የዓለም ዜና

የዓለም ዜና

Download on the App Store

የዓለም ዜና episodes

  • የጥቅምት 25 ቀን 2017 ዓ.ም የዓለም ዜና
    በሶማሊያ ዋና ከተማ መቅዲሹ ላይ አሸባብ ባደረሰው ጥቃት የተመድ ሠራተኞችን ጨምሮ በርካቶች መገደላቸው ተነገረ። ጥቃቱ የደረሰው ከመቃዲሹ አውሮፕላን ማረፊያ አቅራቢያ የሚገኝ ከፍተኛ ጥበቃ በሚደረግለት ስፍራ ነው።
    ስፔን ውስጥ የአደጋ ጊዜ ሠራተኞች ዛሬም የጎርፍ ሰለባዎችን መፈለግ ቀጥለዋል። ቫለንሲያ ግዛት በጎርፍ ከደረሰባት አደጋ ጋር እየታገለች ዛሬ ኃይለኛ ዝናብ የወረደባት ባርሴሎና ከተማ በተጠንቀቅ ላይ ትገኛለች።
    የሱዳን ጦር አዛዥ አብደልፈታህ አል ቡርሀን የባለሥልጣናት ሹም ሽር አደረጉ። አራት አዳዲስ ሚኒስትሮችንም ሰየሙ።
    የእስራኤል ጦር ሰሜን ጋዛ ውስጥ የሚገኘው የክትባት ማዕከል ላይ ጥቃት አላዳረስኩም አለ።
    10 min
  • የጥቅምት 23 ቀን 2017 የዓለም ዜና
    የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት በኦሮሚያ ክልል በተፈጸሙ ጥቃቶች 120 የመንግሥት ወታደሮች ገድያለሁ አለ። ህወሓት በፕሪቶሪያ ግጭት የማቆም ሥምምነት የገባቸውን ግዴታዎች እየፈጸመ አይደለም ሲል የኢትዮጵያ መንግሥትን ከሰሰ። አሜሪካ “ታሪካዊ“ ያለችው “የርስ በርስ ጦርነት ያቆመ ሥምምነት“ የተፈረመበትን ሁለተኛ ዓመት በማስመልከት በኢትዮጵያ ግጭት እንዲቆም ጥሪ አቅርባለች። የወባ ወረርሽኝ በኢትዮጵያ ዋንኛ የሕብረተሰብ ጤና ተግዳሮት እንደሆነ የዓለም ጤና ድርጅት አስጠነቀቀ። ከታኅሳስ 22 ቀን 2016 እስከ ጥቅምት 10 ቀን 2017 ብቻ 7.3 ሚሊዮን የወባ ሕሙማን መመዝገባቸውን፤ 1157 ሰዎች መሞታቸውን አስታውቋል።
    12 min
  • የጥቅምት 22 ቀን 2017 ዓ.ም. የዓለም ዜና
    *በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሸዋ ዞን ዱግዳ ወረዳ በታጠቁ ኃይሎች በደረሰ ጥቃት ቢያንስ የ40 ንጹሃን ሰዎች ህይወት አለፈ።
    *በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ዛሬ ጠዋት በደረሰ የመሬት መንሸራተት አደጋ የ10 ሰዎች ሕይወት አለፈ ፡፡
    *ሁለቱ የህወሓት ቡድኖች በልዩነታቸው ላይ ለመነጋገር እንደተስማሙ ተነገረ።
    *የጀርመን ፌደራል መንግስት በሀገሩ የሚገኙ የኢራን ቆንስላዎች በሙሉ እንዲዘጉ ወሰነ።
    * እስራኤል ሊባቦስ እና ጋዛ ውስጥ ጥቃት ሰነዘረች
    10 min
  • የሐሙስ ጥቅምት 21 ቀን 2017 ዓ/ም የዓለም ዜና
    DW Amharic -በአማራ ክልል ያለውን ቀውስ ለመፍታት የሰላም ጥረት አለመሳካቱን ጠቅላይ ሚንስትሩ መግለፃቸው-ከአየር ንብረት እና ኢኮኖሚያዊ ችግር ጋር ተዳምሮ የግጭት መስፋፋት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን ለከፋ ችግር ዳርጓል መባሉ-ሶማሊያ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አዲስ የሽግግር ተልዕኮ ለማቋቋም መወሰኑን ማወደሷ-እስራኤል ሊባኖስ ውስጥ በፈፀመችው የአየር ጥቃት ሰላማዊ ሰዎች ተገደሉ መባሉ-ሰሜን ኮሪያ አህጉር አቋራጭ የባሊስቲክ ሚሳኤል መተኮሷን መግለጿ በዛሬው የዓለም ዜና የተካተቱ ርዕሶች ናቸው።
    12 min
  • የጥቅምት 20 ቀን 2017 ዓ.ም የዓለም ዜና
    በዎላይታ ዞን እና በሲዳማ ክልል ውስጥ ትናንት በደረሰ መሬት መንሸራተት የዘጠኝ ሰዎች ሕይወት አለፈ። የአደጋው መንስኤ በሌሊት የጣለው ከባድ ዝናብ እንደሆነ ተገልጿል።
    በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጉራጌ ዞን በፀጥታ አባላት የጅምላ እሥር እየተፈጸመ መሆኑን የአካባቢው ነዋሪዎች አመለከቱ። መንስኤው ከሸኔ አለያም ከፋኖ ጋር ግንኙነት አላችሁ የሚል ነው ተብሏል።
    የሴኔጋል ባሕር ኃይል ባለፉት 10 ቀናት 600 የሚሆኑ ሕገወጥ ስደተኞችን ከባሕር ላይ መያዙን አስታወቀ።
    ኢራን በእስራኤል ጥቃት የሚሳኤል ማምረቻዎቼ አልተጎዱም አለች።
    9 min
  • የማክሰኞ፤ ጥቅምት 19 ቀን፣ 2017 ዓ.ም የዓለም ዜና
    አ.አ፥ በተወካዮች ምክር ቤት አባል የፍትሕ ሚንስትር ላይ ትችት ቀረበ፤ መቐለ፥ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የመቐለ ከንቲባን ከሥልጣን ማገዱን ዐሳወቀ፤ ካርቱም፥ ከሱዳን አንድ ሦስተኛ ግድም ነዋሪ ስደተኛ አለያም ተፈናቃይ ነው፤ ኒውዮርክ፥ በእሥራኤል የUNRWA መታገድ በፍልስጥኤም ስደተኞች ላይ የከፋ መዘዝ ያስከትታል ሲል ተመድ አስጠነቀቀ፤
    10 min
  • የዓለም ዜና፤ ጥቅምት 18 ቀን 2017 ሰኞ
    DW Amharic--ግብፅ አራት የሃማስ ታጋች እስራኤላውያንን በተወሰኑ ፍልስጤማዉያን እስረኞች ለመለወጥ በጋዛ የሁለት ቀን የተኩስ አቁም እንዲደረግ ሀሳብ አቀረበች። የግብጹ ፕሬዝዳንት አብዱልፈታህ ኧልሲሲ ይህን ያሉት ከአንድ ዓመት በላይ የዘለቀውን የጋዛ ጦርነት ለማስቆም የሚደረገው ድርድር ድጋሚ በተጀመረበት ወቅት ነው፡፡
    --125 ኢትዮጵያውያን ከሊባኖስ ወደ ሃገራቸዉ መመለሳቸዉን የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።
    --የዩናይትድ ስቴትስ የሪፓብሊካን እጩ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ፤ ተቀናቃኛቸዉ የዲሞክራቶች እጩ ተወዳዳሪ ካማላ ሃሪስ ዩናይትድ ስቴትስን እያወደሙ ነዉ ሲሉ ከሰሱ ። ዝርዝሩን ያድምጡ!
    12 min
  • DW Amharic የጥቅምት 17 ቀን 2017 የዓለም ዜና
    ብሔራዊ የምክክር ኮሚሽን በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ነገ ሰኞ አጀንዳ ማሰባሰብ ሊጀምር ነው። የኢራን መንፈሳዊ መሪ አያቶላ አሊ ኻሚኒ እስራኤል በሀገራቸው ላይ ባለፈው አርብ የፈጸመችው ጥቃት ሊናናቅም ሆነ ሊጋነን እንደማይገባ ተናገሩ። ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታንያሁ በበኩላቸው ጥቃቱ የታለመለትን ዓላማ አሳክቷል ብለዋል። በጋዛ እስራኤል በፈጸመቻቸው ጥቃቶች 45 ፍልስጤማውያን መገደላቸውን የፍልስጤም ባለሥልጣናት አስታወቁ። ዮሚፍ ቀጀልቻ በቫሌንሺያ፤ ሐዊ ፈይሳ በፍራንክፉርት ክብረ ወሰን በማሻሻል የግማሽ ማራቶን እና የማራቶን ውድድሮች አሸነፉ። የቀድሞው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ አሥራት ኃይሌ ሥርዓተ ቀብር ተፈጸመ።
    9 min

About የዓለም ዜና

From the publisher's feed

ዶይቼ ቬለ የዕለቱን ዋና ዋና ዜናዎች ከኢትዮጵያ እና ከመላው ዓለም በየቀኑ ያቀርባል። የኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ፖለቲካዊ እና ኤኮኖሚያዊ ጉዳዮችን ጨምሮ የመላው ዓለምን ውሎ የተመለከቱ ጠቃሚ መረጃዎች በሰባቱም የሣምንቱ ቀናት ከምሽቱ አንድ ሰዓት ከዶይቼ ቬለ ያድምጡ። የዶይቼ ቬለን ዜናዎች በአፕል ፖድካስት…