የዓለም ዜና

የዓለም ዜና

Download on the App Store

የዓለም ዜና episodes

  • የመጋቢት 14 ቀን 2017 ዓ ም የዓለም ዜና
    ኢትዮጵያ ፤ በኢትዮጵያ እና ናይጄሪያ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ህጻናት የተመጣጠነ ምግብ ያለማግኘት አደጋ ተደቅኖባቸዋል
    ኬንያ፤ ስድስት ፖሊሶች ሲገደሉ አራት ቆሰሉ
    ዩጋንዳ፤ የጦር አዛዡ «ወሳኝ» ያሉዋትን የኮንጎ ከተማ ኪሳንጋኒ ለመቆጣጠር እየሰሩ ነው
    ቱርክ፣ የኢስታንቡል ከንቲባ በመላው ቱርክ ህዝባዊ ተቃውሞ እንዲካሄድ ተማፀኑ
    ኢትዮጵያ ተጨማሪ ሜዳሊያዎችን አሸነፈች
    9 min
  • የመጋቢት 13 ቀን 2017 የዓለም ዜና
    የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት እና የፋኖ ታጣቂዎች ባለፉት ቀናት በተካሔዱ ውጊያዎች በየፊናቸው በመቶዎች መግደላቸውን አስታወቁ። የትግራይ ክልል ሰላም እና ጸጥታ ቢሮ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት በብርጋዲየር ጄኔራል ምግበይ ኃይለ ያቀረበውን ክስ ተቃወመ። ኤርትራውያንን ከኢትዮጵያ ወደ ኬንያ ለማሻገር ሲሞክሩ በቁጥጥር ሥር የዋሉ ሁለት የመከላከያ ሠራዊት አባላት በተከሰሱበት የሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር ጥፋተኛ ሆነው በመገኘታቸው በእስራት እና በገንዘብ ተቀጡ። ጀርመን በደቡብ ሱዳንየሚገኝ ኤምባሲዋን በጊዜያዊነት ዘጋች። የፋታሕ ንቅናቄ የፍልስጤምን ሕልውና ለመታደግ ሐማስ ሥልጣን እንዲያስረክብ ጠየቀ።
    11 min
  • የአርብ መጋቢት 12 ቀን 2017 ዓ.ም. የዓለም ዜና
    የአርብ መጋቢት 12 ቀን 2017 ዓም ዐርዕስተ ዜና
    በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ዎላይታ ዞን የዩኒቨርሲቲ መምህራንና የሕግ ጠበቆችን ጨምሮ ሰዎች በጅምላ እየታፈሱ ነው ሲሉ ነዋሪዎች እና የታሳሪ ቤተሰቦች ለዶቼቬለ ተናገሩ። የከተማይቱ ነዋሪዎች እንደሚሉት ካለፈው ሳምንት ጀምሮ አንዳንዶች ከመኖሪያ ቤታቸው ሌሎች ደግሞ ከመንገድ ላይ እየተያዙ ነው።
    የሱዳን ጦር፣ የመንግስት መቀመጫ የሆነውን የካርቱምን ቤተ መንግሥት መልሶ መቆጣጠሩን ዛሬ አስታወቀ።
    የጀርመን ላዕላይ ምክር ቤት ቡንደስራት ፣በሀገሪቱ የብድር ሕግ ገደብ ላይ ታሪካዊ ማሻሻያ አደረገ።
    9 min
  • የመጋቢት 11 ቀን 2017 ዓ.ም. የዓለም ዜና
    ጠ/ሚ አብይ አህመድ በቀይ ባሕር ወደብ ምክንያት መንግሥታቸው ከኤርትራ ጋር ወደግጭት አይገባም አሉ። የባሕር በር ለኢትዮጵያ የህልውና ጉዳይ ነው ያሉት አቢይ ይህ ግን በሰላማዊ ንግግርና በሰጥቶ መቀበል እንደሚሆን ተናግረዋል።
    የኢትዮጵያ ፓርላማ በሁሉም ሠራተኞች ላይ አዲስ የግብር ዓይነት ይፋ አደረገ። አዲሱ የግብር ዓይነት በመንግሥትም ሆነ በግል ዘርፎች ተቀጥረው በሚሠሩ ላይ ተግባራዊ የሚሆን ነው።
    በሱዳን ዋና ከተማ ኻርቱምና በአካባቢው በርካታ ሲቪሎች በቦምብና በሞርታር እየተገደሉ ነው ሲል የተመድ ዛሬ አስታወቀ።
    የአውሮጳ ሕብረት መሪዎች የአውሮጳን የጦር አቅርም ለማጠናከር ብራስልስ ላይ ተሰባስበው እየመከሩ ነው።
    10 min
  • የመጋቢት 10 ቀን 2017 የዓለም ዜና
    -አንድ ሰሞን ፍቅራቸዉ አለቅጥ ፀንቶ የነበረዉ የአዲስ አበባና የአሥመራ ገዢዎች ጠብ ሰሞኑን የተካረረ መስሏል።የቃላት እንኪያ ሰላምቲያዉ አይሏል።የኢትዮጵያ መንግሥት የሚቆጣጠራቸዉ መገናኛ ዘዴዎች ሥለ ወደብና የባሕር በር ማንሳታቸዉ ያሳሰባት ኤርትራ የኢትዮጵያን ጥያቄ «ሐሰት፣ ኋላ ቀር» እና ለኤርትራ «አስጊ» ብላዋለች።
    -እስራኤል ከፍልስጤሙ ደፈጣ ተዋጊ ቡድን ሐማስ ጋር ያደረገችዉን የተኩስ አቁም ሥምምነት ጥሳ ጋዛ ሰርጥን መደብደቧን ቀጥላለች።---የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕና የሩሲያዉ ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን ትናንት በስልክ ያደረጉት ዉይይትና የደረሱበት መግባባት ድጋፍም ጥርጣሬም አስከትሏል።
    12 min
  • የማክሰኞ መጋቢት 09 ቀን፣ 2017 ዓ.ም የዓለም ዜና
    ባሕር ዳር፥ አማራ ክልል የፆታ ጥቃት ለደረሰባቸው 600 ሴቶች የህክምና ድጋፍ መሰጠቱ ተዘገበ፤ ካርቱም፥ የውኃ ጉድጓድ ውስጥ በጅምላ የተቀበሩ ሰዎች ተገኙ፤ ጁባ፥ በደቡብ ሱዳን ግጭት 50,000 ሰዎች መፈናቀላቸው ተገለጠ፤ ቤርሊን፥ የብድር ገደብን የሚያሻሽለው አዋጅ ድምፅ እንዲሰጥበት ተወሰነ፤ ጋዛ፥ እሥራኤል ከአየር የፈጸመችው ድብደባ ዓለም አቀፍ ውግዘት አስከተለ
    10 min
  • የሰኞ መጋቢት 8 ቀን 2017 ዓ.ም. የዓለም ዜና
    በመጀመሪያም ዋና ዋና ርዕሶቹ
    በእነ አቶ ዮሃንስ ቧያሌው የክስ መዝገብ ላይ ዛሬ የዐቃቤ ሕግ ምስክሮች ምስክርነት መሰማት ጀመረ። በዚህ መዝገብ በሽብር ወንጀል ክስ ከቀረበባቸው 51 ተከሳሾች መካከል 16ቱ ተከሳሾች በተገኙበት ምስክሮች ዛሬ ሰኞ በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሕገ- መንግሥት እና የሽብር ወንጀል ጉዳዮች ችሎት ላይ ምስክርነት ሰጥተዋል።
    የሱዳኑ ፈጥኖ ደራሽ ኃይል በካርቱም መንትያ ከተማ ኦምዱርማን ፈጸመ በተባለው ጥቃት 6 ሰዎች መሞታቸው ተሰማ።
    ዩናይትድ ስቴትስ በየመን ሁቲዎች ላይ ዛሬም የአየር ጥቃት ጣለች።
    12 min
  • የቅዳሜ መጋቢት 6 ቀን 2017 ዓ/ም የዓለም ዜና
    DW Amharic-በአማራ ክልል የታጠቁ ሀይሎች ወደ ምክክር እንዲመጡ መጠየቁ፤የቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል አንድ የምክር ቤት አባል ያለመከሰስ መብት ማንሳቱ፣የደቡብ አፍሪቃ አምባሳደርን ለማባረር አሜሪካ በመወሰኗ እንዳሳዘናቸው ሲርል ራማፎዛ መግለፃቸው፤ማዘኗን መ፣የመገናኛ ብዙኃን ገፅታ እየተቀየረ መምጣት አሳሳቢ መሆኑን የጀርመን ፕሬዚዳንት መግለጻቸው።አሜሪካ የፍልስጤም እስላማዊ ቡድን ሀማስ ታጋቾችን እንዲለቅ ማስጠንቀቋ እና ሩሲያ ለዘላቂ ሰላም' የዩክሬንን የተኩስ አቁም ሀሳብ መደገፍ አለባት ሲሉ የአውሮፓ ኮሚሽን ፕሬዝዳንት መግለፃቸው በዛሬው የዓለም ዜና የተካተቱ ርዕሰ ጉዳዮች ናቸው።
    12 min

About የዓለም ዜና

From the publisher's feed

ዶይቼ ቬለ የዕለቱን ዋና ዋና ዜናዎች ከኢትዮጵያ እና ከመላው ዓለም በየቀኑ ያቀርባል። የኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ፖለቲካዊ እና ኤኮኖሚያዊ ጉዳዮችን ጨምሮ የመላው ዓለምን ውሎ የተመለከቱ ጠቃሚ መረጃዎች በሰባቱም የሣምንቱ ቀናት ከምሽቱ አንድ ሰዓት ከዶይቼ ቬለ ያድምጡ። የዶይቼ ቬለን ዜናዎች በአፕል ፖድካስት…