የዓለም ዜና

የዓለም ዜና

Download on the App Store

የዓለም ዜና episodes

  • የኅዳር 5 ቀን 2017 ዓ.ም. የዓለም ዜና
    የኅዳር 5 ቀን 2017 ዓ.ም. አርዕስተ ዜና
    ባለፈው ማክሰኞ የክስ ጭብጣቸው በዐቃቤ ሕግ ተሻሽሎ ከቀረበው በሽብር ወንጀል ከተከሰሱ 51 ሰዎች መካከል በፖሊስ ቁጥጥር ሥር የዋሉት ዛሬ ሐሙስ የእምነት ክህደት ቃላቸውን ሰጡ። በእነ ዶ/ር ወንድወሰን አሰፋ መዝገብ በሽብር ወንጀል ክስ ከቀረበባቸው 51 ተከሳሾች መካከል አራት የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ይገኙበታል።
    የኢትዮጵያ ፌደራል መንግስት፣ የኤርትራ ጦር ከኢትዮጵያ ሉዓላዊ ግዛት እንዲወጣ በይፋ አለመጠየቁ አሳሳቢ ነው የዓሲምባ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ አስታወቀ።
    ቱርክ ብሪክስ በተባለው ቡድን የአጋርነት ደረጃ ተሰጣት።
    10 min
  • የሕዳር 4 ቀን 2017 የዓለም ዜና
    -የሶማሊላንድ ሕዝብ የወደፊት ፕሬዝደንቱን ለምረጥ ዛሬ ድምፅ ሲሰጥ ዉሏል።በምርጫዉ ራስዋን የሶማሊላንድ ሪፐብሊክ ብላ የምትጠራዉን ግዛት ላለፉት ሰባት ዓመታት የመሩት ፕሬዝደንት ሙሴ ቢሒ አብዲ ከዋነኛዉ ተቃዋሚ ፓርቲ ዕጩ ከአብዲረሕማን መሐመድ አብዱላሒ ጋር በቅርብ ርቀት ይፎካከራሉ።----የእስራኤል ጦር ዛሬም እንደመሰንበቻዉ የጋዛ ሠርጥንና የሊባኖስ ርዕሰ ከተማ ቤይሩትን ሲደበድብ ዋለ።--ባኩ-አዘር በጃን በተያዘዉ የዓየር ንብረት ጉባኤ ላይ የአየር ንብረትን በመበከል ቀዳሚዉን ሥፍራ የሚይዙ ሐገራት መሪዎች ባለመገኘታቸዉ ጉባኤዉ ለአግባቢ ዉጤት መድረሱ እያነጋገረ ነዉ።
    11 min
  • የማክሰኞ ኅዳር 03 ቀን፣ 2017 ዓ.ም የዓለም ዜና
    *አራት የመገናኛ ብዙኃን ባለሞያዎችን ጨምሮ በእነ ዶ/ር ወንድወሰን አሰፋ መዝገብ በሽብር ወንጀል ክስ የቀረበባቸው 51 ተከሳሾች የእምነት ክህደት ቃላቸውን ለመስጠት ለሕዳር 5 እንዲቀርቡ ቀጠሮ መስጠቱ ተገለጠ ። ​*የጋዜጠኛ ዜናነህ መኮንን ሥርዓተ-ቀብር ማክሰኞ ኅዳር 03 ቀን፣ 2017 ዓ.ም በእስራኤል ቴል አቪቭ ከተማ ያልሚና ያል ኮን በተባለ ሥፍራ ተፈጸመ ። *በቅርቡ ጥምረቱ የፈረሰበት የጀርመን መንግሥትን ለመተካት ዋነኞቹ የፖለቲካ ፓርቲዎች በሦስት ወራት ጊዜ ውስጥ ሀገር አቀፍ ምርጫ ለማካሄድ ስምምነት ላይ ደረሱ ።
    9 min
  • የዓለም ዜና፤ ኅዳር 2 ቀን 2017 ዓ.ም ሰኞ
    DW Amharic የሳዑዲ አረቢያዉ ልዑል ማሐመድ ቢን ሰልማን በጋዛ እና በሊባኖስ አፋጣኝ የተኩስ አቁም እንዲደረግ ጠየቁ። ቢን ሳልማን ጥሪዉን ያቀረቡት በሳውዲ አረቢያ ሪያድ በአረብ ሊግና በእስልምና ትብብር ድርጅት የጋራ ጉባዔ ላይ ነው።//በኤርትራ ፍርድ ከ 23 ዓመታት በላይ የታሰረዉ ትዉልደ ኤርትራዊዉ ዳዊት ይህሳቅ፤ ለሃሳብ ነጻነት ላደረገዉ ትግል የስዊድንን የመብት ከፍተኛ ሽልማት አገኘ።// ራስ ገዝዋ ሶማሌላንድ የፊታችን ረቡዕ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ እንደምታካሂድ ተነገረ።// ተመራጩ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከጀርመን ቻንስለር ኦላፍ ሾልዝ ጋር በአውሮጳ "ሰላምን በመመለስ" ጉዳይ ላይ ተነጋገሩ።
    11 min
  • የጥቅምት 30 ቀን 2017 የዓለም ዜና
    ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ኅብረት የድጋፍ እና ማረጋጋት የሶማሊያ ተልዕኮ (AUSSOM) መታገዷን የሶማሊያ መከላከያ ሚኒስትር ተናገሩ። በደቡብ ሱዳን ጎርፍ 379,000 ሰዎች አፈናቀለ። በናይጄሪያ ላኩራዋስ የተባለ አዲስ የሽምቅ ተዋጊ በፈጸመው ጥቃት 15 ሰዎች ተገደሉ። በፓኪስታን የባቡር ጣቢያ በደረሰ ፍንዳታ ቢያንስ 24 ሰዎች ተገደሉ። እስራኤል እና ሐማስ ወደ ድርድር ለመመለስ ከልብ ፈቃደኝነታቸውን እስኪያሳዩ ድረስ ቃጣር በጋዛ ተኩስ እንዲቆም የምታደርገውን ጥረት ልታቆም ነው። ኢራን ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ለአራት ዓመታት ሥልጣን ላይ ሣሉ ያሳደሩባትን ከፍተኛ ጫና በሁለተኛ የሥልጣን ዘመናቸው እንዲተዉት ጥሪ አቀረበች።
    11 min
  • የጥቅምት 29 ቀን 2017 ዓ/ም የዓለም ዜና
    አርስተ ዜና፤
    --በአማራ ክልል ሰሜን ጎጃም ዞን አቸፈር ወረዳ ባለፈው ማክሰኞ ጥቅምት 26/2017 በድሮን በተፈፀመ ጥቃት ከ40 በላይ ሰዎች መገደላቸውንና 9 መቁሰላቸውን ነዋሪዎች ተናገሩ።
    --የኢትዮጵያ የገንዘብ ሚኒስቴር በፍራንኮ ቫሉታ ሸቀጦችን ወደ ሃገር ውስጥ ማስገባት ከዛሬ ጀምሮ አገደ።
    --አቶ ዮሃንስ ቧያሌው 1ኛ ተከሳሽ በሆኑበት መዝገብ የተከሰሱና ጉዳያቸው በፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት እየታየ ያለው ግለሰቦች ለሕዳር 20 ቀን 2017 ዓ.ም ተቀጠሩ።
    --በጋዛ ጦርነት ከተገደሉት ውስጥ 70 በመቶ ያህሉ ሴቶች እና ህጻናት መሆናቸው መለየቱን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስታወቀ።
    ሙሉዉን ዜና ያድምጡ!
    12 min
  • የጥቅምት 28 ቀን፣ 2017 ዓ.ም የዓለም ዜና
    ኦሮሚያ ክልል ውስጥ የወረዳ ባለሥልጣናትን ጨምሮ 48 ሰዎች የተገደሉበትን ጥቃት እየመረመረ መሆኑን የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ዛሬ አስታወቀ።
    የባሕርዳር ከተማ አስተዳደር በእገታና በዘረፋ ተሰማርተው ነበር ያላቸውን ክ129 በላይ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ማዋሉን ገለጠ።
    የጀርመን የፋይናንስ ሚኒስትር ከሥልጣናቸው መነሳታቸውን ተከትሎ የሀገሪቱ ጥምር መንግሥት ቀውስ ውስጥ ገብቷል። ተቃዋሚዎች አስቸኳይ ምርጫ እንዲካሄድ ግፊት እያደረጉ ነው። ፕሬዝደንት ፍራንክ ቫልተር ሽታይን ማየር የጥምር መንግሥቱ ለገባበት ቀውስ መፍትሄ ለማምጣት ኃላፊነት የተሞላበት አካሄድ እንዲኖር ፖለቲከኞቹን አሳስበዋል።
    10 min
  • የዓለም ዜና፤ ጥቅምት 26 ቀን 2017 ዓ.ም ማክሰኞ
    DW Amharic አርስተ ዜና
    በአማራ ክልል እየተባባሰ የሄደው ግጭት እንዳሳሰባት አሜሪካ አስታወቀች። በኢትዮጵያ ግጭቶች እልባት ያገኙ ዘንድ የፖለቲካ ውይይቶች መደረግ አለባቸው፤ የሚል አቋም እንዳላትም ገልፃለች።--አሜሪካ 47 ኛዉን ፕሬዚዳንታዊ ምርጫን እያካሄደች ነዉ። ሁለቱ ፕሬዚዳንታዊ እጩዎች በየፊናቸዉ እንደሚያሸንፉ ተናግረዋል። በሌላ በኩል የአሜሪካ የደኅንነት ባለስልጣናት «የውጭ ኃይሎች» ያሏቸዉ የአሜሪካ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ እምነት እንዲያጣ ሙከራ እያደረጉ ነው ሲሉ እየከሰሱ ነዉ።--የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎዲሜር ዜሌንስኪ 11,000 የሰሜን ኮሪያ ወታደሮች ሩስያ ድንበር ኩርስክ ግዛት መግባታቸዉን በስጋት ገለፁ።
    12 min

About የዓለም ዜና

From the publisher's feed

ዶይቼ ቬለ የዕለቱን ዋና ዋና ዜናዎች ከኢትዮጵያ እና ከመላው ዓለም በየቀኑ ያቀርባል። የኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ፖለቲካዊ እና ኤኮኖሚያዊ ጉዳዮችን ጨምሮ የመላው ዓለምን ውሎ የተመለከቱ ጠቃሚ መረጃዎች በሰባቱም የሣምንቱ ቀናት ከምሽቱ አንድ ሰዓት ከዶይቼ ቬለ ያድምጡ። የዶይቼ ቬለን ዜናዎች በአፕል ፖድካስት…