የአርብ የካቲት 21 ቀን 2017 ዓም አርዕስተ ዜና
የተመድ በኮንጎውw ውጊያ ምክንያት ብሩንዲ የሚገኙ ዓለም አቀፍ ሠራተኞቹ ሀገሪቱን ለቀው እንዲወጡ አዘዘ።
እስራኤል በኃይል በያዘችው ሰሜናዊ ዌስት ባንክ በምታካሂዳቸው ወታደራዊ ዘመቻዎች ለሰላማዊ ሰዎችና የሰላማዊ ሰዎች መገልገያ ለሆኑ መሠረተ ልማቶች ጥበቃ እንድታደርግ ጀርመን ጠየቀች።
ትናንት ዋሽንግተን የነበሩት የብሪታንያ ጠቅላይ ሚኒስትር ኪር ስታርመር በርካታ የአውሮጳና የአውሮጳ ኅብረት አባል ሀገራት መሪዎች በዩክሬን የወደፊት ጉዞና በሀገሪቱ የፀጥታ ጉዳይ ላይ በሚመክር ጉባኤ ላይ እንዲገኙ ጋበዙ ።