የዓለም ዜና

የዓለም ዜና

Download on the App Store

የዓለም ዜና episodes

  • የግንቦት 23 ቀን 2017 ዓ ም የዓለም ዜና
    *ዲሞክራሲያዊ ስምረት ትግራይ በቀጣዩ ሀገራዊ ምርጫ እንደሚሳተፍ አስታወቀ
    *ፖላንድ ኢትዮጵያን ጨምሮ በስድስት ሀገራት ህገ ወጥ ስደተኞች ላይ ጠንካራ የግንዛቤ ማስጨበጫ ዘመቻ ጀመረች
    *በደቡብ ሱዳን ላይ የተጣለውን የጦር መሣሪያ ግዢ ማዕቀብ አራዘመ
    *ናይጄሪያ ውስጥ በጎርፍ አደጋ የሞቱት ሰዎች ቁጥር ከ 150 አለፈ
    *የተራቡ ፍልስጤማውያን የርዳታ ምግብ ዘረፉ
    *ኢራን የተብላለ የዩራንየም ክምችቷን 60 በመቶ አደረሰች
    12 min
  • የግንቦት 22 ቀን 2017 የዓለም ዜና
    ከአዲስ አበባና ከሌሎች የመሐል ኢትዮጵያ ግዛቶች ሸቀጦች ጭነዉ ወደ ትግራይ ይጓዙ የነበሩ የጭነት መኪኖች አፋርና አማራ ክልል በሚገኙ የፍተሻ ጣቢያዎች መታገዳቸዉን ሾፌሮች አስታወቁ።---የአሜሪካዉ አዉሮፕላን አምራች ኩባንያ ቦይንግ ኢንዶኔዢያና ኢትዮጵያ ዉስጥ በደረሱ አደጋዎች ሰበብ የተመሠረተበት ክስ ሊነሳለት ነዉ።ክሱ የሚነሳዉ ቦይንግ 1.1 ቢሊዮን ዶላር ለመክፈል በመስማማቱ ነዉ።-እስራኤል ለጋዛ ሕዝብ ሰብአዊ ርዳታ እንዳይደርስ ማገዷን እንድታቆም የሚደረግባት ግፊት እንደቀጠለ ነዉ።የእስራኤል መከላከያ ሚንስትር ግን መንግሥታቸዉ ምዕራባዊ ዮርዳኖስ ወንዝ ዳርቻ የአይሁዳዊ የእስራኤል መንግሥት እንደሚመሠርት ዝተዋል።
    12 min
  • የግንቦት 21 ቀን 2017 ዓ ም የዓለም ዜና
    *የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በኢሳያስ አፈወርቂ ወቀሳ ላይ ምላሽ ሰጠ
    *የግብፁ ፕሬዚዳንት አልሲሲ ብርቱ ተፎካካሪ ከስር ተፈቱ
    * ናይጄሪያ ውስጥ በሁለት አመታት ውስጥ ከ 10 000 በላይ ሰዎች ተገደሉ
    *«እስራኤል በጋዛ የጦር ወንጀል እየፈፀመች ነው» የቀድሞ የእስራኤል ጠ/ሚነስትር
    *ኤሎን ማስክ ለትራምፕ መስራታቸውን ሊያቆሙ ነው
    *የዩናይትድ ስቴትስ ለአለም አቀፍ ተማሪዎች ቪዛ ላለመስጠት መወሰኗ ቁጣ ቀሰቀሰ
    11 min
  • የግንቦት 20 ቀን 2017 ዓ.ም. የዓለም ዜና
    የደርግ ሥርዓት ከኢትዮጵያ የመንግሥት ሥልጣን ከተወገደ ዛሬ 34 ዓመቱን ደፈነ። ከሦስት አስርት ዓመታት በላይ በብሔራዊ በዓልነት ይታሰብ የነበረው ግንቦት 20 በሌሎች የኢትዮጵያ ክፍሎች መደበኛ የሥራ ቀን ሆኖ ሲያልፍ ትግራይ ክልል ግን በደመቀ ሥርዓት ተከብሯል።
    ፖርት ሱዳንን ጨምሮ በሱዳን ጦር ኃይል የተያዙ አካባቢዎች ላይ የሰው አልባ አውሮፕላን ጥቃት መፈጸሙ ተዘገበ።
    የኢራን አብዮታዊ ዘብ አዛዥ ዩናይትድ ስቴትስን አስጠነቀቁ።
    የፈረንሳይ ፍርድ ቤት በአብዛኛው ለአካለ መጠን ያልደረሱ ሕጻናትን ጨምሮ ወደ 300 ገደማ ህሙማን ላይ በደል በፈጸመ የቀዶ ህክምና ባለሙያ ላይ የ20 ዓመት እስራት ፈረደ።
    10 min
  • የዓለም ዜና፤ ግንቦት 19 ቀን 2017
    አርስተ ዜና
    የጀርመኑ መራሔ መንግሥት ፍሬድሪክ ሜርስ ስራኤል በጋዛ እየፈፀመች ያለዉ ድርጊት «ትክክል ያልሆነ» ሲሉ ወቀሱ። በሌላ በኩል ጀርመንን ጨምሮ ቁልፍ ምዕራባዉያን የዩክሪን ደጋፊዎች ለዩክሪን በሚልኩት የጦር መሳርያ ላይ የተጣለ ገደብን አነሱ።--በእነአቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራ ዴሞክራሲያዊ ስምረት ትግራይ የተሰኘ አዲስ የፖለቲካ ፓርቲ በምርጫ ቦርድ ግዚያዊ የምዝገባ ፍቃድ አገኘ።--በጦርነት በተመሰቃቀለችዉ ሱዳን በኮሌራ በሽታ የተያዘዉ ሰዉ ቁጥር መጨመሩን የጤና ጥበቃ ሚ/ር አስታወቀ።--የሩሲያ ወታደራዊ አውሮፕላኖች የፊንላንድ የአየር ክልልን ጥሰዋል ከተባለ በኋላ ፊንላንድ የሩሲያን አምባሳደር ለጥያቄ ጠራች።
    12 min
  • የግንቦት 18 ቀን 2017 ዓ.ም. የዓለም ዜና
    በጋምቤላ ክልል ዲማ ወረዳ ታጣቂዎች በአንድ አውቶብስ ላይ ባደረሱት ጥቃት አምስት ሰዎች ተገደሉ። ሌሎች ስድስት ሰዎችም ተጎድተዋል። ጥቃት አድራሾቹ ከደቡብ ሱዳን የመጡ የሙርሌ ታጣቂዎች መሆናቸው ተገልጿል።
    የግሪክ ባሕር ኃይል ከ500 በላይ ስደተኞችን ከመስመጥ ማዳኑን የሀገሪቱ ባለሥልጣናት ገለጹ።
    ዩጋንዳ ከጀርመን ጋር መከላከያን በተመለከተ ያላትን ትብብር ማቋረጧን አስታወቀች።
    የእስራኤል መንግሥት በቅርቡ ጋዛ ላይ የተኩስ አቁም እንዲደረግ የቀረበለትን ጥያቄ ውድቅ ማድረጉ ተነገረ። ሃገራት እስራኤል ጋዛ ላይ የምትወስደውን የኃይል እርምጃ እንድታቆም እየጠየቁ ነው።
    9 min
  • DW Amharic የግንቦት 17 ቀን 2017 የዓለም ዜና
    በኢትዮጵያ “ኤምፖክስ” ተብሎ በሚጠራው የጦጣ ፈንጣጣ የተያዘ ሰው መገኘቱን የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ። ፕሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂ የኤርትራ መንግሥት እና ሕዝብ ለኢትዮጵያ “ተሐድሶ ወይም ለውጥ በከፍተኛ ተስፋ ባደረጉት ያልተቆጠበ ድጋፍ ድንገት በተፈጠሩ ክስተቶች ምክንያት እንደማይቆጩ” ተናገሩ። በጋዛ በአንድ ቀን 38 ሰዎች በእስራኤል ጥቃቶች መገደላቸውን የሐማስ የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ። ሩሲያ እና ዩክሬን በሦስት ዙር ያካሔዱትን የጦር ምርኮኞች ልውውጥ አጠናቀቁ። የጀርመን የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር አሌክሳንደር ዶብሪንት የተወሰኑ ስደተኞች ቤተሰቦቻቸውን ወደ ጀርመን ከማምጣት የሚከለክል ሕግ እየተዘጋጀ መሆኑን አረጋገጡ።
    9 min
  • DW Amharic የግንቦት 16 ቀን 2017 የዓለም ዜና
    አፍሪካ በማዕድናት፣ በሚታረስ መሬት እና በኢንዱስትሪ ያላትን እምቅ ሀብት ለዛሬውም ሆነ ለወደፊቱ ትውልድ ሲባል መጠበቅ እንደሚያስፈልግ የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀ-መንበር አሳሰቡ። ፕሬዝደንት ኢስማኤል ዑመር ጉሌሕ በሚያዝያ 2018 በሚካሔደው የጅቡቲ ምርጫ ሊወዳደሩ እንደሚችሉ በገደምዳሜ ፍንጭ ሰጡ። በኬንያ ዋና ከተማ ናይሮቢ ማኪና በተባለ አካባቢ በተቀሰቀሰ የእሳት ቃጠሎ ቢያንስ ስምንት ሰዎች ሕይወታቸውን አጡ። በእስራኤል ጥቃት የተገደሉ የ79 ሰዎች አስከሬኖች ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ ወደ ሆስፒታሎች መድረሳቸውን የጋዛ የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።
    9 min
  • የዐርብ ግንቦት 15፣ ቀን 2017 ዓ.ም የዓለም ዜና
    ቤኒሻንጉል፥ በካማሺ ዞን ምዥጋ ወረዳ የታጣቂዎች ጥቃት፤ ለንደን፥ አምነስቲ ኢንተርናሽናል፦ የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት ከጤና ባለሞያዎች ጋር በአሰቸኳይ ሊነጋገሩ ይገባል አለ፤ አአ፥ ዩናይትድ ስቴትስ ኢትዮጵያ ውስጥ ሕዝቡን እየጎዳ ላለው ግጭት መፍትሄ እንዲፈለግ አሳሰበች፤ ጋምቤላ፥ ኢትዮጵያ የሚገኙ የደቡብ ሱዳን ስደተኞች «የጤና ቀውስ» የማይቀር ነው ተባለ፤ ዋሽንግተን፥ ትራምፕ የአውሮጳ ኅብረት ሸቀጦች ላይ የ50 በመቶ ቀረጥ ሊጥል ነው፤ ዩክሬን እና ሩስያ ከዚህ ቀደሙ ከፍተኛ የሆነ የእስረኛ ልውውጥ አደረጉ ።
    10 min
  • የግንቦት 14 ቀን 2017 ዓ,ም የዓለም ዜና
    የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ከደመወዝ ጭማሪ ጋር በተገናኘ የህክምና ባለሙያዎች ለሚወስዱት እርምጃ የሚሰጠው ምላሽ ወደ መብት ጥሰት ማምራት እንደሌለበት አሳሰበ።
    በአሜሪካ የእስራኤል ኤምባሲ ሁለት ሠራተኞች ዋሽንግተን ዲሲ ላይ መገደላቸው የተለያዩ ሃገራትን ውግዝት አስከተለ። እስራኤል መንስኤው ጸረ ሴማዊነት ነው ብላለች።
    የእስራኤል መንግሥት ዶሀ ቀጠር በመካሄድ ላይ ከሚገኘው የጋዛ የተኩስ አቁም ድርድር መውጣቱ እየተነገረ ነው።
    የጀርመን አቀብያነ ሕግ የሁቲ አማፂ ቡድን አባል ሳይሆን አቅርም በሚል ተጠረጠረ ግለሰብን በዛሬው ዕለት በቁጥጥር ሥር ማዋላቸውን ገለጹ።
    10 min

About የዓለም ዜና

From the publisher's feed

ዶይቼ ቬለ የዕለቱን ዋና ዋና ዜናዎች ከኢትዮጵያ እና ከመላው ዓለም በየቀኑ ያቀርባል። የኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ፖለቲካዊ እና ኤኮኖሚያዊ ጉዳዮችን ጨምሮ የመላው ዓለምን ውሎ የተመለከቱ ጠቃሚ መረጃዎች በሰባቱም የሣምንቱ ቀናት ከምሽቱ አንድ ሰዓት ከዶይቼ ቬለ ያድምጡ። የዶይቼ ቬለን ዜናዎች በአፕል ፖድካስት…