የዓለም ዜና

የዓለም ዜና

Download on the App Store

የዓለም ዜና episodes

  • DW Amharic የጥር 05 ቀን 2017 የዓለም ዜና
    የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ መንግሥት “የሲቪክ ምኅዳሩን የሚያጠቡ እርምጃዎች ከመዉሰድ በመቆጠብ በኢትዮጵያ ሕገ-መንግሥት በተደነገገው መሠረት ለመደራጀት መብት ያለውን ቁርጠኝነት እንዲያረጋግጥ” 50 የመብቶች ተሟጋች ድርጅቶች ጠየቁ። በጦርነት ከቀያቸው ተፈናቅለው በትግራይ ክልል መቐለ ከተማ የተጠለሉ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች የተቃውሞ ሰልፍ አካሔዱ። በናይጄሪያ ራሱን እስላማዊ መንግሥት ብሎ ከሚጠራው ታጣቂ ቡድን የወገኑ ኃይሎች በፈጸሙት ጥቃት ቢያንስ 40 ገበሬዎች መገደላቸውን የሀገሪቱ ባለሥልጣናት ተናገሩ። ቃጣር የጋዛን ጦርነት ለማብቃት የተዘጋጀ ሥምምነት የመጨረሻ ረቂቅ ለእስራኤል እና ለሐማስ ተደራዳሪዎች አቀረበች።
    10 min
  • የጥር 4 ቀን 2017 ዓ ም የዓለም ዜና
    ለአንድ ዓመት ገደማ ከዘለቀ ውጥረት በኋላ ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸውን ወደነበረበት ለመመለስ እና ለማጠናከር ተስማሙ።
    የሱዳን ጦር ወሳኝ እና ስልታዊ ያለውን የዋድ ማዳኒ ከተማን መልሶ መቆጣጠሩን አስታቀወ።
    ጀርመን 50 ሚሊዮን ዩሮ ተጨማሪ ድጋፍ ለሶሪያ እንደምትሰጥ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አናሌና ቤርቦክ በሳዑዲ አረቢያ ዋና ከተማ ሪያድ በተሳተፉበት ጉባኤ ላይ ዛሬ ተናገሩ።
    በዩናይትድ ስቴትሷ ሎስ አንጀለስ ከተማ እና አካባቢዋ የተከሰተው ሰደድ እሳት የሟቾች ቁጥር ወደ 16 ከፍ ብሏል።
    የንጋፋው ፖለቲከኛና የምጣኔ ሐብት ባለሙያ አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ስርዓተ ቀብር ዛሬ ተፈፀመ።
    9 min
  • የዓለም ዜና፤ ጥር 1 ቀን፤ 20217 ዓ.ም ሃሙስ
    DW Amharic አርስተ ዜና --የትግራይ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት፣ በአክሱም ከተማ ትምህርት ቤቶች ሴት ሙስሊም ተማሪዎች ሂጃብ እንዳይለብሱ የከተማዋ ትምህርት ቢሮ የጣለውን እገዳ ለማስነሳት ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት መውሰዱን አስታወቀ።-የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት የነዳጅ ውጤቶች ግብይት ሥርዓትን የሚደነግግ አዋጅ አፀደቀ፡፡ ምንጩ ያልታወቀ ሀብትን ለመንግስት ለማስመለስ ያስችላል የተባለም አዋጅም ጸደቋል። የንብረት ማስመለስ አዋጅ "የፖለቲካ ማጥቂያ መሣሪያ እንዳይሆን" ተጠይቋል። በጀርመን ውስጥ ከግማሽ ሚሊዮን የሚበልጡ ሰዎች ቤት አልባ ናቸው ሲል የጀርመን ፌደራል መንግስት አኃዛዊ መረጃ ተቋም ይፋ አደረገ።
    11 min
  • የታኅሳስ 30 ቀን 2017 የዓለም ዜና
    -በደቡብ ኢትዮጵያ ኮሬ ዞን፣ ጎርካ ወረዳ ታጣቂዎች ሁለት ገበሬዎችን በጥይት ደብደዉ፣ በገጀራ ተልትለዉ ገደሉ።የኮሬ ዞን ባለሥልጣናት ገዳዮቹን ከአጎራባች ወረዳ የገቡ «ፀረ-ሠላም» ኃይላት ብለዋቸዋል።በዞኑ ታጣቂዎች በተደጋጋሚ ሰላማዊ ሰዎችን ይገድላሉ።-----ዩናይትድ ስቴትስ የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ሠራዊት አዛዥ ጄኔራል መሐመድ ሐምዳን ዳግሎ (ሕምዲቲ)ና ቤተሰቦቻቸዉ አሜሪካ እንዳይገቡ አገደች---የዩናይትድ ስቴትስ ተመራጭ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ የፓናማ ቦይን፣የዴንማርክን ግሪንላንድንና ካናዳን በኃይል ጭምር ለመያዝ መዛታቸዉ የአዉሮጳና የአሜሪካ መንግሥታትን አስደግጧል።
    11 min
  • የታህሳስ 27 ቀን 2017 የዓለም ዜና
    የሱዳን የሰላም ተስፋ
    እስራኤል በጋዛ ባካሄደችው ጥቃት በአለፉት 24 ሰዓታት 88 ፍልስጤማውያን መገደላቸውን
    ዩክሬይን የሩስያ ግዛት በሆነችው የክርሱክ ግዛት ዛሬ መጠነሰፊ የመልሶ ማጥቃት ማካሄዷን
    9 min
  • DW Amharic የታኅሳስ 26 ቀን 2017 የዓለም ዜና
    የመሬት መንቀጥቀጥ ካሰጋቸው በአፋር እና በኦሮሚያ ክልሎች የሚገኙ ቀበሌዎች ከ14,000 በላይ ሰዎች ወደ ሌላ ቦታ መዘዋወራቸውን የኢትዮጵያ መንግሥት አስታወቀ። ባለፉት 15 ገደማ ሰዓታት አምስት የመሬት መንቀጥቀጦች መከሰታቸውን ጉዳዩን የሚከታተሉ የአውሮፓ እና የአሜሪካ የምርምር ተቋማት መዝግበዋል። ከ9 ሚሊዮን በላይ የኢትዮጵያ ልጆች ከትምህርት ቤት ውጪ መሆናቸውን ናቸው። የናይጄሪያ ታጣቂዎች አምስት የካሜሩን ወታደሮች ሁለቱ ሀገሮች በሚዋሰኑበት ድንበር አካባቢ ገደሉ። እስራኤል በጋዛ በፈጸመቻቸው የአየር ጥቃቶች 62 ሰዎች ተገደሉ። ዩክሬን በአሜሪካ ሠራሽ ሚሳይል ጥቃት ሞከረች ያለችው ሩሲያ እንደምትበቀል ዛተች
    7 min

About የዓለም ዜና

From the publisher's feed

ዶይቼ ቬለ የዕለቱን ዋና ዋና ዜናዎች ከኢትዮጵያ እና ከመላው ዓለም በየቀኑ ያቀርባል። የኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ፖለቲካዊ እና ኤኮኖሚያዊ ጉዳዮችን ጨምሮ የመላው ዓለምን ውሎ የተመለከቱ ጠቃሚ መረጃዎች በሰባቱም የሣምንቱ ቀናት ከምሽቱ አንድ ሰዓት ከዶይቼ ቬለ ያድምጡ። የዶይቼ ቬለን ዜናዎች በአፕል ፖድካስት…