የዓለም ዜና

የዓለም ዜና

Download on the App Store

የዓለም ዜና episodes

  • የታኅሳስ 25 ቀን 2017 የዓለም ዜና
    -ኢትዮጵያ የሶማሊያን ሠላም ለማስከበር አዲስ ተልዕኮ ከተቀበለዉ የአፍሪቃ ሕብረት ሠራዊት ጋር እንደምትተባበር አስታወቀች።የኢትዮጵያ ዉጪ ጉዳይ ሚንስቴር የኢትዮጵያን ዕቅድ ይፋ ያደረገዉ የኢትዮጵያ መከላከያ ሚንስትር ከሶማሊያ ፕሬዝድንትና ከሌሎች ባለሥልጣናት ጋር ትናንት ከተነጋገሩ በኋላ።----ኢትዮጵያ ዉስጥ የአፋር ክልልን በተከታታይ የመታዉ የመሬት መንቀጥቀጥ እሳተ ጎሞራ ሳያፈነዳ እንዳልቀረ ተነገረ።-----ጀርመንና ፈረንሳይ ለአዲሶቹ የሶሪያ ባለሥልጣናት ድጋፍ እንደሚሰጡ የሁለቱ ሐገራት ዉጪ ጉዳይ ሚንስትሮች አስታወቁ።ሁለቱ ዉጪ ጉዳይ ሚንስትሮች ደማስቆ ዉስጥ ከአዳዲሶቹ የሶሪያ መሪዎች ጋር ተነጋግረዋል።ዜናዉ በዝርዝር።
    14 min
  • የታኅሣሥ 24 ቀን 2017 ዓ.ም. የዓለም ዜና
    የኢትዮጵያ የመከላከያ ሚኒስትር አይሻ መሐመድ ወደ ሶማሊያ መጓዛቸው ተነገረ። የመቃዲሹ ከፍተኛ ባለሥልጣን መረጃውን ቢያረጋግጡም ለምን ጉዳይ የሚለውን ግን እንዳልገለጹ ሮይተርስ አመልክቷል።
    ማዕከላዊ ቱኒዚያ አቅራቢያ ስደተኞችን የጫኑ ሁለት ጀልባዎች በደረሰባቸው አደጋ 27ቱ መሞታቸውን ባለሥልጣናት ዛሬ አስታወቁ። 83ቱን ማትረፍ ተችሏል። ያልተገኙ እንዳሉ በሚል ፍለጋው ቀጥሏል።
    ደቡብ ኮርያ የሀገሪቱን ፕሬዝደንት የሚደግፉና የሚቃወሙ ዜጎችን ሰልፍ ስታስተናግድ ዋለች።
    በጎርጎሪዮሳዊው አዲስ ዓመት በዩናይትድ ስቴትስ የተለያዩ ግዛቶች የደረሱ ጥቃቶች ከሽብር ጋር ግንኙነት እንዳላቸው እየተመረመረ ነው።
    11 min
  • DW Amharic የታኅሳስ 23 ቀን 2017 የዓለም ዜና
    ኢትዮጵያ በጠና የታመሙ ሰዎች “የአንጎል ሞት ሲረጋገጥ” በመሣሪያ ላይ ብቻ የተመሠረተ ሰው ሠራሽ የአተነፋፈስ ዕገዛ ማቋረጥን የሚፈቅድ ሕግ አጸደቀች። የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር ሁለት የአምቡላንስ ሾፌሮች በኦሮሚያ እና በአማራ ክልሎች በተፈጸመባቸው ጥቃቶች ቆሰሉ። የዋጋ ግሽበት “ከፍተኛ እና በመካከለኛ ጊዜ ሊደረስበት ከታሰበው የባለ አንድ አኃዝ ግብ በላይ መሆኑን” የብሔራዊ ባንክ የገንዘብ ፖሊሲ ኮሚቴ ገለጸ። የአፍሪካ ኅብረት የድጋፍ እና ማረጋጋት የሶማሊያ ተልዕኮ (AUSSOM) በይፋ ሥራ ጀመረ። የአይቮሪ ኮስት ፕሬዝደንት አላሳን ዋታራ የፈረንሳይ ወታደሮች በዓመቱ መጨረሻ ከሀገራቸው ለቀው እንደሚወጡ አስታወቁ።
    10 min
  • የታኅሣሥ 21 ቀን 2017 ዓ.ም. የዓለም ዜና
    በሲዳማ ክልል በደረሰ የመኪና አደጋ የ71 ሰዎች ሕይወት አለፈ። የተጎዱም አሉ። አደጋው የደረሰው ትናንት ነው።
    ኬንያ ውስጥ መንግሥትን የሚተቹ ወጣት ዜጎች ላይ ያነጣጠረ እገታ እንዲቆም ለተቃውሞ አደባባይ የወጡ በርካቶች ታሠሩ።
    የወንጀል ድርጊት በመጨመሩ ምክንያት ትሪኒዳድና ቶቤጎ ውስጥ የአስቸኳይ ጊዜ ታወጀ።
    39ኛው የአሜሪካ ፕሬዝደንት ጂሚ ካርተር ትናንት ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ። መቶ ዓመታቸው
    11 min
  • የታኅሳስ 19 ቀን 2017 የዓለም ዜና
    የተመ የጸጥታ ጥበቃ ምክር ቤት የአፍሪካ ኅብረት የድጋፍ እና ማረጋጋት የሶማሊያ ተልዕኮን አጸደቀ። ኢትዮጵያ ከአትሚስ ወደ አዲሱ ተልዕኮ የሚደረገው ሽግግር “ስኬታማ የሚሆነው የሶማሊያ የጸጥታ ኃይሎች ሙሉ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ከተጠናከሩ ብቻ ነው” ብላለች። ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ በኬንያ የተስፋፋውን የግለሰቦች አፈና ለማቆም ቃል ገቡ። የእስራኤል ጦር በሰሜን ጋዛ ሥራ ላይ ከነበሩ የመጨረሻዎቹ ሆስፒታሎች የአንዱን ዳይሬክተር ማሰሩን የጋዛ የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ። የአዘርባጃን አየር መንገድ አውሮፕላን መከስከስ በፍጥነት እና በገለልተኝነት እንዲመረመር የአውሮፓ ኅብረት የውጪ ጉዳይ ኃላፊ ካያ ካላስ ጥሪ አቀረቡ።
    11 min
  • የታኅሣሥ 17 ቀን 2017 ዓ.ም. የዓለም ዜና
    መንግሥት ሁለት የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶችን አገደ። የታገዱት የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ጉባኤ (ኢሰመጉ) እና የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች ማዕከል ናቸው።
    እስራኤል እና ሃማስ አንዳቸው ሌላቸውን የጋዛን የተኩስ አቁም ውይይት በማደናቀፍ እየከሰሱ ነው።
    አዘርባጃን በአውሮፕላን አደጋ ለሞቱት 38 ሰዎች በዛሬው ዕለት ብሔራዊ ሀዘን አወጀች። የዛሬ 20 ዓመት ኢንዶኔዢያ ላይ በደረሰው የሱናሚ አደጋ ያለቁት ከ200 ሺህ በላይ ሰዎች በጸሎትና በሻማ ማብራት ታስበዋል።
    ዩክሬን በተደጋጋሚ በምዕራባውያን ሚሳኤል እና ሰው አልባ አውሮፕላን ሲቪሎችን ኢላማ በማድረግ ላደረሰችው ጥቃት ምላሽ እንደምትሰጥ ሩሲያ አስታወቀች።
    12 min

About የዓለም ዜና

From the publisher's feed

ዶይቼ ቬለ የዕለቱን ዋና ዋና ዜናዎች ከኢትዮጵያ እና ከመላው ዓለም በየቀኑ ያቀርባል። የኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ፖለቲካዊ እና ኤኮኖሚያዊ ጉዳዮችን ጨምሮ የመላው ዓለምን ውሎ የተመለከቱ ጠቃሚ መረጃዎች በሰባቱም የሣምንቱ ቀናት ከምሽቱ አንድ ሰዓት ከዶይቼ ቬለ ያድምጡ። የዶይቼ ቬለን ዜናዎች በአፕል ፖድካስት…