የዓለም ዜና

የዓለም ዜና

Download on the App Store

የዓለም ዜና episodes

  • DW Amharic የሕዳር 25 ቀን 2017 የዓለም ዜና
    አቶ ታዬ ደንደአ በፍርድ ቤት በተፈቀደላቸው ዋስትና መሠረት ከእስር ቤት ሲወጡ በጸጥታ ኃይሎች ታፍነው መወሰዳቸውን ቤተሰቦቻቸው ተናገሩ። በኦሮሚያ ክልል ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን አሙሩ ወረዳ በአይሱዙ መኪና ላይ በደረሰው ጥቃት ስድስት ሰዎች መገደላቸውን ነዋሪዎች ተናገሩ። በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ሸዋሮቢት ከተማ በመንግሥት ኃይሎች እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል ወጊያ ሲካሔድ መዋሉን የከተማዋ ነዋሪዎች ተናገሩ። ልማት ባንክ እና የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽንን ጨምሮ ስምንት ድርጅቶች በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ሥር ተጠቃለሉ። ናሚቢያ ኔቱምቦ ናንዲ ንዳይትዋ የመጀመሪያዋ ሴት ፕሬዝደንት እንዲሆኑ መረጠች።
    11 min
  • የኅዳር 24 ቀን 2017 ዓ.ም. የዓለም ዜና
    ሂውማን ራይትስ ዎች የኢትዮጵያ መንግሥት ሰብአዊ መብቶች ላይ የሚያተኩሩ ሦስት የሀገር ውስጥ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን ማገዱን ተቸ። ድርጅቱ ባወጣው መግለጫ፤ ድርጊቱ ግጭት በተባባሰበት ጊዜ የቀረውን ብቸኛ ገለልተኛ የምልከታ መድረክ በማጥበብ መዝጋት ነው ሲል ወቅሷል።
    ዴሞክራቲክ ኮንጎ ሪፐብሊክ ውስጥ ምንነቱ ባልታወቀ በሽታ 143 ሰዎች መሞታቸው ተነገረ።
    የየመን ሁቲ ሚሊሺያዎች ከኢራቅ ሚሊሺያ ጋር በመተባበር እስራኤል ላይ የሰው አልባ አውሮፕላን ጥቃት ማድረሳቸውን አስታወቁ። ከእስራኤል በኩል ግን የተሰማ ነገር የለም።
    10 min
  • የሰኞ ኅዳር 23 ቀን 2017 ዓ/ም የዓለም ዜና
    DW Amharic-በኢትዮጵያ ሰላም እንዲመጣ ከተፈለገ ከመግለጫ ያለፈ ስራ በቁርጠኝነት ሊሰራ ይገባል መባሉ፤አቶ ታዬ ደንደዓ በዋስ እንዲፈቱ ፍርድ ቤት መወሰኑ-የኦሮምያ ክልል መንግስት የሰላም ስምምነት የተፈራረመው ተቀባይነት ከሌለው አመራሬ ጋር ነው” ነው ሲል የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት መግለጹ-ሶማሊያ ከኢትዮጵያ ጋር ለሽምግልና ከመቀመጧ በፊት ሀገሪቱ ከሶማሌ ላንድ ጋር የተፈራረመችውን ስምምነት እንድትሰርዝ ቅድመ ሁኔታ አስቀመጠች መባሉ-የጀርመኗ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አናሊና ቤርቦክ ቻይና ለሩሲያ የምታደርገውን ድጋፍ እንድታቆም ማስጠንቀቃቸው-
    በዛሬው የዓለም ዜና ተካተዋል።
    12 min
  • የሕዳር 22 ቀን 2017 የዓለም ዜና
    የሰላም ስምምነት በኦሮሚያ ክልል መንግሥት እና በኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት መካከል ፣
    ትራምፕ የብሪክስ አባላትን አስጠነቀቁ፣ ማሊ፤ በሰው አልባ አይሮፕላን በርካታ የቱአሬግ አማፂያን ተገደሉ፣
    እስራኤል ከየመን የተወነጨፈ ሚሳኤል ማክሸፏን ገለፀች፣ በቫሌንሲያ ማራቶን መገርቱ አለሙ ወርቅ አሸነፈች
    9 min
  • DW Amharic የሕዳር 21 ቀን 2017 የዓለም ዜና
    ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በአማራ እና በኦሮሚያ ክልሎች ከመንግሥታቸው የሚዋጉ ታጣቂዎች “አንድ ሺሕ ዓመት ቢታገሉ ስለማያሸንፉን፤ ያኛውን መንገድ ጥለው ወደ ሰላም እንዲመጡ” የሚል ጥሪ አቀረቡ። የኬንያ ፕሬዝደንት ዊሊያም ሩቶ ከዩጋንዳው አቻቸው ዩዌሪ ሙሴቬኒ ጋር በመሆን ኢትዮጵያን ከሶማሊያ ለማሸማገል እገዛ እንደሚያደርጉ አስታወቁ። በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን ሽርካ ወረዳ ታጣቂዎች ዘጠኝ ሰዎች መግደላቸውን ተከትሎ “መንግሥት ለደህንነታችን ሊደርስ ይገባል” ሲሉ ነዋሪዎች ጥሪ አቀረቡ። ፈረንሳይ ለምርምር በሚል ከ40 ዓመታት በላይ ይዛ ያቆየቻቸውን ወደ 3,500 የሚጠጉ የአርኪዮሎጂ ቅርሶች ለኢትዮጵያ አስረከበች።
    11 min
  • የአርብ ኅዳር 20 ቀን 2017 ዓ.ም. የዓለም ዜና
    አርዕስተ-ዜና
    የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እስካሁን የሠላም ሚንስትር የነበሩትን ብናልፍ አንዷለምን ሽረዉ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሐን ባለሥልጣን የበላይ ኃላፊ የነበሩትን መሐመድ ኢድሪስን
    በሠላም ሚንስትርነት ሾመዋል።
    በምዕራብ ኦሮሚያ ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን ሱሉላ ፍንጫ ወረዳ የሚገኘው የፍንጫ ስኳር ፍብሪካ የአገዳ ምርት ትናንት መቃጠሉን የፋብሪካዉ ሠራተኞችና ነዋሪዎች አስታወቁ።
    በምግብ ቀውስ ውስጥ በሚገኘው በጋዛ ሰርጥ በአንድ ዳቦ ቤት ውስጥ በተፈጠረ ግፍያ ሁለት ህጻናትና አንዲት ሴት ታፍነው መሞታቸውን የህክምና ባለሥልጣናት ተናገሩ።
    10 min
  • የኅዳር 19 ቀን 2017 ዓ.ም. የዓለም ዜና
    በአማራ ክልል በመንግሥት ሠራዊትና በፋኖ ታጣቂዎች በሚካሄደው ግጭት 4,5 ሚሊየን ሕጻናት ከትምህርት ገበታ ውጪ መሆናቸው መምህራንም መሰደዳቸው ተገለጸ።
    የሲዳማ ክልል የነዳጅ ግብይትና ቁጥጥር ግብረሀይል 2 የንግድና ገበያ ልማት መምሪያ ባለሙያዎችን ጨምሮ «ሕገ ወጥ የቤንዚን ንግድ ሲያከናውኑ ደረስኩባቸው» ያላቸውን 34 ሰዎች አሠረ።
    ሰሞኑን እግድ የተጣለባቸው ሦስት ሲቪል ድርጅቶች ላይ በአጭር ጊዜ የማጣራት ሥራው ተጠናቆ የመጨረሻ ውሳኔ እንደሚወሰን የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለሥልጣን አስታወቀ።
    በመላው ዓለም የሚታየው የአየር ብክለት በየዓመቱ ከ1,5 ሚሊየን በላይ ሰዎች ሞት ምክንያት መሆኑን አንድ ጥናት አመለከተ።
    11 min
  • የረቡዕ ኅዳር 18 ቀን 2017 ዓ.ም. የዓለም ዜና
    ኅዳር 18 ቀን 2017 ዓ.ም. አርዕስተ-ዜና
    -በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኮሬ ዞን ሳርማሌ ወረዳ በእሥር ላይ የነበሩ 66 መምህራን መፈታታቸውን የክልሉ መምህራን ማህበር ፕሬዝዳንት አቶ አማኑኤል ጳውሎስ ለዶቼ ቬለ ተናገሩ ፡፡
    -የኤርትራ ፕሬዚደንት ኢሣይያስ አፈወርቂ የሱዳን የእርስ በእርስ ጦርነት መፍትኄ ሊያገኝ የሚችለው በሱዳን ሕዝብ እና በሱዳን ጎረቤቶች ድጋፍ ብቻ ነው አሉ ።
    -በእስራኤልና የሊባኖሱ ደፈጣ ተዋጊ ቡድን ሒዝቡላሕ መካከል የተደረገው የተኩስ አቁም ስምምነት ዛሬ ገቢር መሆን ከጀመረ በኋላ በሺህዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች ወደ ሊባኖስ እየተመለሱ ነው ።
    10 min
  • የሕዳር 17 ቀን 2017 የዓለም ዜና
    -የኢትዮጵያ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለ2017 ዓመት 582 ቢሊዮን ብር ተጨማሪ በጀት አጠደቀ።የምክር ቤት አባላት ተጨማሪዉ በጀት የዋጋ ግሽበትን ያጠናክራል፣ ግብር ከፋዩን ያማርራል፤ ምጣኔ ሐብቱን ያዉካል የሚል ተቃዉሞ አንስተዉ ነበር ግን በአብላጫ ድምፅ ፀድቋል።-የኢትዮጵያ መንግሥት በቅርቡ 3 የመብት ተሟጋች ድርጅቶችን ማገዱን የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብቶች ተሟጋቾች ተቃወመዉ፤ አምንስቲ ኢንተርናሽናል አወገዘዉ።-እስራኤልና የሊባኖሱ ደፈጣ ተዋጊ ቡድን ሒዝቡላሕ ተኩስ ሊያቆሙ ነዉ።
    12 min
  • የዓለም ዜና፤ ኅዳር 16 ቀን ቀን 2017 ዓ.ም
    አርስተ ዜና
    --«G7» ሰባቱ በኢንዱስትሪ የበለፀጉት አገራት የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በመካከለኛዉ ምስራቅና በሩስያ ዩክሬይን ቀዉስ ጉዳይ ላይ ለመምከር የሁለት ቀን ስብሰባ ጣልያን ዉስጥ ጀመሩ። ሚኒስትሮቹ በእስራኤል ባለስልጣናትና በሃማዝ ወታደራዊ አዛዥ ላይ የተላለፈዉ የእስር ማዘዣም የመወያያ ርዕሳቸዉ ነዉ።--“ፅንፈኛና ሽብርተኛ” ያላቸው አካላት ሰሞኑን በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ደራ ወረዳ ፈጸሙት ያለውን ግድያ፤ የአማራ ከልል መንግሥት አወገዘ፡፡ ያም ሆኖ፤ የሰሞኑን ግድያ በገለልተኛ ወገን እንዲጣራ በተለያዩ ወገኖች ጥሪ እየቀረበ ነው። -- ቀሲስ በላይ መኮንን ዛሬ የመከላከያ ምስክሮቻቸውን ማሰማት ጀመሩ፡፡
    11 min

About የዓለም ዜና

From the publisher's feed

ዶይቼ ቬለ የዕለቱን ዋና ዋና ዜናዎች ከኢትዮጵያ እና ከመላው ዓለም በየቀኑ ያቀርባል። የኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ፖለቲካዊ እና ኤኮኖሚያዊ ጉዳዮችን ጨምሮ የመላው ዓለምን ውሎ የተመለከቱ ጠቃሚ መረጃዎች በሰባቱም የሣምንቱ ቀናት ከምሽቱ አንድ ሰዓት ከዶይቼ ቬለ ያድምጡ። የዶይቼ ቬለን ዜናዎች በአፕል ፖድካስት…