የዓለም ዜና

የዓለም ዜና

Download on the App Store

የዓለም ዜና episodes

  • የሚያዚያ 22 ቀን 2017 የዓለም ዜና
    -ኢትዮጵያ ዉስጥ መብታቸዉን ለማስከበር በሚጠይቁ ሠራተኞች ላይ አሠሪዎች የሚደርሱት ጫናና በደል እንዲቆም የሐገሪቱ የሠራተኛ ማሕበራት ኮንፌደሬሽን ጠየቀ።---የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ፀጥታ አስከባሪዎች ለሱዳን መከላከያ ጦር ሊላክ ነበረ ያሉትን በሚሊዮን የሚቆጠር ጥይት መያዛቸዉ ተነገረ።የሱዳን መከላከያ ጦር ግን የአቡዳቢን መግለጫ በሱዳን ሕዝብ ዓይን ዉስጥ አዋራ ለመሞጀር የተቃጣ ዉሸት በማለት አጣጥሎ ነቅፎታል።---የዩናይትድ ስቴትስ ጦር ሰዓዳ-የመን ዉስጥ ባደረሰዉ የአዉሮፕላን ጥቃት የአፍሪቃ ሥደተኞች የተጠለሉበትን ማቆያ ጣቢያ አወደመ።የየመን ባለሥልጣናት እንዳሉት በድብደባዉ 68 ሰዎች ተገድለዋል።
    12 min
  • የዓለም ዜና፤ ሚያዝያ 21 ቀን 2017 ዓ.ም ማክሰኞ
    አርስተ ዜና
    --ከሰሃራ በታች ባሉ የአፍሪቃ ሃገራት ያሉ የእናቶችና የህጻናትን ጤና ለማሻሻል ያለመ የ500 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ማሰባሰብያ ዛሬ አቡዳቢ ላይ ጀመረ። የተሰበሰበዉ ገንዘብ በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት ኢትዮጵያ፣ ጋና፣ ጨምሮ ከ10 አፍሪቃ ሀገራት ጋር አጋርነት ለመፍጠር ያለመ ነዉ።--ዓለምአቀፉ ማህበረሰብ በዓለም አቀፍ ደረጃ ሰብአዊ መብቶችን መጠበቅ አልቻለም ሲል የዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርግት አምነስቲ ኢንተርናሽናል ከሰሰ።--የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ለሁለተኛ ጊዜ ስልጣን ከያዙ ዛሬ 100 ኛ ቀናቸዉን ደፈኑ።
    10 min
  • የሚያዝያ 20 ቀን 2017 ዓ.ም. የዓለም ዜና
    የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) «ኤርትራ ሀገር ሆና የተመሰረተችበት ሂደት ቅቡልነት ላይ ጥያቄ አለኝ» አለ።
    የቱኒዚያ የባሕር ጠረፍ ጠባቂዎች ስደኞችን አሳፍራ ወደ አውሮጳ ስትጓዝ የመስመጥ አደጋ ከደረሰባት ጀልባ 29ኙን አተረፉ። ጠባቂዎቹ በዛሬው ዕለት የስምንት አፍሪቃውያን ስደተኞችን አስከሬን ማግኘታቸውን ገልጸዋል።
    ሃገራት በከፍተኛ ፍጥነት የጦር ኃይላቸውን እያስታጠቁ መሆኑን አንድ የጥናት ተቋም አስታወቀ። የስቶክሆልም የሰላም ምርምር ኢንስቲትዩት (SIPRI ) እንደሚለው በግጭቶች ጦርነቶች ምክንያት ወታደራዊ ወጪው በዓለም አቀፍ ደረጃ በ9.4 በመቶ ከፍ ብሏል።
    9 min
  • DW Amharic የሚያዝያ 19 ቀን 2017 የዓለም ዜና
    ርዋንዳ በሙስና እና ሥልጣን ያለአግባብ በመጠቀም የጠረጠረቻቸውን ሦስት ባለሥልጣናት አሰረች። በኢራን ሻሒድ ራጃኢ ወደብ ላይ በተከሰተ ፍንዳታ የሞቱ ሰዎች ቁጥር ወደ 40 አሻቀበ። በካናዳ ቫንኮቨር ከተማ በሚኖሩ የፊሊፒንስ ዜጎች መርሐ-ግብር ላይ አንድ ግለሰብ ተሽከርካሪ ነድቶ ዘጠኝ ሰዎች ገደለ። የእስራኤል ጦር በቤይሩት ደቡባዊ ክፍል የሚኖሩ ሰዎች ለቀው እንዲወጡ አስጠነቀቀ። ሩሲያ የዩክሬን ጦር ሠራዊት፣ የውጪ ተዋጊዎች እና በአውሮፓ የተላኩ ወታደራዊ አሰልጣኞች የሚጠቀሙባቸው ዒላማዎች ላይ ጥቃት መፈጸሟን እንደምትቀጥል አስታወቀች። በለንደን ማራቶን ኢትዮጵያዊቷ ትዕግሥት አሰፋ የዓለም የሴቶች ክብረ-ወሰን በማሻሻል አሸነፈች
    8 min
  • DW Amharic የሚያዝያ 16 ቀን 2017 የዓለም ዜና
    የኢትዮጵያ ሪፖርተር ጋዜጣ አበበ ፍቅር የተባለ ዘጋቢው የክፍለ ከተማ ኃላፊዎች ለማነጋገር ሲሞክር መታሰሩን አስታወቀ። ኬንያ እና ቻይና ግንኙነታቸውን ወደ አዲስ ደረጃ ለማሳደግ እና የንግድ እንቅፋቶችን ለመቃወም ተስማሙ። በመሐመድ ሐምዳን ደጋሎ በሚመራው የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይል ተመሠረተ የተባለውን ትይዩ መንግሥት ግብጽ እና ጅቡቲ ተቃወሙ። እስራኤል በጋዛ ሠርጥ በምትገኘው ጃባሊያ በአንድ ፖሊስ ጣቢያ ሐሙስ ላይ በፈጸመችው ጥቃት ቢያንስ አስር ሰዎች ተገደሉ። የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ሩሲያ በዩክሬን የምትፈጽማቸውን ጥቃቶች እንድታቆም ጥሪ አቀረቡ።
    11 min
  • የሚያዚያ 15 ቀን 2017 ዓ.ም. የዓለም ዜና
    የሚያዚያ 15 ቀን 2017 ዓ.ም. አርዕስተ ዜና
    በምስራቅ ወለጋ ዞን ኪረሙ ወረዳ ትናንት ታጣቂዎች በፈጸሙት ጥቃት የሚሊሻ አባላትን ጨምሮ 15 ሰዎች መገደላቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናገሩ፡፡ በጥቃቱ ከባድ መሣሪያዎችም ጥቅም ላይ መዋላቸውንም ለዶቼቬለ ተናግረዋል።
    ጅቡቲ ሕገ ወጥ ስደተኞችን በቅርቡ ማባረር እንደምትጀምር አስታወቀች። ስደተኞቹ እስከሚቀጥለው ሳምንት ድረስ ሀገሪቱን ለቀው እንዲወጡ የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር አዟል።
    የፍልስጤም ፕሬዝዳንት መሐሙድ አባስ ሀማስ ጋዛ ውስጥ የያዛቸውን ታጋቾች በሙሉ እንዲለቅ ጠየቁ። ታጋቾቹን ይዞ መቆየቱ እስራኤል በፍልስጤም ጥቃቷን እንድትቀጥል ሰበብ ሆኗታል ብለዋል።
    11 min

About የዓለም ዜና

From the publisher's feed

ዶይቼ ቬለ የዕለቱን ዋና ዋና ዜናዎች ከኢትዮጵያ እና ከመላው ዓለም በየቀኑ ያቀርባል። የኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ፖለቲካዊ እና ኤኮኖሚያዊ ጉዳዮችን ጨምሮ የመላው ዓለምን ውሎ የተመለከቱ ጠቃሚ መረጃዎች በሰባቱም የሣምንቱ ቀናት ከምሽቱ አንድ ሰዓት ከዶይቼ ቬለ ያድምጡ። የዶይቼ ቬለን ዜናዎች በአፕል ፖድካስት…