የዓለም ዜና

የዓለም ዜና

Download on the App Store

የዓለም ዜና episodes

  • የታኅሣሥ 15 ቀን 2017 ዓ.ም. የዓለም ዜና
    የሶማሊያ መንግሥት የኢትዮጵያ ጦር በድንበር አካባቢ ባሉ ሁለት ከተሞች ላይ ጥቃት አድርሶብኛል ሲል ከሰሰ። ክሱን አስደንጋጭ ያለው የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በበኩሉ ሀሰት ነው ሲል አስተባብሏል። ድርጊቱ የሁለቱን ሃገራት ጤናማ ግንኙነት ለማበላሸት ባለሙ ኃይሎች የተፈጸመ ነውም ብሏል።
    ቀጠር ሶርያ ላይ የተጣለው ዓለም አቀፍ ማዕቀብ ባስቸኳይ እንዲነሳ ጠየቀች።
    16 ሰዎች አሳፍራ የነበረች አንድ የሩሲያ ዕቃ ጫኝ መርከብ ስፔን አቅራቢያ መስመጧ ተሰማ። ከተሳፋሪዎቹ ሁለቱ አልተገኙም።
    የአሜሪካ አየር መንገድ ጠቅላላ በረራዎቹን የቴክኒክ ችግር ባለው ምክንያት ማቋረጡን ዛሬ አስታወቀ።
    10 min
  • የታህሳስ 12 ቀን 2017 የዓለም ዜና
    የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) የፋኖ ኃይሎች በኦሮሚያ ክልል ወለጋ አከባቢ ዕዝ እንዲመሰርቱ መንግስት ድጋፍ አድርጓል ሲል ከሰሰ፡፡
    በጀርመን በደረሰው ጥቃት 5ሞቱ ከ200 በላይ ቆሰሉ
    11 min
  • የሐሙስ ታኅሣሥ 10 ቀን፣ 2017 ዓ.ም የዓለም ዜና
    *ባለፈው ሰኞ በመቅረዝ ጠቅላላ ሆስፒታል የቅድመ ካንሰር ምርመራ የተደረገላቸውና በእሥር ላይ ያሉት አቶ ክርስትያን ታደለ እና አቶ ዮሐንስ ቧያለው ዛሬም ሆስፒታል ሳይወሰዱ መቅረታቸው ተነገረ ።
    *በዶክተር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል የሚመራው ሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ሕወሓት) ቡድን «አዲስ» ያለውን የትግል አቅጣጫ እንደሚከተል ዐሳወቀ ።
    *በውጭ አገራት የርዳታ ተግባር ላይ ተሰማርተው የነበሩ ከ280 በላይ ሠራተኞች ባለፉት 12 ወራት ውስጥ ብቻ መገደላቸው ተገለጠ ።
    *ጀርመን ውስጥ ከማኅበረሰቡ ጋር ያልተዋሐዱ ሶሪያውያን ሊባረሩ ይገባል ሲሉ አንድ ከፍተኛ ፖለቲከኛ ተናገሩ ።
    10 min
  • የታኅሳስ 9 ቀን 2017 ዓ.ም. የዓለም ዜና
    የታኅሳስ 9 ቀን 2017 ዓ.ም. አርዕስተ ዜና
    የኢትዮጵያ መንግሥት የመብቶች እና ዴሞክራሲ ማዕከል የተባለውን የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅት ዳግም «ከማንኛውም የሥራ እንቅስቃሴ» አገደ።
    የአውሮጳ ኅብረት በሶሪያ ላይ የጣላቸውን አንዳንድ የኤኮኖሚ ማዕቀቦች ማንሳትን እንደገና ሊያጤን እንደሚችል አስታወቀ።
    የፈረንሳይ ከፍተኛ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት የቀድሞው ፕሬዝዳንት ኒኮላ ሳርኮዚ በሙስና እና ስልጣናቸውን አለአግባብ በመጠቀም ተከሰው የተበየነባቸውን ውሳኔ አፀና። ፍርድ ቤቱ ሳርኮዚ እንቅስቃሴያቸውን የሚከታተል የኤሌክትሮኒክ መሳሪያ ለአንድ ዓመት እንዲያደርጉም አዟል።
    11 min
  • የማክሰኞ ታኅሣሥ 8 ቀን፣ 2017 ዓ.ም የዓለም ዜና
    በአማራ ክልል ጎጃም ቀጣና በፋኖ ትዕዛዝ ለሳምንት ተዘግቶ የቆየው የእንቅስቃሴ ገደብ ከዛሬ ጠዋት ጀምሮ አገልግሎት መስጠት መጀመሩ ተገለጠ ። መንገዶቹ መከፈታቸውን አንዳንድ ተገልጋዮች ለዶይቸ ቬለ ተናግረዋል ።
    የውጭ ባንኮች ኢትዮጵያ ውስጥ ገብተው እንዲሠሩ የሚፈቅድ አዋጅ ዛሬ ጸደቀ ። አዋጁ በሦስት ተቃውሞ፤ በአብላጫ ድምፅ መጽደቁ ተገልጧል ።
    ሩስያ ከፍተኛ የጦር መኮንኗን ሞስኮ ውስጥ በተጠመደ ቦንብ ፍንዳታ አጣች ። የ54 ዓመቱ ሩስያዊ ሊውቴናንት ጄኔራል ከረዳታቸው ጋር ዛሬ ጠዋት የተገደሉት በእግር ተረግጦ በሚገፋ የኤሌክትሪክ መጓጓዣ ወይንም ስኩተር ላይ በተጠመደ ፈንጂ ፍንዳታ መሆኑ ተዘግቧል ።
    11 min
  • የዓለም ዜና፤ ታህሳስ 7 ቀን 2017 ዓ.ም ሰኞ
    --ባለፉት 8 ቀናት በጎጃም ቀጠና የነበረው የእንቅስቃሴ ገደብ መነሳቱን የአማራ ፋኖ በጎጃም አስታወቀ። የአማራ ፋኖ በጎጃም የህዝብ ግንኙነት መምሪያ ምክትል ኃላፊ እንደሆኑ የገለፁልን ዮሐንስ ዓለማየሁ ባለፉት 8 ቀናት በጎጃም ቀጠና አንዳንድ አካባቢዎች በተደርጉ ውጊያዎች ህብረተሰቡ በመንግድ ሊገጥመው የሚችለውን ሞትና እንግልት ለማስወገድ የመንገድና የንግድ እንቅስቃሴዎች ላይ ገደብ ተጥሎ መቆየቱን ተናግረዋል።
    -- የቱርኩ ፕሬዚዳንት ራቺብ ታይብ ኤርዶጋን በቅርቡ ኢትዮጵያን እና ሶማልያን እንደሚጎበኙ ተነገረ።--የሶርያዉ ባሽር አልአሳድ ከሶሪያ አቅጄ አልወጣሁም ለመዉጣትም እቅድ አልነበረኝም፤ የወጣሁት በሩስያ ነዉ አሉ።
    13 min
  • የታህሳስ 6 ቀን 2017 የዓለም ዜና
    በሱዳን በድሮን ጥቃት 3 ስቪሎች መገደላቸውንና ከ20 በላይ መቁሰላቸውን
    ያለውጤት የተበተነው ድርድር
    ቱርክ የበሽር አልአሳድን መንግስት ለገረሰሱት አማጽያን ወታደራዊ ድጋፍ ለመስጠት ዝግጁ እንደሆነች
    ከ7,500 የሚበልጡ ሶሪያውያን ስደተኞች ከቱርክ ወደሐገራቸው መግባታቸውን
    10 min

About የዓለም ዜና

From the publisher's feed

ዶይቼ ቬለ የዕለቱን ዋና ዋና ዜናዎች ከኢትዮጵያ እና ከመላው ዓለም በየቀኑ ያቀርባል። የኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ፖለቲካዊ እና ኤኮኖሚያዊ ጉዳዮችን ጨምሮ የመላው ዓለምን ውሎ የተመለከቱ ጠቃሚ መረጃዎች በሰባቱም የሣምንቱ ቀናት ከምሽቱ አንድ ሰዓት ከዶይቼ ቬለ ያድምጡ። የዶይቼ ቬለን ዜናዎች በአፕል ፖድካስት…