የዓለም ዜና

የዓለም ዜና

Download on the App Store

የዓለም ዜና episodes

  • የጥር 25 ቀን 2017 ዓ ም የዓለም ዜና
    * የጅቡቲ የድሮን ጥቃት
    * በዩናይትድ ስቴትስ ጦር እገዛ ሶማሊያ ውስጥ ቢያንስ 46 አሸባሪዎች ተገደሉ
    * ሀገር አቀፍ ሰልፎች በጀርመን ተካሄዱ
    *ካናዳ፣ ሜክሲኮ እና ቻይና በየዩናይትድ ስቴትሱ ግብር ላይ እርምጃ እንወስዳለን አሉ
    *ቤንጃሚን ኔታንያሁ ለሁለተኛው ዙር የተኩስ አቁም ድርድር ወደ ዩናይትድ ስቴትስ አቀኑ
    8 min
  • DW Amharic የጥር 24 ቀን 2017 የዓለም ዜና
    ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በኢትዮጵያ “አሁን ያለውን የፖለቲካ ጩኸት እንዳትመለከቱ” የሚል ጥሪ ለብልጽግና ፓርቲ አባላት አቀረቡ። የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይል በኦምዱርማን በገበያ ላይ በከባድ መሣሪያ በፈጸመው ድብደባ 54 ሰዎች መገደላቸውን የሱዳን መንግሥት አስታወቀ። ኤርትራ፣ ግብጽ እና ሶማሊያን ጨምሮ ቻይና ከበርካታ የአፍሪካ፣ የአውሮፓ እና የእስያ ሀገራት እንስሳት ወደ ሀገሯ እንዳይገቡ አገደች። የአረብ ሀገራት የአሜሪካው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ፍልስጤማውያንን ወደ ግብጽ እና ዮርዳኖስ ለማዘዋወር ያቀረቡትን ሐሳብ ውድቅ አደረጉ። ዛሬ ቅዳሜ ሐማስ ሦስት ታጋቾች እስራኤል 183 ፍልስጤማውያን እስረኞችን ለቀዋል።
    10 min
  • የጥር 23 ቀን 2017 ዓ.ም. የዓለም ዜና
    የጥር 23 ቀን 2017 ዓ.ም. አርዕስተ ዜና
    የኦሮሚያ ክልል የሰላሌ ወረዳ ነዋሪዎች በአካባቢያቸው በግጭቱ ምክንያት ሕይወታቸው ለአደጋ መጋለጡን ለዶቼቬለ ተናገሩ ።
    የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ የBRICS አባል ሐገራት የአሜሪካዉን ዶላር ትተዉ በሌላ ገንዘብ ለመገበያየት ከወሰኑ ለዩናይትድ ስቴትስ ገበያ በሚያቀርቡት ሸቀጦቻቸዉ ላይ የ100% የቀረጥ ጭማሪ ለማድረግ ዛቱ።
    የጀርመን ወግ አጥባቂ እሕትማማች ፓርቲዎች የክርስቲያን ዴሞክራት ሕብረት (CDU)ና የክርስቲያን ሶሻል ሕብረት (CSU) አዲስ ያረቀቁት ስደተኞችን የሚያግድ ሕግ የሐገሪቱን ፖለቲከኞች እያሟገተ ነው።
    11 min
  • የጥር 22 ቀን 2017 የዓለም ዜና
    በማጭበርበር ወንጀል የተከሰሱት ቀሲስ በላይ መኮንንና ሁለት ተባባሪዎቻቸዉ ከ3 እስከ 5 ዓመት በሚደርስ ፅኑ እስራትና በገንዘብ እንዲቀጡ የኢትዮጵያ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ወሰነ።----የአማራ ክልል የገቢዎች መሥሪያ ቤት ሠራተኞች በተደጋጋሚ የጠየቁት የደሞዝ ጭማሪ እስካሁን እንዳልተከፈላቸዉ አስታወቁ።-----ዩናይትድ ስቴትስ ርዕሠ ከተማ ዋሽግተን አጠገብ አንድ የመንገደኞች አዉሮፕላንና አንድ የጦር ሔሊኮፕተር ተጋጭተዉ በርካታ ሰዎች ሞቱ።የአደጋ ሠራተኞች እንዳሉት በአደጋዉ ሁለት የሩሲያ እዉቅ አትሌቶችን ጨምሮ ከስልሳ በላይ ሰዎች ሳይሞቱ አልቀሩም።
    12 min
  • DW Amharic የጥር 17 ቀን 2017 የዓለም ዜና
    የትግራይ ክልል የሰላም እና ጸጥታ ቢሮ ከፍተኛ የትግራይ ወታደራዊ መኮንኖች የሰጡትን መግለጫ እና የያዙት አቋም “በመደገፍም ሆነ በመቃወም” ሰልፍ ማካሔድ እንደማይቻል አስታወቀ። ኢትዮጵያ በኬንያ በኩል 100 ሜጋ ዋት ኤሌክትሪክ ለታንዛኒያ የምትሸጥበት ሥምምነት መጠናቀቁን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታወቀ። በሱዳን ዳርፉር ግዛት ኤል-ፋሽር በሚገኝ ሆስፒታል ላይ በሰው አልባ አውሮፕላን በተፈጸመ ጥቃት 30 ሰዎች ሲገደሉ በርካቶች ቆሰሉ። ሦስት የደቡብ አፍሪካ ሰላም አስከባሪዎች በዴሞክራቲት ሪፐብሊክ ኮንጎ ተገደሉ። በጋዛ የተኩስ አቁም ሥምምነት መሠረት እስራኤል 200 ፍልስጤማውያን እስረኞችን፤ ሐማስ 4 ታጋቾችን ዛለቀቁ።
    9 min
  • የጥር 16 ቀን 2017 ዓ.ም. የዓለም ዜና
    ባለፉት ሦስት ወራት ውስጥ በአማራ እና ኦሮሚያ ክልልሎች በመንግሥት እና በታጣቂ ኃይሎች ከ167 በላይ ሰዎች መገደላቸውን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን አስታወቀ።
    የአፋር ክልልን ከኦሮሚያ ክልል ጋር በሚያዋስነው አካባቢ በድጋሚ ከፍተኛ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከሰተ።
    የዲላ ዩኒቨርሲቲ ሴት የእስልምና እምነት ተከታይ ተማሪዎች ሂጃብ እና ኒቃብ ለብሰው ወደ ግቢ መግባት በመከልከላቸው በመስጂዶች ለማደር ተገደናል አሉ።
    ኤየዊን የተሰኘው ኃያል ወጀብና ንፋስ በሚሊየኖች የሚቆጠሩ የአየርላንድና የሰሜን ብሪታንያ ነዋሪዎች ከቤታቸው እንዳይወጡ አደረገ።
    11 min

About የዓለም ዜና

From the publisher's feed

ዶይቼ ቬለ የዕለቱን ዋና ዋና ዜናዎች ከኢትዮጵያ እና ከመላው ዓለም በየቀኑ ያቀርባል። የኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ፖለቲካዊ እና ኤኮኖሚያዊ ጉዳዮችን ጨምሮ የመላው ዓለምን ውሎ የተመለከቱ ጠቃሚ መረጃዎች በሰባቱም የሣምንቱ ቀናት ከምሽቱ አንድ ሰዓት ከዶይቼ ቬለ ያድምጡ። የዶይቼ ቬለን ዜናዎች በአፕል ፖድካስት…