የዓለም ዜና

የዓለም ዜና

Download on the App Store

የዓለም ዜና episodes

  • የሰኔ 13 ቀን 2017 የዓለም ዜና
    -የኢጣሊያና የአዉሮጳ ሕብረት መሪዎች የአፍሪቃ ሥደተኞችን ለመግታት ለተለያዩ የአፍሪቃ ሐገራት ሊሰጥ ሥለታቀደዉ ርዳታ ዛሬ ተነጋገሩ።---የሥደተኞችን ቁጥር ለመቀነስ የአዉሮጳ ሕብረት ኢትዮጵያን ጨምሮ ለ14 የአፍሪቃ ሐገራት 5.5 ቢሊዮን ዩሮ ይሰጣል።---የእስራኤልና የኢራን የጦር ሜዳ ዉጊያ የዲፕሎማሲ እንኪያ ሰላንቲያም ዛሬም እንደመሰንበቻዉ ቀጥሎ ዉሏል።የእስራኤል ጦር የኢራን የሚሳዬል ማወንጨፊያዎችን ጨምሮ የተለያዩ ተቋማትን መደብደቡን አስታዉቋል።የኢራን ሚሳዬሎችም ዛሬ በእስራኤል ግዛቶች ላይ ሲዝንቡ ነዉ የዋሉት።-በዲፕሎማሲዉ መስክ የኢራንና የሶስት የአዉሮጳ ሐገራት ዉጪ ጉዳይ ሚንስትሮች እየተነጋገሩ ነዉ።
    12 min
  • የሰኔ 12 ቀን 2017 ዓ.ም. የዓለም ዜና
    *በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ወለጋ ዞን 17 ንጹሀን ዜጎች በታጣቂዎች ተገደሉ
    *ፍርድ ቤት የቀድሞው የሀዋሳ ከተማ ከንቲባን በነጻ አሰናበተ
    *ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ እና ሩዋንዳ የሰላም ስምምነት ሊፈራረሙ ነው
    *እስራኤል በኢራን ላይ የአፀፋ ርምጃ እንደምትወስድ አሳሰበች
    *ዜጎችን ከእስራኤል እና ኢራን የማስወጣት ርምጃው ቀጥሏል
    *ሩሲያ ጀርመንን አስጠነቀቀች
    11 min
  • የሰኔ 11 ቀን 2017 ዓ.ም. የዓለም ዜና
    በአማራ እና ትግራይ ክልሎች የሚገኙ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች መንግሥት ወደየቀያቸው እንዲመልሳቸው ጠየቁ።
    የትራምፕ አስተዳደር ዜጎቻቸው ላይ የጉዞ እገዳ እንዳይጣል ተገቢውን ማጣሪያ እንዲያደርጉ ለ36 ሃገራት ማሳሰቢያ ሰጠ። ማሳሰቢያው ከደረሳቸው 25ቱ የአፍሪቃ ሃገራት ሲሆኑ ኢትዮጵያ አንዷ ናት።
    እስራኤል ሁለት የኢራን የኒኩሊየር ማብላያ የሚገኝባቸው ሕንጻዎች አወደመች። ኢራን በአሜሪካ ድጋፍ ተደርጓል ላለችው ጥቃት የምትመልሰው አጸፋ የከፋ እንዲሚሆን ዝታለች። እስራኤል ለጥቃቱ ከ50 በላይ ተዋጊ ጀቶችን ማሰለፏን አስታውቃለች ።
    12 min
  • የዓለም ዜና፤ ሰኔ 10 ቀን 2017 ዓ.ም ማክሰኞ
    አርስተ ዜና፤
    --ኤርትራዉያን ስልታዊ የመብት ጥሰት እየደረሰባቸዉ መሆኑን የመንግሥታቱ ድርጅት አጋለጠ።
    --በእስራኤል የሚገኘው የቻይና ኤምባሲ በሀገሪቱ የሚገኙ የቻይና ዜጎች በሙሉ እስራኤልን በድንበር በኩል አቋርጠው እንዲወጡ አሳሰበ። በሌላ በኩል እስራኤል በኢራን ላይ የምታካሂደዉ ጥቃት በመቀጠሉ ጋና ዜጎቿን ከኢራን ማስወጣት ጀመረች።
    --ቡድን ሰባት በመባል የሚታወቁት ሰባቱ የበለፀጉት ሀገራት መሪዎች ትናንት ካናዳ ላይ የጀመሩትን ጉባኤ ዛሬ ለሁለተኛ ቀን እንደቀጠሉ ነዉ።--ፕሬዚዳንት ትራምፕ በበኩላቸዉ በመካከለኛዉ ምስራቅ ቀዉስን ተከትሎ አቋርጠዉ ወደ አገራቸዉ ተመልሰዋል።
    13 min
  • የሰኔ 9 ቀን 2017 ዓ.ም. የዓለም ዜና
    ኢራንና እስራኤል ዛሬም ለአራተኛ ቀን አንዳቸው በሌላኛቸው ላይ የሚሳይል ጥቃቶችን መፈጸማቸውን ቀጥለዋል። ኢራን ዛሬም ወደተለያዩ የእስራኤል ከተሞች ባስወነጨፈቻቸው ሚሳይሎች በደረሱ ጥቃቶች 11 ሰዎች ተገድለዋል።
    የተ።መ የሰብዓዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽነር የጋዛ ጦርነት እንዲያበቃ ግፊት እንዲደረግ ጥሪ አቀረቡ። ኮሚሽነር ፎልከር ቱርክ ሁሉም ከተኛበት ነቅቶ ግጭቱን ለማስቆም በእስራኤልና በሀማስ ላይ ግፊቱን እንዲያጠናክር ጠይቀዋል።
    ቡድን ሰባት የሚባለው የዓለም ባለፀጋ ሀገራት ስብስብ የመሪዎች ጉባኤ በካናዳዋ በካናናስኪስ ከተማ ውስጥ ዛሬ ከጥቂት ሰዓታት በኋላ ይጀምሯል።
    11 min
  • DW Amharic የሰኔ 08 ቀን 2017 የዓለም ዜና
    በዶናልድ ትራምፕ የሚመራው የዩናይትድ ስቴትስ አስተዳደር ኢትዮጵያን ጨምሮ 36 ሀገራትን የጉዞ ዕቀባ ከጣለባቸው ጎራ የማካተት ዕቅድ አለው ተባለ። በጋዛ ሠርጥ በእስራኤል እና በአሜሪካ ድጋፍ ምግብ በሚታደልበት ቦታ በተከፈተ ተኩስ ስምንት ሰዎች መገደላቸውን ባለሥልጣናት አስታወቁ። እስራኤል እና ኢራን አንዳቸው በሌላቸው ላይ በፈጸሟቸው ጥቃቶች የተገደሉ ሰዎች ቁጥር ጨመረ። የጀርመን መራኄ መንግሥት ኦላፍ ሾልስ በቡድን ሰባት ሀገራት ስብሰባ ላይ የእስራኤል እና የኢራንን ግጭት ለማቆም በአራት ጉዳዮች ላይ ከሥምምነት ይደረሳል የሚል ተስፋ እንዳላቸው አስታወቁ። በሰሜናዊ ሕንድ ሔሊኮፕተር ተከስክሶ የሰባት ሰዎች ሕይወት አለፈ።
    9 min
  • የሰኔ 7 ቀን 2017 ዓ.ም. የዓለም ዜና
    *ደቡብ አፍሪቃ በጎርፍ አደጋ ቢያንስ 86 ሰዎች ሞቱ
    *እስራኤል እና ኢራን ውጥረት ቀጥሏል
    *የአሜሪካ ድምጽ አገልግሎት የፋርስ ቋንቋ ስርጭቱን መልሶ ጀመረ
    *ከትራምፕ 79ኛ የልደት ቀን ጋር የተገጣጠመው የዩናይትድ ስቴትስ ጦር 250ኛ ዓመት
    *የሸንገን ስምምነት 40 ዓመት ሞላው
    *ሩሲያ ተጨማሪ 1,200 የዩክሬን ወታደሮች አስክሬን መለሰች
    11 min
  • የሰኔ 6 ቀን፣ 2017 ዓ.ም የዓለም ዜና
    ሞያሌ፥ ኢትዮጵያ ውስጥ በኤምፖክስ የተያዙ 19 ደረሱ፣ ካርቱም፥ ሱዳን እና ቻድ ስደተኛ መጠለያዎች ውስጥ ኮሌራ ወረሺኝ እየተዛመተ ነው፣ አ.አ፥ ጋዜጠኛ ተስፋለም ወልደየስ ከእሥር መፈታቱን ሐቅ ሚዳያ ዐሳወቀ፣ ቴሕራን፥ ኢራን በእሥራኤል ከተደበደበች በኋላ 100 ድሮኖችን እሥራኤል ውስጥ ተኩስ ከፈቱ፣ ዋሽንግተን፥ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ፦ «ሁሉም ነገር ከማክተሙ በፊት ኢራን መደራደር አለባት» ሲሉ አስጠነቀቁ»፣ ዓለምአቀፍ፥ ከእሥራኤል የኢራን ጥቃት በኋላ በርካታ በረራዎች ተሰረዙ፣ አህመዳባድ፥ ከአውሮፕላን አደጋው አንድም ሰው መትረፉ ተዓምር ነው ተባለ
    12 min
  • የሰኔ 5 ቀን 2017 ዓ,ም የዓለም ዜና
    የሲዳማ ክልል ምክር ቤት የክልሉ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ የነበሩትን የአቶ አለማየሁ ጢሞቲዮስን ያለመከሰስ መብት አነሳ።
    የአዲስ አበባ ሰበር ሰሚ ችሎት የጋዜጠኛ ተስፋለም ወልደየስ የዋስትና መብት እንዲጠበቅ ወሰነ።
    ከሕንድ ወደ ለንደን ለመጓዝ 242 መንገደኞችን አሳፍሮ የተነሳው አውሮፕላን በደቂቃዎች ውስጥ ተከስክሶ በርካቶች መሞታቸው ተሰማ።
    የአውሮጳ ሕብረት ኢራን የኒኩሊየር ጦር መሳሪያ እንዳይመረት የሚያግደዉንና የተቀበለችዉን ግዴታ እንድታከብር ጠየቀ።
    12 min
  • የሰኔ 4ቀን 1017 የዓለም ዜና
    -መቀሌ ዉስጥ ዛሬ አደባባይ የተሰለፉ የትግራይ ተፈናቃዮች የክልሉ ፕሬዝደንት ፅሕፈት ቤት የሚገኝበትን ቅጥር ግቢ ጥሰዉ ገቡ።ከቤት ንብረታቸዉ የተፈናቀሉ ነዋሪዎች ወደቀያቸዉ እንዲመለሱ በተደጋጋሚ በአደባባይ ሠልፍ እየጠየቁ ነዉ።---የኢትዮጵያ መንግስት የሕግ ሒደትንም ሆነ የፕሬስ ነፃነትን እንደማያከብር ሁለት የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ድርጅቶች አስታወቁ።--ዩናይትድ ስቴትስ ኢራንን ካጠቃች የኢራን ጦር መካከለኛዉ ምሥራቅ የሚገኙ የአሜሪካ ጦር ሠፈሮችን እንደሚመታ የኢራን መከላከያ ሚንስትር አስጠነቀቁ።
    11 min

About የዓለም ዜና

From the publisher's feed

ዶይቼ ቬለ የዕለቱን ዋና ዋና ዜናዎች ከኢትዮጵያ እና ከመላው ዓለም በየቀኑ ያቀርባል። የኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ፖለቲካዊ እና ኤኮኖሚያዊ ጉዳዮችን ጨምሮ የመላው ዓለምን ውሎ የተመለከቱ ጠቃሚ መረጃዎች በሰባቱም የሣምንቱ ቀናት ከምሽቱ አንድ ሰዓት ከዶይቼ ቬለ ያድምጡ። የዶይቼ ቬለን ዜናዎች በአፕል ፖድካስት…