንዳሳሰበው» የአፍሪቃ ኅብረት ዐሳወቀ፤ ሐዋሳ፥የቀድሞው የሐዋሳ ከተማ ከንቲባ በ13 ዓመት ፅኑ እሥራት ተቀጡ፤ ጋምቤላ፥ ቢያንስ 31 ሰዎች በኮሌራ ወረርሺኝ መሞታቸው ተዘገበ፤ ቤርሊን፥ የጀርመን ፓርቲዎች ታሪካዊ ስምምነት ላይ ደረሱ፤ ዋሽንግተን፥ ዶናልድ ትራምፕ ቭላድሚር ፑቲንን ተማጸኑ
    11 min
  • የዓለም ዜና፤ መጋቢት 4 ቀን 2017 ዓ.ም
    አርስተ ዜና፤
    --በትግራይ ክልል የበረታው ውጥረት ጊዜያዊ አስተዳደሩን እና በፕሪቶሪያ የተፈረመውን የግጭት ማቆም ሥምምነት ከማፍረስ ባሻገር ጦርነት ሊቀሰቅስ እንደሚችል አቶጌታቸው ረዳ አስጠነቀቁ። በሌላ በኩል በዶክተር ደብረፅዮን የሚመራው የህወሓት ቡድን፥ ሦስተኛ ወገን ወደ ትግራይ እንዲገባ “ጥሪ መደረግ የለበትም” በማለት ተቃዉሞታል።
    --በኢትዮጵያ እና ኤርትራ መንግሥታት መካከል የተቀሰቀሰዉ ዉጥረት ለቀጠናዉ ሌላ ስጋት መፍጠሩን ሮይተርስ ዛሬ ዘገበ።
    --የኮንጐ ሪፓብሊክ ባለሥልጣናት ከ M23 አማፂያን ለድርድር በሚቀጥለዉ ሳምንት ሉዋንዳ አንጎላ ላይ ለመገናኘት ተስማሙ።
    12 min
  • የረቡዕ መጋቢት 3 ቀን 2017 ዓ.ም. የዓለም ዜና
    የረቡዕ መጋቢት 3 ቀን 2017 ዓ.ም. አርዕስተ ዜና
    በሱዳን ትይዩ መንግስት ማስተዋወቅ ለሁለት ዓመታት ለሚጠጋ ጊዜ በጦርነት የተመሰቃቀለችውን ሀገሪቱን ለመሰንጠቅ አደጋ እንደሚያጋልጥ የአፍሪቃ ኅብረት አስጠነቀቀ።
    የሶማሊያን መንግሥት የሚወጋው አሸባብ ትናንት ማዕከላዊ ሶማሊያ በሚገኝ ሆቴል ላይ በፈጸመው ጥቃት የሞቱት ሰዎች ቁጥር ወደ 10 ከፍ አለ።
    አሜሪካ ከዛሬ ጀምሮ በብረት እና በአሉምንየም ላይ ተግባራዊ ለምታደርገው አዲሱ ታሪፍ፣የአውሮጳ ኅብረት የአጸፋ እርምጃ እንደሚወስድ አስታወቀ።
    11 min
  • የመጋቢት 2 ቀን፣ 2017 ዓ.ም የዓለም ዜና
    ዋሽንግተን፥ የዩናይትድ ስቴትስ የመጓጓዣ ኃላፊ የቦይንግ ዋና ሥራ አስፈጻሚን ሊያናግሩ ነው፤ ሞቃዲሹ፥ አልሸባብ መዓከላዊ ሶማሊያ ውስጥ ጥቃት አደረሰ፤ ጁባ፥ ኡጋንዳ ወደ ደቡብ ሱዳን ዋና ከተማ ልዩ ኃይል መላኳን ገለጠች፤ ጅዳ፥ የዩክሬን እና ዩናይትድ ስቴትስ ውጭ ጉዳይ ሚንሥትሮች ዛሬ ሣዑዲ ዓረቢያ ውስጥ ተወያዩ፤ ቤጂንግ፥ ቻይና ለዩክሬን ሩስያ ጦርነት «ፍትኃዊ እና ዘላቂ መፍትኄ» እንደሚመጣ ተስፋ መሰነቋን ገለጠች፤ ሞስኮ፥ ዩክሬን መጠነ ሰፊ የድሮን ጥቃት ሞስኮ ላይ አደረሰች፤ ኩርክስ፥ ሩስያ ከኩርክስ ግዛቷ በርካታ ከተሞችን ከዩክሬን «ነጻ ማውጣቷን» ገለጠች
    10 min
  • የዓለም ዜና፤ መጋቢት 1 ቀን 2017 ዓ.ም ሰኞ
    የዓለም ዜና፤ መጋቢት 1 ቀን 2017 ዓ.ም ሰኞ
    --ከሩሲያ ጋር በሚደረገው ጦርነት ዩክሬን በዓለም ትልቁ የጦር መሳሪያ አስመጪ ሃገር መሆንዋ ተገለፀ። የጦር መሳሪያ ላኪ ከሚባሉት ቀዳሚ የዓለም ሃገሮች መካከል ዩናይትድ ስቴትስ፣ ፈረንሳይ፣ ሩሲያ እና ቻይና ናቸዉ። ጀርመን በአምስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች። --ምያንማር ውስጥ በችግር ላይ የነበሩ 32 ኢትዮጵያውያን አዲስ አበባ መመለሳቸዉ ተሰማ።
    በሶርያ በሲቪሎች እና እስረኞች ላይ ግድያ መፈፀሙን የሚመለክተዉ ዘገባ አስደንጋጭ ነዉ ሲል የጀርመን የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዛሬ ይፋ ባደረገዉ መግለጫ አስታወቀ።
    11 min
  • የየካቲት 29 ቀን 2017 ዓ/ም የዓለም ዜና
    DW Amharic-በዛሬው የዓለም ዜና ስደተኞች ያሳፈሩ ጀልባዎች ተገልብጠው ከ180 በላይ ሰዎች መሞታቸውን ፣ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን ዛሬ በመላው ዓለም በልዩ ልዩ ዝግጅቶች ተከብሮ መዋሉን፣ሱዳን የተባበሩት አረብ ኤምሬትስን በዘር ማጥፋት ወንጀል መክሰሷን፣በሶርያ በተቀሰቀሰ ግጭት ከ600 በላይ ሰዎች መገደላቸውን፣ አራት የአውሮፓ ሀገራት ጋዛን መልሶ የመገንባት እቅድን መደገፋቸውን፣አሜሪካ ከ15 ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ አንድ የሞት ፍርደኛ በጥይት እንዲገደል ማድረጓን የሚያስቃኙ ዘገባዎችን አካቷል።
    11 min
  • የአርብ የካቲት 28 ቀን 2017 ዓ.ም. የዓለም ዜና
    የየካቲት 28 ቀን 2017 ዓም አርዕስተ ዜና
    በራያ አላማጣ ወረዳ ጥሙጋ ከተማ ተናንት ሌሊት ዳነ ምህረት ቤተክርስቲያን ውስጥ በተፈፀመ ጥቃት አንድ ዓይነስውር የቤተክርስቲያን መምህርን ጨምሮ 4 የቆሎ ተማሪዎች ተገድለዋል ሲሉ የአካባቢው ነዋሪዎች ተናገሩ፡፡
    ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን የጫኑ አራት ጀልባዎች ትናንት ለሊት በየመንና በጅቡቲ የባህር ክልል ሰጥመው ቢያንስ ሁ2 ት ሰዎች ሲሞቱ186 የደረሱበት ሳይታወቅ ቀረ ።
    የአውሮጳ ኅብረት አባል ሀገራት መሪዎች በዩናይትድ ስቴትስ ፖሊሲዎች መቀየር ምክንያት የመከላከያ ወጪአቸውን ይበልጥ ለመጨመርና ከዩክሬንጎን መቆማቸውን ለመቀጠል ማቀዳቸውን አስታወቁ።
    11 min
  • የሐሙስ፤ የካቲት 27 ቀን፣ 2017 ዓ.ም የዓለም ዜና
    *ኢትዮጵያ ከጦር መሣሪያ ሽያጭ ከ30 ሚሊየን ዶላር ያላነሰ ገቢ ማግኘት መቻሏን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ አመለከቱ ።
    *ኦነግ እና ኦፌኮ ከሳምንታት በፊት በኦሮሚያ ክልል የጋራ «ሽግግር መንግሥት» እንዲመሠረት ከተለያዩ አካላት አደራ መቀበላቸውን በሚመለከት ያራመዱትን አቋም አራት የፖለቲካ ድርጅቶ ተቃወሙ ።
    *ዘ ሔግ በሚገኘው የተመድ ፍርድ ቤት የተባበሩት ዓረብ ኤሚሬቶች የዘር ፍጅት ዓለም አቀፍ ድንጋጌ ተላልፋለች ስትል ሱዳን ክስ መሠረተች ።
    *የአውሮጳ ኅብረት መሪዎች «ግልጽ የሆነ አደጋ ተደቅኖባታል» ላሏት አውሮጳ የ800 ቢሊዮን ዩሮ «አውሮጳን ዳግም የማስታጠቅ» እቅድ በጉባኤ ማቅረባቸው ተዘገበ ።
    9 min

About የዓለም ዜና

From the publisher's feed

ዶይቼ ቬለ የዕለቱን ዋና ዋና ዜናዎች ከኢትዮጵያ እና ከመላው ዓለም በየቀኑ ያቀርባል። የኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ፖለቲካዊ እና ኤኮኖሚያዊ ጉዳዮችን ጨምሮ የመላው ዓለምን ውሎ የተመለከቱ ጠቃሚ መረጃዎች በሰባቱም የሣምንቱ ቀናት ከምሽቱ አንድ ሰዓት ከዶይቼ ቬለ ያድምጡ። የዶይቼ ቬለን ዜናዎች በአፕል ፖድካስት…