የዓለም ዜና

የዓለም ዜና

Download on the App Store

የዓለም ዜና episodes

  • የሚያዚያ 1 ቀን 2017 የዓለም ዜና
    -በአማራ ክልል የሚደረገዉ ግጭት የክልሉን የግንባታ ሥራና እንቅስቃሴ ማስተጓጎሉን ባለሙያዎችና ሠራተኞች አስታወቁ።ባለሙያዎች እንዳሉት በግንባታ መስክ የተሰማሩ አብዛኞቹ ባለሐብቶች ወደ አዲስ አበባ ሸሽተዋል።-ባለፈዉ የካቲት ጀርመን ዉስጥ በተደረገዉ ምርጫ የመጀመሪያና ሶስተኛዉን ደረጃ የያዙት የጀርመን የፖለቲካ ፓርቲዎች ተጣማሪ መንግስት ለመመሥረት ተስማሙ።-----ዩናይትድ ስቴትስ ከዓለም የንግድ ተሻራኪዎችዋ ጋር የገጠመችዉ የንግድ ጦርነት እየተባባሰ ነዉ።አንዳድ መንግስታት ከፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር ጋር ለመደራደር ጠይቀዋል።ቻይና ግን በአሜሪካ ሸቀጦች ላይ አፀፋ ቀረጥ ጥላለች።
    12 min
  • የዓለም ዜና፤ መጋቢት 30 ቀን 2017 ዓ.ም
    አርስተ ዜና
    --ጄኔራል ታደሰ ወረደ፤ አቶ ጌታቸው ረዳን በመተካት የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዚዳንት ሆነዉ ተሾሙ። ተሰናባቹ አቶ ጌታቸዉ ረዳ በበኩላቸዉ፤የሁለት ዓመት የጊዜያዊ መስተዳድር ሀላፊነቴን በይፋ አስረክቤያለሁ። የትግራይ ህዝብ ላሳየኝ ክብርና ድጋፍ ላቅ ያለ ምስጋና አቀርባለሁ ብለዋል።--ዩናይትድ ስቴትስና ኢራን የኒውክሌር ድርድር ለመጀመር እቅድ እንደያዙ ገለጹ።--ቻይና የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከቻይና ወደ አሜሪካ በሚገቡ ሸቀጦች ላይ ተጨማሪ ቀረጥ ለመጣል ያቀረቡትን ዛቻ ጭቆና ስትል አጣጣለች። ይህን የጭቆና እርምጃንም እስከመጨረሻዉ እዋጋለሁ ስትል ቻይና ዝታለች።
    12 min
  • የዓለም ዜና፤ መጋቢት 29 ቀን 2017 ዓ.ም
    አርስተ ዜና
    --ጄኔራል ታደሰ ወረደ፤ አቶ ጌታቸው ረዳን በመተካት የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዚዳንት ሆነዉ ተሾሙ። ተሰናባቹ አቶ ጌታቸዉ ረዳ በበኩላቸዉ፤የሁለት ዓመት የጊዜያዊ መስተዳድር ሀላፊነቴን በይፋ አስረክቤያለሁ። የትግራይ ህዝብ ላሳየኝ ክብርና ድጋፍ ላቅ ያለ ምስጋና አቀርባለሁ ብለዋል።--ዩናይትድ ስቴትስና ኢራን የኒውክሌር ድርድር ለመጀመር እቅድ እንደያዙ ገለጹ።--ቻይና የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከቻይና ወደ አሜሪካ በሚገቡ ሸቀጦች ላይ ተጨማሪ ቀረጥ ለመጣል ያቀረቡትን ዛቻ ጭቆና ስትል አጣጣለች። ይህን የጭቆና እርምጃንም እስከመጨረሻዉ እዋጋለሁ ስትል ቻይና ዝታለች።
    17 min
  • የመጋቢት 29 ቀን 2017 ዓ.ም. የዓለም ዜና
    በትግራይ ክልል 1,2 ሚልዮን ሕፃናት እና አዳጊ ልጆች ወደ ትምህርት ገበታ አለመመለሳቸው ተገለጸ። ከዚህም ሌላ በክልሉ የትምህርት ጥራት ላይም ክፍተት መኖሩ ተጠቁሟል።
    በደቡብ አፍሪካ የተባበሩት የኢትዮጵያ ማህበር አንድ አመራር አባል መገደላቸውን የሟች የሥራ ባልደረቦች እና ቤተሰቦች ገለጹ።
    በናይጀሪያዋ ፕላቶ ግዛት ውስጥ ታጣቂዎች ለቀናት ባደረሱት ጥቃት 52 ሰዎችን ገደሉ። ከሁለት ሺህ በላይ ሰዎችም ከመኖሪያ አካባቢያቸው ተፈናቀሉ።
    የአውሮጳ ሕብረት የትራምፕ አስተዳደር የጣለውን አዲሱን ቀረጥ በተመለከተ ከዩናይትድ ስቴትስ ጋር ለመደራደር ዝግጁ መሆኑን አስታወቀ።
    10 min
  • የአርብ መጋቢት 26 ቀን 2017 ዓም የዓለም ዜና
    የአርብ መጋቢት 26 ቀን 2017 ዓም አርዕስተ ዜና
    በአጭበርባሪዎች ተታለው ምያንማር የሄዱ ወጣት ኢትዮጵያውያን ዳግም የድረሱልን ጥሪ አቀረቡ።
    ምሥራቅ ኮንጎ የሚንቀሳቀሰው M23 የተባለው አማጺ ቡድን ከስልታዊቷ ከተማ ዋሊካሌ ለቆ መውጣቱ ተሰማ። የኮንጎ መንግሥትና M23 የመጀመሪያውን ቀጥታ ንግግር ዶሀ ውስጥ የፊታችን ረቡዕ ሊካሂዱ ነው።
    ቤጂንግ ለዩናይትድ ስቴትስ ታሪፍ የአጸፋ ምላሽ ሰጠች። ቻይና ከዩናይትድ ስቴትስ ወደ ሀገርዋ በሚገቡ እቃዎች ላይ ተጨማሪ የ34 በመቶ ታሪፍ መጣሏን ዛሬ አስታውቃለች። ካናዳን የመሳሰሉ ከፍተኛ ታሪፍ የተጣለባቸው ሀገራትም የአጸፋ እርምጃ ለመውሰድ እየተዘጋጁ ነው።
    9 min
  • የዓለም ዜና፤ መጋቢት 25 ቀን 2017 ሃሙስ
    አርስተ ዜና--የግሪክ ባህር ድንበር ላይ አንዲት ስደተኞችን የጫነች ጀልባ ተገልብጣ ሁለት ህጻናትን ጨምሮ የሰባት ሰዎች ህይወት አለፈ።--በአማራ ክልል አንዳንድ አካባቢዎች የኮሌራ በሽታ መከሰቱን የአማራ ክልል ህብረተሰብ ጤና ተቋም አስታወቀ። በቋራና በባህር ዳር ዙሪያ ወረዳዎች 1000 የሚጠጉ ሠዎች በበሽታው ተይጠዋል እስካሁን ዘጠኝ ሰዎች ሞተዋል።-- ትራምፕ ትዮጵያም ወደ አሜሪካ በምትልከዉ ሸቀጦች ላይ የ 10 በመቶ የቀረጥ ጭማሪ ጣሉ።--ዓለምአቀፉ የጦር ወንጀለኞች መዳኛ ፍርድ ቤት የእስር ማዘዣ የቆረጠባቸዉ፣ የእስራኤሉ ጠ/ሚ ቤንያሚን ኔታንያሁ ያለምንም ችግር ቡዳፔስት ገቡ።
    10 min

About የዓለም ዜና

From the publisher's feed

ዶይቼ ቬለ የዕለቱን ዋና ዋና ዜናዎች ከኢትዮጵያ እና ከመላው ዓለም በየቀኑ ያቀርባል። የኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ፖለቲካዊ እና ኤኮኖሚያዊ ጉዳዮችን ጨምሮ የመላው ዓለምን ውሎ የተመለከቱ ጠቃሚ መረጃዎች በሰባቱም የሣምንቱ ቀናት ከምሽቱ አንድ ሰዓት ከዶይቼ ቬለ ያድምጡ። የዶይቼ ቬለን ዜናዎች በአፕል ፖድካስት…