የዓለም ዜና

የዓለም ዜና

Download on the App Store

የዓለም ዜና episodes

  • DW Amharic የሕዳር 14 ቀን 2017 የዓለም ዜና
    የተመድ ጠቅላላ ጉባኤ የሕግ ኮሚቴ በሰብአዊነት ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎችን ለመከላከል እና አጥፊዎችን ለመቅጣት የሚያስችል ሥምምነት ለማዘጋጀት የሚያስችል ድርድር እንዲጀመር መንገድ የሚጠርግ የውሳኔ ሐሳብ አጸደቀ። በቀድሞው የደቡብ ሱዳን ፕሬዝደንት ሳልቫ ኪር ከጸጥታ ሹማምንቶቻቸው ጋር አስቸኳይ ስብሰባ አካሔዱ። እስራኤል በቤይሩት እና ሾምስታር በተባለች ከተማ በፈጸመቻቸው ሁለት ጥቃቶች ቢያንስ 19 ሰዎች መገደላቸውን ሊባኖስ አስታወቀች። የከባቢ አየር ለውጥ የበረታ ዳፋ የሚያሳድርባቸው ትናንሽ የደሴት ሀገራት እና አፍሪካውያን በአዘርባጃን ዋና ከተማ ባኩ በመካሔድ ላይ ከሚገኘው ድርድር ረግጠው በመውጣት ተቃውሟቸውን አሰሙ።
    12 min
  • የዓለም ዜና፤ ኅዳር 13 ቀን 2017 ዓ.ም
    አርስተ ዜና፤
    --በአዘርባጃን ባኩ እየተካሄደ ባለዉ የመጨረሻ ቀን የአየር ንብረት ጉባዔ ሁለተኛው የዕቅድ ስምምነት ለመጀመሪያ ጊዜ ወሳኝ የአየር ንብረት የፋይናንስ ግብ ማሳያ ቁጥር ያስቀምጣል ተብሎ ይጠበቃል።--እስራኤል እና አጋሮችዋ ዓለም አቀፉ የጦር ወንጀለኞች መዳኛ ፍርድ ቤት ለእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ፤ የእስር ማዘዣ እንዲሰጥ መወሰኑን አወገዙ። በሌላ በኩል ቱርክና የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች እርምጃውን በደስታ ተቀብለውታል።--የሃድያ ዞን ፖሊስ በሙስና ተጠርጥረው የተያዙ አንድ ከፍተኛ የዞን ባለሥልጣንን፤ ሆን ብለው ከማረሚያ ቤት አስምልጠዋል ያላቸውን፤ አምስት የፖሊስ አባላትን አሠረ፡፡
    11 min
  • የህዳር 12 ቀን ቀን 2017 የዓለም ዜና
    የኢትዮጵያ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ለ2017 ተጨማሪ 582 ቢሊዮን ብር ገደማ በጀት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲቀርብ ወሰነ። የቀድሞው የትግራይ ኃይሎች አባላት የነበሩ ከ300 በላይ ተዋጊዎች የጦር መሣሪያዎቻቸውን ለኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት አስረከቡ። ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ ኬንያ ከሕንዱ አዳኒ ግሩፕ ጋር የናይሮቢ የአውሮፕላን ማረፊያን ለማስፋፋት እና የኃይል መሠረተ-ልማት ለመገንባት የያዘችውን ዕቅድ ሰረዙ። ዓለም አቀፉ የጦር ወንጀሎች መዳኛ ፍርድ ቤት የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታንያሁ፣ የቀድሞ መከላከያ ሚኒስትራቸው ዮቭ ጋላንት እና የሐማስ ወታደራዊ አዛዥ ሞሐመድ ዲይፍ ላይ የእስር ማዘዣ አወጣ።
    11 min
  • የኅዳር 11 ቀን 2017 ዓ.ም.የዓለም ዜና
    የኅዳር 11 ቀን 2017 ዓ.ም. አርዕስተ ዜና
    ብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን ትጥቅ የፈቱ፣ የሰላም ስምምነት የፈረሙ ድርጅቶች ውስጥ አባል የነበሩ እና በ6 ክልሎች የሚገኙ 371,971 የቀድሞ ተዋጊዎችን ትጥቅ በማስፈታት ወደ ተሃድሶ ማዕከላት እንደሚገቡ ተናግሯል።
    ማዕከላዊ ሱዳን ውስጥ ፈጥኖ ደራሹ ኃይል ከትናንት አንስቶ ባደረሰው ጥቃት 40 ሰዎች መገደላቸው ተሰማሩ።
    በአዘርባጃኑ ኮፕ 29 ላይ የተሳተፉ 25 ሀገራት አዳዲስ የድንጋይ ከሰል የኃይል ማመንጫ ላለመገንባት ቃል ገቡ።ቃል ከገቡት ባለጸጋ ሀገራት መክከል ብሪታንያ ፣ ካናዳ ፣ፈረንሳይ፣ ጀርመን እና አውስትራሊያ ይገኙበታል።
    11 min
  • የማክሰኞ ኅዳር፤ 10 ቀን፣ 2017 ዓ.ም የዓለም ዜና
    አርዕስተ ዜና
    *የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው መደበኛ ጉባኤው የአንድ የምክር ቤቱን አባል የአለመከሰስ መብት አነሳ ።
    *የሶማሊላንድ ፕሬዚደንት ሙሴ ቢሂ አብዲ በፕሬዚደንታዊ ምርጫው ተሸነፉ ። ራስዋን የሶማሊላንድ ሪፐብሊክ ብላ የምትጠራዉ ግዛት የምርጫ ኮሚሽን ተቃዋሚው አብዲራህማን ሞሐመድ አብዱላሂ በቅጽል ስማቸው «ኢሮ» የፕሬዚደንታዊ ምርጫውን ማሸነፋቸውን ዛሬ ይፋ አድርጓል ።
    *ሩስያ ዩክሬንን በጦር ኃይል ከወረረች ከ1000 ቀን በኋላ ዛሬ ለመጀመሪያ ጊዜ የዩክሬን ጦር በዩናይትድ ስቴትስ የረዥም ርቀት ሚሳይል ሩስያን መምታቱን ዐሳወቀ ። የ
    11 min
  • የዓለም ዜና፤ ኅዳር 09 ቀን 2017 ዓ.ም
    DW Amharic አርስተ ዜና፤
    --የቡድን 20 አገሮች የሁለት ቀናት የመሪዎች ጉባኤ ዛሬ ብራዚል ሬዮዴጄኔሮ ላይ ጀመረ። 19 በእንዱስትሪ የበለጽጉ እና ያደጉ የዓለም አገሮች እንዲሁም የአውሮጳ ህብረትን ያካተተዉ የቡድን 20 ጉባዔን ለመሳተፍ ሀገራት መሪዎች ከፍተኛ ልዑካኖቻቸዉን አስከትለዉ በጉባኤዉ ለመሳተፍ ሬዮዴጄኔሮ ገብተዋል።
    --የቀድሞ የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ታዬ ደንደዓ ዛሬ በቀጠሮያቸው መሰረት በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት ቀረቡ።
    --የሱዳን የፈጥኖ ደራሽ ኃይላት በጦርነቱ ለተፈፀመዉ ሰብዓዊ ጥሰት ኃላፊነት እንደማይወስዱ ገለፁ።
    12 min
  • DW Amharic የሕዳር 08 ቀን 2017 የዓለም ዜና
    በጋምቤላ ክልል ከ4 ዞኖች ለ138 የህግ ታራሚዎች ይቅርታ ተደረገ። ሳዑዲ አረቢያ በጎርጎሮሳውያኑ 2024 ሰባት ኢትዮጵያውያን ጨምሮ ከ100 በላይ የውጪ ሀገራት ዜጎች በሞት መቅጣቷን AFP ዘገበ። ሒዝቦላሕ ቃል አቀባዩ ሞሐመድ አፊፍ በእስራኤል የአየር ጥቃት መገደላቸውን አስታወቀ። ሩሲያ በ120 ሚሳይሎች እና 90 ሰው አልባ አውሮፕላኖች በዩክሬን የኃይል መሠረተ-ልማቶች ላይ ከባድ የአየር ድብደባ ፈጸመች። የጀርመን መራኄ መንግሥት ኦላፍ ሾልስ ከሩሲያ ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር ያደረጉትን የስልክ ንግግር ተከላከሉ። የቻይናው ፕሬዝደንት ሺ ዢንፒንግ ከአሜሪካው ተመራጭ ፕሬዝደንት ዶናልፕ ትራምፕ ጋር ለመሥራት ቃል ገቡ።
    10 min
  • የኅዳር 6 ቀን፣ 2017 ዓ.ም የዓለም ዜና
    ማሊ ውስጥ የቆየው የተመድ ተልዕኮ በዛሬው ዕለት ለሀገሪቱ ወታደራዊ ኹንታ ባለሥልጣናት ወታደራዊ ሰፈሩን አስረከበ። በያዝነው ዓመት ታኅሣስ ማለቂያ አካባቢ ተልዕኮው አጠቃሎ ከማሊ ይወጣል።
    ዓመታዊው የተመድ የአየር ንብረት ለውጥ ተከታታይ ጉባኤ የተነሳለትን አላማ ማሳካት ተስኖታል የሚሉ ወገኖች የማሳሰቢያ ደብዳቤ ለጉባኤው አቀረቡ።
    ተመራጩ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ የመካከለኛው ምሥራቅ እና የሩሲያ እና የዩክሬን ጦርነት መቆም አለበት አሉ።
    የጀርመን መራኄ መንግሥት ኦላፍ ሾልስ ከሁለት ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ዛሬ ከሩሲያው ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር በስልክ ተነጋገሩ።
    10 min

About የዓለም ዜና

From the publisher's feed

ዶይቼ ቬለ የዕለቱን ዋና ዋና ዜናዎች ከኢትዮጵያ እና ከመላው ዓለም በየቀኑ ያቀርባል። የኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ፖለቲካዊ እና ኤኮኖሚያዊ ጉዳዮችን ጨምሮ የመላው ዓለምን ውሎ የተመለከቱ ጠቃሚ መረጃዎች በሰባቱም የሣምንቱ ቀናት ከምሽቱ አንድ ሰዓት ከዶይቼ ቬለ ያድምጡ። የዶይቼ ቬለን ዜናዎች በአፕል ፖድካስት…