የዓለም ዜና

የዓለም ዜና

Download on the App Store

የዓለም ዜና episodes

  • የሐሙስ ጥር 15 ቀን 2017 ዓ.ም. የዓለም ዜና
    የሐሙስ ጥር 15 ቀን 2017 ዓ.ም. አርዕስተ ዜና
    በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሥልጤ ዞን ሁልባራግ ወረዳ ሌፎ በተባለ አካባቢ ዛሬ ረፋድ በደረሰ የመኪና አደጋ የ8 ሰዎች ህይወት አለፈ ፡፡
    የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከዚህ ቀደም ወደ ዩናይትድ ስቴትስ እንዲገቡ የተፈቀደላቸውን ጨምሮ ሌሎች ስደተኞችም ወደ አሜሪካን እንዳይገቡ ያስተላለፉት ትዕዛዝ ከፊታችን ሰኞ አንስቶ ተግባራዊ ይሆናል።
    ሱዳን ውስጥ በደቡብ ሱዳናውያን ላይ ተፈጽሟል ስለተባለው ግድያ በማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች የወጡ ቪድዮዎች ብጥብጥና የበቀል ጥቃት ካስከተሉ በኋላ የደቡብ ሱዳን ባለሥልጣናት ማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎችን አገዱ
    10 min
  • የጥር 14 ቀን 2017 የዓለም ዜና
    -የደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የቤንዚን እጥረትና ሽያጭን ለመቆጣጠር በክልሉ ቤንዚን በኩፖንና በቁነና እንዲሸጥ ወሰነ።የኢትዮጵያ መንግስት በነዳጅ ዘይት ዋጋ ላይ በተደጋጋሚ የጣለዉ የዋጋ ጭማሪና የተከሰተዉ እጥረት የአብዛኛዉን ኢትዮጵያዊ ኑሮና እንቅስቃሴ እያወከ ነዉ።---ኢትዮጵያዉያን ስደተኞችን አሳፍራ ከጅቡቲ ወደ የመን ትቀዝፍ የነበረች አንዲት አነስተኛ ጀልባ ተገልብጣ 20 ኢትዮጵያዉያን ስደተኞች ሞቱ።---የአዲሱ የዩናትድ ስቴትስ ፕሬዝደንት የዶናልድ ትራምፕ መርሕ ያሰጋቸዉ የአዉሮጳ መሪዎች መፍትሔ ፍለጋ እየባተሉ ነዉ።
    12 min
  • የዓለም ዜና፤ ጥር 13 ቀን 2017 ዓ.ም ማክሰኞ
    DW Amharic አርስተ ዜና
    --የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ "የአሜሪካ ውድቀት አብቅቷል" አሉ። ትራምፕ የአሜሪካ ወርቃማ ጊዜ ዛሬ ጀምሯል፤ የአሜሪካ ማሽቆልቆል ያበቃል ብለዋል።ትራምፕ ከሳቸው በፊት የነበረውን የጆ ባይደንን አስተዳደር በጠንካራዉ ተችተዋል። በሌላ በኩል አገራቸዉ ከዓለም ጤና ድርጅት (WHO) ትወጣለች ማለታቸዉ ብዞዎችን አስገርሟል።--በአክሱም ከተማ ሴት ሙስሊም ተማሪዎች ሒጃብ መልበስ ክልከላን የሚቃወም ሰላማዊ ሰልፍ ዛሬ በመቐለ ተካሄደ።--በብራዚል እና በቬትናም የተከሰተዉ ድርቅ በዓለም ላይ የቡና ዋጋን በእጅጉ ሊያንር፤ ምርቱም አነስተኛ ሊሆን እንደሚችል ተነገረ።
    ዝርዝሩን ያድምጡ!
    13 min
  • የጥር 12 ቀን 2017 ዓ.ም. የዓለም ዜና
    በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን መንዝ ላሎ ምድር ወረዳ የሚገኙ መምህራንና ሌሎች ሠራተኞች ለአራት ወራት ደመወዝ እንዳላገኙ አመለከቱ። የወረዳው የመንግሥት ኮሚኖኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት በወረዳው 1300 የሚሆኑ የመንግሥት ሠራተኞች ለችግር መጋለጣቸውን ገልጿል።
    ኦክስፋም የተሰኘው የረድኤት ድርጅት የቢሊየነሮች ሀብት በፍጥነት እያደገ ሊሄድ ይችላል አለ። ድርጅቱ እንደሚለው ከዓለም ሀብት 45 በመቶ የሚሆነው ከዓለም ሕዝብ አንድ በመቶ ብቻ በሚሆኑት ቱጃሮች እጅ ነው።
    የዩናይትድ ስቴትስ ተመራጭ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ በዛሬው ዕለት ቃለመሐላ በመፈጸም በይፋ ሥራቸውን እንደሚጀምሩ እየተጠበቀ ነው።
    11 min
  • DW Amharic የጥር 10 ቀን 2017 የዓለም ዜና
    የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት የሥራ አስፈጻሚ ቦርድ የኢትዮጵያን የተራዘመ የብድር አቅርቦት ሁለተኛ ግምገማ አጸደቀ። የኬንያው ፕሬዝደንት ዊሊያም ሩቶ ከኢትዮጵያ የሥለላ ኃላፊ ሬድዋን ሑሴን ተገናኝተው በአፍሪካ ቀንድ የጸጥታ ጉዳይ ላይ ተወያዩ። በአማራ እና በኦሮሚያ ክልሎች እየተካሔዱ በሚገኙ ግጭቶች የኢትዮጵያ መንግሥት ኃይሎች የሚወስዷቸው እርምጃዎች አሳሳቢ መሆናቸውን በአሜሪካ የውጪ ጉዳይ መሥሪያ ቤት የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ሚኒስትር ሞሊ ፊ ተናገሩ። በናይጄሪያ ዛሬ ቅዳሜ የነዳጅ ማመላለሻ ቦቴ ላይ በደረሰ አደጋ ቢያንስ 60 ሰዎች ተገደሉ። የጋዛ ተኩስ አቁም እሁድ ተግባራዊ ይሆናል ተባለ።
    9 min
  • የዓርብ ጥር 9 ቀን 2017 ዓ.ም. የዓለም ዜና
    የአርብ ጥር 9 ቀን 2017 ቀን ዐርዕስተ ዜና
    በኢትዮጵያ የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ የኑሮውን ጫና ማክበዱን ዶቼቬለ ከተለያየ የሀገሪቱ አካባቢዎች የጠየቃቸው ሰዎች ተናገሩ።
    የሱዳን ጦር ኃይል ዩናይትድ ስቴትስ በሱዳኑ መሪ አብዱልፈታህ አል ቡርሀን ላይ የጣለችውን ማዕቀብ ኢፍትሀዊ ሲል አወገዘ።
    የእስራኤል የደኅንንት ካቢኔ እስራኤልና ሀማስ ሐሙስ ማታ የተስማሙበትን የተኩስ አቁምና ታጋቾችን የመልቀቅ ስምምነት ዛሬ አጸደቀ። አጠቃላዩ ካቢኔ ዛሬ ማምሻውን ስምምነቱን ያጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል
    9 min
  • የጥር 7 ቀን 2017 ዓ.ም. የዓለም ዜና
    ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አፍሪካ ሕብረት ቅርንጫፍ ከ6 ሚሊየን ዶላር በላይ «በሀሰተኛ ሰነድ» ለማውጣት ሙከራ እድርገዋል በሚል የሙስና እና ከባድ የማታለል ወንጀል ተጠርጥረው የተከሰሱት እነ ቀሲስ በላይ መኮንን ጥፋተኛ ተባሉ።
    የአክሱም ከተማ ወረዳ ፍርድቤት አምስት የከተማዋ ትምህርት ቤቶች በሴት ሙስሊም ተማሪዎች ላይ የጣሉት ክልከላ ታግዶ እንዲቆይ ወሰነ።
    ዴሞክራቲክ ኮንጎ ውስጥ ወርቅ እና በርካታ ገንዘብ በሕገወጥ መንገድ ይዘዋል በሚል የተከሰሱ ሦስት ቻይናውያን ሰባት ዓመት እስራት ተፈረደባቸው።
    ከሥልጣናቸው በግዳጅ እንዲነሱ ግፊት የተደረገባቸው የደቡብ ኮርያ ፕሬዝደንት ታሠሩ።
    11 min
  • የጥር 6 ቀን 2017 የዓለም ዜና
    -የአፋር ክልልን በመታዉ የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ ከቤት ንብረታቸዉ የተፈናቀሉ ሰዎች በቂ ዕርዳታ እንዳላገኙ አስታወቁ።በመሬት መንቀጥቀጡ ከተጎዱ አካባቢዎች ከ60 ሺሕ በላይ ሰዎች ተፈናቅለዋል።ተፈናቃዮቹና ርዳታ አቀባዮች እንደሚሉት የምግብ፣የመድሐኒትና የመጠለያ ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል።----የሶማሊያ የፀጥታ ኃይላት በሐገሪቱ ሰሜናዊ ግዛት ሸምቀዉ ነበር ያሏቸዉን የእስላማዊ መንግስት (IS) ታጣቂዎች መግደላቸዉን አስታወቁ።-የእስራኤልና የሐማስ ተደራዳሪዎች ጋዛን የሚያወድመዉን ጥቃት ለማቆምና ታጋቾችን ለመልቀቅ የሚረዳ ስምምነት ለማድረግ መቃረባቸዉ እየተነገረ ነዉ።
    11 min

About የዓለም ዜና

From the publisher's feed

ዶይቼ ቬለ የዕለቱን ዋና ዋና ዜናዎች ከኢትዮጵያ እና ከመላው ዓለም በየቀኑ ያቀርባል። የኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ፖለቲካዊ እና ኤኮኖሚያዊ ጉዳዮችን ጨምሮ የመላው ዓለምን ውሎ የተመለከቱ ጠቃሚ መረጃዎች በሰባቱም የሣምንቱ ቀናት ከምሽቱ አንድ ሰዓት ከዶይቼ ቬለ ያድምጡ። የዶይቼ ቬለን ዜናዎች በአፕል ፖድካስት…