የዓለም ዜና

የዓለም ዜና

Download on the App Store

የዓለም ዜና episodes

  • የታኅሳስ 5 ቀን 2017 ዓ.ም. የዓለም ዜና
    ኢትዮጵያዊ ባለሀብት በደቡብ ሱዳን ታጣቂዎች ጋምቤላ ክልል ተገደሉ፤
    የCOP16 ጉባኤ ያለ አርኪ ውጤት ተጠናቀቀ፤
    የጀርመኑ ፕሬዚዳንት የአራት ቀናት የአፍሪቃ ጉዟቸውን አጠናቀቁ፤
    የጀርመን መራኄ መንግሥት ኦላፍ ሾልስ ፓርቲያቸው በዋና እጩነት መረጣቸው፤
    የድንበር የለሽ የሀኪሞች ቡድን መርከብ ስራ ለማቆም ተገደደች፤
    የደቡብ ኮሪያው ፕሬዝዳንት ዩን ከስልጣን እንዲወርዱ የሀገሪቱ ምክር ቤት ወሰነ
    11 min
  • የአርብ ታኅሳስ 4 ቀን 2017 ዓ.ም. የዓለም ዜና
    የአርብ ታኅሳስ 4 ቀን 2017 ዓ.ም. አርዕስተ ዜና
    ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ በመካከላቸው የተፈጠረውን ውዝግብ ለመፍታት «ቴክኒካዊ ውይይት» ለማድረግ መስማማታቸውን የአፍሪቃ ኅብረት ፣ኢጋድ ፣ዩናይትድ ስቴትስና የተመድ አወደሱ ።
    አምነስቲ ኢንተርናሽናል የሱዳን ጦር ሕዝብ በብዛት በተሰበሰበበት የገበያ ስፍራ የፈጸመው የአየር ጥቃት ግልፅ የጦር ወንጀል ነው አለ።
    ተመራጩ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ዩክሬን ዩናይትድ ስቴትስ በሰጠቻት የጦር መሣሪያዎች በሩስያ ምድር የሚገኙ ዒላማዎችን እንድትመታ እንደማይፈቅዱ ተናገሩ።
    10 min
  • የሐሙስ ታኅሣሥ 3 ቀን፣ 2017 ዓ.ም የዓለም ዜና
    *በቱርክ ፕሬዝዳንት ረቺብ ጣይብ ኤርዶኻን አሸማጋይነት አንካራ ውስጥኢትዮጵያ እና ሶማሊያ በመካከላቸው የተፈጠረውን ውዝግብ ለለመፍታት «ቴክኒካዊ ውይይት» ለማድረግ መስማማታቸው ተገለጠ ።
    *ከአንድ ዓመት የእስር ጊዜ በኋላ ባለፈው ሳምንት የተለቀቁት የቀድሞ የሰላም ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ታዬ ደንደዓ ዛሬ ለመጀመሪያ ጊዜ ከማረሚያ ቤት ውጪ በራሳቸው ፍርድ ቤት ቀረቡ ።
    *የራስ ገዟ ሶማሊላንድ አዲስ ፕሬዚደንት አብዲራሕማን ሞሐመድ አብዱላሂ ዛሬ ሀርጌሳ ውስጥ ቃለ መሐላ ፈጸሙ ።
    *ሣዑዲ ዓረቢያ እንደ ጎርጎሪዮስ አቆጣጠር በ2034 የዓለም ዋንጫን ለማስተናገድ ተመረጠች ።
    10 min
  • የዓለም ዜና፤ ታህሳስ 1 ቀን፤ 2017 ዓ.ም
    አርስተ ዜናዎች፤
    --የእስራኤል ጠ/ሚ ቤንያሚን ኔታንያሁ ለተጠረጠሩባቸው ክሶች የምስክር ቃላቸዉን ሰጡ። ኔታንያሁ ዛሬ በቴል አቪቭ በአንድ በህዝብ የተጨናነቀ ፍርድ ቤት በሰጡት የመክፈቻ ምስክርነት ቃል የእስራኤልን ጥቅሞች የሚጠብቁ ታማኝ መሪና ጠባቂ እንደሆኑ ገልፀዋል። የቀረበባቸዉ ክስ አገራቸዉን ሲከላከሉ ከገጠማቸዉ ተፈታታኝ ሁኔታዎች ጋር ሲነጻጸር፤ በውቅያኖሱ ውስጥ እንዳለ ጠብታ የሚታይ ነዉ ብለዉታል።
    --የኬንያ ፖሊስ ዛሬ መዲና ናይሮቢ ላይ የሴቶች ግድያ እንዲቆም ሲሉ ለተቃዉሞ በወጡ ሰልፈኞች ላይ አስለቃሽ ጢስ ተኮሰ፤ ሦስት ሰዎችን አሰረዋል።
    ሙሉዉን ዜና የድምፅ ማድመጫ ማዕቀፉን በመጫን ይከታተሉ!
    10 min
  • የሰኞ ኅዳር 30 ቀን 2017 ዓ.ም.የዓለም ዜና
    የሰኞ ኅዳር 30 ቀን 2017 ዓ.ም. አርዕስተ ዜና
    ትናንት በአዲስ አበባ ከተማና በሌሎች ከተሞች ወደ ተሃድሶ ማዕካላት በሚያመሩ የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ታጣቂዎች በተከፈተ የተኩስ እሩምታ ድንጋጤ መፍጠሩን የየከተማዎቹ ነዋሪዎች ለዶቼቬለ ተናገሩ። በተኩስ እርምታው ነዋሪው ላይ ለተፈጠረው ድንጋጤና ረብሻ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ይቅርታ ጠይቋል።
    ከሀገራቸው የሸሹት የሶሪያው ፕሬዝዳንት በሽር አል አሳድ ሞስኮ ናቸው መባሉን ክሬምሊን ከማረጋገጥ ተቆጠበች።
    የሶሪያው ፕሬዝዳንት በሽር አላሳድ በአማጽያኑ ከተገለበጡ በኋላ ጀርመን የሶሪያ ዜጎች የተገን ጥያቄዎች ላይ የሚሰጡ ውሳኔዎችን ለጊዜው እንደምታቆም አስታወቀች።
    11 min
  • የዐርብ ኅዳር 27 ቀን፣ 2017 ዓ.ም የዓለም ዜና
    ሕጻናትን ጨምሮ የግዳጅ የውትድርና ምልመላ በኦሮሚያ ክልል፤ ምሥራቅ ወለጋ ዞን መንግሥት ትጥቅ እንዲፈቱ ያደረጋቸው የአማራ ተወላጆች የደህንነት ስጋት ላይ መውደቃቸው ተገለጠ፤፥ ኢትዮጵያ ተጨማሪ ጦር ወደ ሶማሊያ መላኳ ተዘገበ፥ ሶማሊያ ኢትዮጵያ በጁባላንድ ግዛቴ ጣልቃ እየገባች ነው ስትል ከሳለች ።
    11 min
  • የሐሙስ ኅዳር 26 ቀን 2017 ዓ.ም. የዓለም ዜና
    የኅዳር 26 ቀን 2017 ዓም አርዕስተ ዜና
    በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን ላስታ ወረዳ “ ብልባላ” በተባለች መንደር ባለፈው ማክሰኞ ሌሊት ተፈፀመ በተባለ የድሮን ጥቃት አንዲት የ83 ዓመት እናታቸው እንደተገደሉባችው የሟች ልጅ ለዶቼቬለ ተናገሩ።
    የቀድሞ የሰላም ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ታዬ ደንደዓ፤ ዛሬ ህዳር 26 ቀን 2017 ዓ.ም. እኩለ ቀን ላይ ከእስር ተለቀው ቤታቸው መግባታቸውን ባለቤታቸው ወ/ሮ ስንታየሁ ዓለማየሁ ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል፡፡
    የፈረንሳይ ጠ/ሚ ሚሼል ባርንየ የስራ መልቀቂያ ቢያስገቡም የማክሮ ጽህፈት ቤት እንዳለው ባርንየ አዲስ መንግሥት እስኪሰየም ድረስ ከሚኒስትሮቻቸው ጋር በሞግዚትነት ይቆያሉ ።
    11 min

About የዓለም ዜና

From the publisher's feed

ዶይቼ ቬለ የዕለቱን ዋና ዋና ዜናዎች ከኢትዮጵያ እና ከመላው ዓለም በየቀኑ ያቀርባል። የኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ፖለቲካዊ እና ኤኮኖሚያዊ ጉዳዮችን ጨምሮ የመላው ዓለምን ውሎ የተመለከቱ ጠቃሚ መረጃዎች በሰባቱም የሣምንቱ ቀናት ከምሽቱ አንድ ሰዓት ከዶይቼ ቬለ ያድምጡ። የዶይቼ ቬለን ዜናዎች በአፕል ፖድካስት…