የዓለም ዜና

የዓለም ዜና

Download on the App Store

የዓለም ዜና episodes

  • የየካቲት 5 ቀን 2017 የዓለም ዜና
    -የኦሮሚያ ክልል ባለሥልጣናት ክልሉን ከተፈናቃዮችና ከርዳታ ነፃ ለማድረግ እየጣሩ መሆኑን አስታወቁ።አማራ ክልል የሚደረገዉ ግጭትና ዉጊያ የሕዝቡን ሕይወትና ሁለንታዊ እንቅስቃሴ ማወኩን የክልሉ መሪ አመኑ።የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ባለሥልጣናት ደግሞ መንገድ መሥሪያ በጀት የለም አሉ።----የሱዳን ተፋላሚ ኃይላት በመጪዉ የሙስሊሞች ቅዱስ ወር ረመዳን ተኩስ እንዲያቆሙ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ያቀረበችዉን ሐሳብ የሱዳን መከላከያ ጦር ዉድቅ አደረገዉ።----የዩናይትድ ስቴትስ መከላከያ ሚንስትር ፔተ ሔግሴት ዩክሬን የኔቶ አባል ትሆን ማለት ከእዉነታዉ የሚቃረን በማለት አጣጣሉት።
    13 min
  • የየካቲት 3 ቀን 2017 ዓ.ም. የዓለም ዜና
    የየካቲት 3 ቀን 2017 ዓ.ም. አርዕስተ ዜና
    የተመድ ፣የሱዳንን ጦር የሚወጋውን የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይልን እርዳታ በማገድ ከሰሰ የድርጅቱ የሱዳን እርዳታ አስተባባሪ እንደተናገሩት ፣ በተለይ በሱዳንዋ ግዛት ዳርፉር የሚገኙ ሰብዓዊ እርዳታ አቅራቢዎች አስፈላጊ የሆኑ እርዳታዎችን ለሚያስፈልጓቸው ሰዎች ማቅረብ አልቻሉም።
    በጋዛ የተኩስ አቁም ቀጣይ ደረጃ ላይ ለመነጋገር ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ዶሀ ኳታር ሄዶ የነበረው የእስራኤል የልዑካን ቡድን ወደ ሀገሩ መመለሱን የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቢሮ አስታወቀ።
    ትራምፕ ወደ አሜሪካን በሚገቡ ብረታ ብረቶች ላይ የ25 በመቶ ቀረጥ እጥላለሁ አሉ።
    11 min
  • የየካቲት 02 ቀን 2017 ዓ ም የዓለም ዜና
    * የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (IMF) ኃላፊ በኢትዮጵያ የተደረጉት የኢኮኖሚ ማሻሻያዎችን አወደሱ ።
    * ሊቢያ፤ 50 የሚጠጉ የስደተኞች አስከሬን ተገኘ
    * የመጀመሪያው የናሚቢያ ፕሬዚዳንት ሳም ኑጆማ በ95 ዓመታቸው አረፉ
    * ዱባይ፤ አትሌት ያለምዘርፍ የኋላው የዱባይ ግማሽ ማራቶን አሸነፈች
    8 min
  • DW Amharic የየካቲት 01 ቀን 2017 የዓለም ዜና
    በምሥራቃዊ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የሚንቀሳቀሱ ሁሉም ታጣቂ ቡድኖች ግጭት እንዲያቆሙ የኬንያ ፕሬዝደንት ጥሪ አቀረቡ። የሱዳን ጦር በኻርቱም ባሕሪ የተባለ አካባቢ መቆጣጠሩን አስታወቀ። በማሊ በሀገሪቱ ጦር እና የሩሲያው ቫግነር ቅጥረኛ ወታደሮች አጀብ የሚጓዝ የተሽከርካሪዎች ቅፍለት ላይ በተፈጸመ ጥቃት 32 ሰዎች ተገደሉ። ሐማስ ሦስት ታጋቾችን፤ እስራኤል 183 ፍልስጤማውያንን በቀይ መስቀል በኩል ተለዋወጡ። ዩክሬን በሩሲያ ኩርስክ ግዛት ጥቃት መጀመሯን ፕሬዝደንት ቮሎዶሚር ዜሌንስኪ አረጋገጡ። ጠቅላይ ሚኒስትር ጀስቲን ቱሩዶ ዶናልድ ትራምፕ ካናዳን ወደ አሜሪካ ለመጠቅለል ያቀረቡት ሐሳብ ተጨባጭ እንደሆነ አስጠነቀቁ።
    10 min
  • የጥር 30 ቀን 2017 ዓ.ም የዓለም ዜና
    አርስተ ዜና፤
    -በዴሞክራቲክ ኮንጎ ጦር እና በሩዋንዳ ይደገፋል በሚባለው የM 23 አማጺዎች መካከል ውጊያው መባባሱ ተነገረ። ኮንጎ በሲቪሎች ላይ ለደረሰው ግድያ እና አስከፊ የሰብአዊ መብቶች ጥሰት የተመድ ሩዋንዳን ተጠያቂ ያድርግልኝ ብላለች። --በአማራ ክልል ምዕራብ ጎንደር ዞን መኪና በማስቆም በተደረገ እገታ አንድ ሰው ተገደለ፤ አራት ደግሞ መቁሰላቸውን የዓይን እማኝ ተናገሩ።--የአሜሪካው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ዓለም አቀፉ የጦር ወንጀል ተመልካች ፍርድ ቤት ላይ የጣሉትን እገዳ በርካታ ሃገራት ተቃወሙ። ትራምፕ የICCን ንብረት በማገድ፤ ባለሥልጣናቱ፣ ሠራተኞቹ እና ቤተሰቦቻቸው ላይ የጉዞ እገዳ ጥለዋል።
    12 min
  • የዓለም ዜና፤ ጥር 29 ቀን 2017 ዓ.ም ሃሙስ
    አርስተ ዜና፤
    የአሜሪካዉ ፕሬዝዳንት ትራምፕ ጾታቸዉን የቀየሩ አትሌቶች፤ በሴቶች የስፖርት ዘርፍ ላይ እንዳይሳተፉ የሚያግድ ትዕዛዝ አስተላለፉ። ትራምፕ እርምጃው "በሴቶች ስፖርት ላይ የሚደረገውን ጦርነት" የሚያበቃ ሲሉ ማድነቃቸዉም ተዘግቧል። -የእስራኤል መከላከያ ሚኒስትር ፍልስጤማውያን ጋዛን ለቀው እንዲወጡ የሚያስችል እቅድ እንዲያዘጋጅ ለጦር ኃይሉ ኃላፊነት መስጠታቸዉ ተመለከተ። የአሜሪካዉ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በፍልስጤም ጋዛ ጉዳይ ማወዛገባቸዉን እንደቀጠሉ ነዉ። ትራምፕ በጋዛ ሰርጥ የእስራኤል እና የሃማዝ ጦርነት ሲጠናቀቅ እስራኤል ጋዛን ለአሜሪካ አሳልፋ ትሰጣለች ማለታቸዉ ተሰምቷል። ሙሉዉን ዜና ያድምጡ!
    12 min
  • የጥር 28 ቀን 2017 ዓ.ም. የዓለም ዜና
    ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ የውጭ እርዳታን ማቆማቸው አፍሪቃ ውስጥ ድንጋጤ አስከትሏል። USAID በአሜሪካም ሆነ በውጪው ለሚገኙ ሠራተኞቹ ከፊታችን ዓርብ ጀምሮ አስተዳደራዊ እረፍት መስጠቱን ይፋ አድርጓል።
    በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን ክልሉን ከትግራይ የሚያገናኘው የብረት ድልድይ ትናንት በደረሰበት ጉዳት አገልግሎት መስጠት ማቋረጡ ተገለጸ።
    ፍልስጤማውያን ከአካባቢው ሳይለቁ ባስቸኳይ ጋዛ መልሶ እንዲገነባ ግብፅ ጥሪ አቀረበች። የፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ጋዛን የማስተዳደር ዕቅድ ከወዲሁ ጠንካራ ትችት ገጥሞታል።
    የዩጋንዳ ፖሊስ የሀገሪቱ ማዕከላዊ ባንክ መረጃ መጠለፉን ተከትሎ ዘጠኝ የፋይናንስ ሚኒስቴር ባለሥልጣናት አሠረ።
    12 min
  • DW Amharic የጥር 27 ቀን 2017 ዓ,ም. የዓለም ዜና
    አርዕስተ ዜና
    -የዩኤስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር፤ ከቻይና በሚገቡ ምርቶች ላይ የተጣለውን 10 በመቶ ታሪፍ ተከትሎ፤ ቻይና የአጸፋ እርምጃ እንደምትወስድ አስታወቀች።
    -የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ኬንያ ያቀረበችበትን ክስ አስተባበለ። ድርጅቱ ማስተባበያ የሰጠዉ፤ የኬንያ ፖሊስ የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊትን በሕገ ወጥ የጦር መሣሪያና አደዛዥ እጽ ዝውወር ብሎም በሰዎች እገታ ክስ መግለጫ ማዉጣቱን ተከትሎ ነዉ።
    -በጎጂ ዞን ሳባ ቦሩ ወረዳ በባህላዊ መንገድ ማዕድን እያወጡ በነበረው ሰዎች ላይ በደረሰው የመሬት መደርመስ የስምንት ሰዎች ሕይወት ማለፉ ተሰማ።
    12 min

About የዓለም ዜና

From the publisher's feed

ዶይቼ ቬለ የዕለቱን ዋና ዋና ዜናዎች ከኢትዮጵያ እና ከመላው ዓለም በየቀኑ ያቀርባል። የኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ፖለቲካዊ እና ኤኮኖሚያዊ ጉዳዮችን ጨምሮ የመላው ዓለምን ውሎ የተመለከቱ ጠቃሚ መረጃዎች በሰባቱም የሣምንቱ ቀናት ከምሽቱ አንድ ሰዓት ከዶይቼ ቬለ ያድምጡ። የዶይቼ ቬለን ዜናዎች በአፕል ፖድካስት…