የዓለም ዜና

የዓለም ዜና

Download on the App Store

የዓለም ዜና episodes

  • የየካቲት 14 ቀን 2017 ዓ.ም. የዓለም ዜና
    ከቀናት በፊት በሰሜን ጎጃም ዞን ጎንጂ ቆለላ ወረዳ በታጣቂዎች ታግተው የነበሩ 13 መምህራን ትናንት መለቀቃቸውን ቤተሰቦችና ጓደኞቻቸው ተናገሩ። ሌሎች ሁለት መምህራን መታገታቸው ተሰምቷል።
    ከመንግሥት ጋር የሰላም ስምምነት ላደረጉ የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት በምህጻሩ ኦነሰ አመራሮች በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ሹመት ተሰጣቸው።
    በሱዳን እና በኬንያ መካከል የዲፕሎማሲ ግንኙነቱ ውጥረት ነግሶበታል። የሱዳን ወታደራዊ መንግሥት ትናንት በኬንያ የሚገኙ የሀገሪቱን አምባሳደር ጠርቷል።
    እስራኤል በሃማስ ታግታ ከነሕጻናት ልጆቿ የተገደለችው እናት አስከሬን እንዲሰጣት ጠየቀች።
    12 min
  • የሐሙስ የካቲት 13 ቀን፣ 2017 ዓ.ም የዓለም ዜና
    *ሰሞኑን ጋምቤላ ክልል፤ ኑዌር ዞን ውስጥ የተከሰተው በሽታ ኮሌራ መሆኑን የክልሉ ጤና ጽ/ቤት ዐሳወቀ ። እስከ ትናንት ምሽት ድረስ በጤና ባለሞያዎች የተረጋገጠ የኮሌራ በሽተኞች ቁጠር 192 መድረሱ ተገልጧል ።
    *ፈረንሣይ የመጨረሻ የጦር ሠፈሯን ለለኮት ዲቯር ዛሬ አስረከበች ። ይህም ፈረንሣይ ለዐሥርተ ዓመታት በምዕራብ አፍሪቃዊቷ አገር የነበራትን ወታደራዊ ይዞታ ሙሉ ለሙሉ እንዲያከትም የሚያደርግ ነው ተብሏል ።
    *ሐማስ በመስከረም 26ቱ ድንገተኛ ጥቃት እሥራኤል ውስጥ ካገታቸው 250 ሰዎች መካከል ሕይወታቸው ያለፉ ሦስት የቤተሰብ አባላትን እና የአንድ አዛውንትን አስክሬን ዛሬ አስረከበ ።
    9 min
  • የየካቲት 11 ቀን 2017 የዓለም ዜና
    -ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) የተመሠረተበት 50ኛ ዓመት ለሁለት ከተከፈሉት የፓርቲዉ አንጃዎች በአንደኛዉ መቀሌ ዉስጥ ተከበረ።ጠቅላይ ሚንስትር ዓብይ አሕመድ በዓሉን ምክንያት በማድረግ መልዕክት አስተላልፈዋል።----የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ጦር በሁለት የደቡባዊ ሱዳን መንደሮች በከፈተዉ ጥቃት በትንሹ 200 ሠላማዊ ሰዎች መግደሉን አንድ የመብት ተሟጋች ቡድን አስታወቀ።----የሩሲያና የዩናይትድ ስቴትስ ዉጪ ጉዳይ ሚንስትሮች ሪያድ-ሳዑዲ አረቢያ ዉስጥ ባደረጉት ዉይይት የዩክሬኑ ጦርነት እንዲያበቃ የሚደራደር የባለሥልጣናት ቡድን ለመሰየምና የአሜሪካና የሩሲያ ግንኙነትን ለማሻሻል ተስማሙ።
    13 min
  • የየካቲት 10 ቀን 2017 ዓ.ም. የዓለም ዜና
    ጋምቤላ ክልል በ4 ወረዳዎች የተከሰተ «ኮሌራ መሰል» በሽታ የዘጠኝ ሰዎችን ሕይወት ቀጠፈ።
    በሶማሊያዋ ፑንትላንድ ከ240 በላይ እራሴን «እስላማዊ መንግሥት» የሚለው ታጣቂ ቡድን አባላት መገደላቸው ተገለጸ።
    የሩሲያው ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን ከፍተኛ ዲፕሎማትና የክሬምሊን አማካሪያቸውን ወደ ሳውድ አረቢያ ላኩ። የዩክሬንን ጦርነት ለማስቆም ለሚካሄደው ውይይት አዲሱ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሮቢዮ ሳውዲ ገብተዋል።
    የዩክሬን ፕሬዝደንት ቮሎድሚር ዘለንስኪ ኪየቭን ያላካተተ ውይይት ውጤት አይኖረውም አሉ።
    የእስራኤል ጦር ዛሬ ደቡባዊ ሊባኖስ ውስጥ ባካሄደው የአየር ድብደባ የሀማስን የጦር አዛዥ መግደሉን አስታወቀ።
    10 min
  • የየካቲት 08 ቀን 2017 የዓለም ዜና
    የጅቡቲ ውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ማሕሙድ አሊ ይሱፍ የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ሆነው ተመረጡ። ናይጄሪያዊው ባለጠጋ አሊኮ ዳንጎቴ የኦሞ ኩራዝ ስኳር ኩባንያን ለማስፋፋት ዕቅድ እንዳላቸው ተገለጸ። በኦሮሚያ ክልል ከመተሐራ ከተማ አቅራቢያ በሬክተር ስኬል 6.0 የተመዘገበ ርዕደ መሬት ተከሰተ። ሐማስ ሦስት ታጋቾች፤ እስራኤል 369 ፍልስጤማውያን እስረኞችን ዛሬ ቅዳሜ በቀይ መስቀል በኩል ተለዋወጡ። አሜሪካ ከዩክሬን ጀርባ ከሩሲያ ጋር ሥምምነት እንዳትፈጽም ፕሬዝደንት ቮሎዶሚር ዜሌንስኪ አስጠነቀቁ። መራኄ-መንግሥት ኦላፍ ሾልስ በጀርመን “ዴሞክራሲ ውስጥ የውጪ ጣልቃ ገብነትን” እንደማይቀበሉ ተናገሩ።
    9 min
  • የዐርብ የካቲት 7 ቀን፣ 2017 ዓ.ም የዓለም ዜና
    አርዕስተ ዜና
    *በአሳሳች የሥራ ዕድል ተታለው ወደ ምያንማር የሄዱ ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ በርካታ የውጭ አገራት ዜጎች ብርቱ ሥቃይ እንደሚደርስባቸው የፈረንሣይ ዜና አገልግሎት ዘገበ ።
    *የኮንጎ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፕሬዚደንት ፌሊክስ ሺሴኬዲ ድጋፍ ፍለጋ ከአገር ውጪ ባሉበት በዛሬው ዕለት በሩዋንዳ የሚደገፈዉ M23 አማፂ ቡድን ሁለት ተጨማሪ ከተሞችን ተቆጣጠረ ።
    *የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬሽ ሱዳን ውስጥ የጦር መሣሪያ ፍሰት እንዲቆም ጥሪ አስተላለፉ ።
    11 min
  • የሐሙስ የካቲት 6 ቀን 2017 ዓ/ም የዓለም ዜና
    DW Amharic- በዛሬው የዓለም ዜና ህወሓትን ለሶስት ወራት ከፖለቲካዊ እንቅስቃሴ መታገዱ፣በአማራ ክልል ዋግኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር 40ሺህ በላይ ሰዎች መፈናቀላቸው፣ሳልሳይ ወያነ ትግራይ የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነትን ያፈራረሙ አካላት ጦርነቱን ተከትሎ ለተፈናቀሉ ዜጎች እንዲደርሱ ጥሪ ማቅረቡ፣ ሱዳን እና ሩሲያ በቀይ ባህር ጠረፍ የጦር ሰፈር ለማቋቋም ስምምነት መድረሳቸው፣በጀርመኗ ሙኒክ ከተማ በተሰበሰበ ሕዝብ መካከል መኪና በመንዳት ቢያንስ 28 ሰዎች መጎዳታቸው፣የሩሲያው ፕሬዚዳንት ብላሚር ፑቲን የሩሲያ ዩክሬን ጦርነትን ለማስቆም ለድርድር ተስማምተዋል ሲሉ ዶናልድ ትራምፕ መግለፃቸው አካቷል።
    12 min

About የዓለም ዜና

From the publisher's feed

ዶይቼ ቬለ የዕለቱን ዋና ዋና ዜናዎች ከኢትዮጵያ እና ከመላው ዓለም በየቀኑ ያቀርባል። የኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ፖለቲካዊ እና ኤኮኖሚያዊ ጉዳዮችን ጨምሮ የመላው ዓለምን ውሎ የተመለከቱ ጠቃሚ መረጃዎች በሰባቱም የሣምንቱ ቀናት ከምሽቱ አንድ ሰዓት ከዶይቼ ቬለ ያድምጡ። የዶይቼ ቬለን ዜናዎች በአፕል ፖድካስት…