የዓለም ዜና

የዓለም ዜና

Download on the App Store

የዓለም ዜና episodes

  • የሐምሌ 11 ቀን 2017 ዓ.ም. የዓለም ዜና
    የሐምሌ 11 ቀን 2017 ዓ.ም. አርዕስተ ዜና
    መንግሥት የሠራተኞች ዝቅተኛ የደሞዝ ወለል ተግባራዊ እንዲያደርግ የኢትዮጵያ ኤኮኖሚክስ አሶስየሽን ማኅበር ጠየቀ።
    ዩናይትድ ስቴትስ ወደ ደቡብ አፍሪቃዊቷ ሀገር ኤስዋቲኒ የጠረዘቻቸው 5 ስደተኛ እስረኞች ላልተወሰነ ጊዜ በተለየ ቦታ ለብቻቸው ተይዘው እንደሚቆዩ የኤስዋቲኒ መንግሥት ዐሳወቀ።
    የአውሮጳ ኅብረት በዩክሬኑ ጦርነት ምክንያት ለ18ተኛ ጊዜ በሩስያ ላይ ዛሬ አዳዲስ ማዕቀቦች ጣለ። በተለይ በሩስያ ነዳጅ ዘይት ላይ የተጣለውን ማዕቀብ የሚያካትተው የአዲሱ ማዕቀብ ዓላማ በሩስያ ላይ ግፊቱን ጠናከር ነው ተብሏል።
    11 min
  • የሐምሌ 9 ቀን 2017 ዓ.ም. የዓለም ዜና
    በአማራ ክልል ምዕራብ ጎጃም ዞን ደጋ ዳሞት ወረዳ ፈረስ ቤት ከተማ ትናንት በመንግሥት ኃይሎች እና በፋኖ መካከል ከፍተኛ ውጊያ እንደነበር ተሰማ።
    እራሱን እስላማዊ መንግሥት የሚለው ጽንፈኛ ቡድን አባላት መሆናቸው የተጠረጠ 82 ግለሰቦችን በቁጥጥር ሥር ማዋሉን የብሔራዊ የስለላና የደኅንነት አገልግሎት ዐሳወቀ።
    በአፋር ክልል አፍዴራ ከተማ ትናንት ምሽት የጣለዉ ብርቱ ንፋስ የቀላቀለ ዝናብ ለአንድ ሰዉ ሕይወት መጥፋት ምክንያት ሆነ፤ 31 ሰዎችም ተጎዱ። በሺህዎች የሚቆጠሩም ተፈናቅለዋል።
    የኬንያ መንግሥት ለበርካታ የአፍሪቃ እና የካሬቢያን ሃገራት የይለፍ ፈቃድ መስፈርቶችን አነሳ።
    10 min
  • የዓለም ዜና ፤ ሐምሌ 8 ቀን 2017 ማክሰኞ
    አርስተ ዜና፤
    -የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ እንደ ቻይና እና ህንድ ባሉት የሩሲያ የንግድ አጋሮች ሸቀጥ ላይ እስከ 100 በመቶ የሚደርስ የትራፊ ጭማሪ እጥላለሁ አሉ። የሩሲያ ባለሥልጣናት ግን ይህ እርምጃ ጦርነቱን ከማስቀጠል በቀር ምንም የሚፈይደዉ ነገር የለም ሲሉ አጣጣሉት አጣጥላዋለች።-ድንበር የለሽ ሐኪሞች ድርጅት የተባለዉ ግብረ ሠናይ ድርጅት የዛሬ አራት ዓመት ትግራይ ክልል ዉስጥ ሆነ ተብሎ ስለተገደሉ ሦስት ባልደረቦቹ አሟሟት ያደረገዉን የዉስጥ ምርመራ ዉጤት ዛሬ በይፋ አሰራጨ።-በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን ከ80 ሺህ በላይ ነዋሪዎች በኦሞ ወንዝ ሙላት መከባባቸውን ነዋሪዎች ገለፁ፡፡
    11 min
  • የሐምሌ 7 ቀን 2017 ዓ.ም. የዓለም ዜና
    የሐምሌ 7 ቀን 2017 ዓ.ም. አርዕስተ ዜና
    ሊቢያ ውስጥ በወሮበሎች ተይዘው ሲሰቃዩ የነበሩ ከ100 በላይ ስደተኞች ነጻ መውጣታቸውን ሊቢያ አስታወቀች።ከመካከላቸው 5 ሴቶች ይገኙባቸዋል።
    የአውሮጳ ኅብረት ከዋሽንግተን ጋር የሚያካሂደው የታሪፍ ንግግር ክልተሳካ 72 ቢሊዮን ዩሮ የሚያወጡ የአሜሪካን ምርቶች የታሪፍ ጭማሪ ዒላማ ሊሆኑ እንደሚችሉ አስጠነቀቀ።
    ባለፉት ሁለት ወራት ስፔን ውስጥ ከፍተኛ ሙቀት 1,180 ሰዎችን መግደሉን የሀገሪቱ የአካባቢ ሚኒስቴር አስታወቀ። እንደ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ እንዳለው ከሟቾቹ አብዛኛዎቹ እድሜያቸው ከ65 ዓመት በላይ ነው። ከግማሽ በላይ የሚሆኑት ደግሞ ሴቶች ናቸው።
    11 min
  • የሐምሌ 06 ቀን 2017 የዓለም ዜና
    ናይጄሪያ የሽብር እንቅስቃሴ በገንዘብ ይደግፋሉ ያለቻቸውን 44 የቦኮ ሐራም አባላት እስከ 30 ዓመታት በሚደርስ እስራት ቀጣች። በጋዛ ሕጻናትን ጨምሮ ውኃ ለመቅዳት በመጠባበቅ ላይ የነበሩ 10 ፍልስጤማያውን በተፈናቃዮች መጠለያ ውስጥ በእስራኤል የአየር ጥቃት መገደላቸውን የግዛቲቱ የሲቪል ሰዎች ደህንነት ጥበቃ ኤጀንሲ አስታወቀ። የሰሜን ኮሪያ መሪ ኪም ጆንግ ዑን ሩሲያ በዩክሬን ያለውን ግጭት ለመፍታት የምታደርገውን ጥረት ሀገራቸው “ያለ ምንም ቅድመ-ሁኔታ ለመደገፍ” ዝግጁ እንደሆነች ማረጋገጫ ሰጡ። ፕሬዝደንት ቮሎዶሚር ዜሌንስኪ ባለፈው አንድ ሣምንት ብቻ ሩሲያ በ1,800 ድሮኖች በዩክሬን ላይ ጥቃት እንደሰነዘረች ተናገሩ።
    9 min
  • የሐምሌ 5 ቀን 2017 ዓ.ም የዓለም ዜና
    የሐምሌ 5 ቀን 2017 ዓ.ም የዓለም ዜና
    በሲዳማ ክልል የሀዋሳ ዙሪያ ወረዳ ነዋሪዎች ለተቃውሞ አደባባይ ወጡ ፡፡
    በኳታር አሸማጋይነት በእስራኤልና ሐማስ መካከል እየተካሄደ የነበረው ቀጥታዊ ያልሆነ የተኩስ አቁም ድርድር «በእስራኤል ተደራዳሪዎች እንቅፋት እየገጠመው ነው» ሲል ሐማስ ወቀሰ።
    ሩስያ ሌሊቱን ለዛሬ ቅዳሜ አጥቢያ በዩክሬይን ላይ ፈጸመችው በተባለ የድሮንና የሚሳይል ጥቃቶች ቢያንስ 2 ሰዎች መገደላቸውንና 14 መቁሰላቸውን ክዬቭ አስታወቀች።
    11 min
  • የሐምሌ 4 ቀን 2017 ዓ.ም. የዓለም ዜና
    የሐምሌ 4 ቀን 2017 ዓ.ም. አርዕስተ ዜና
    ሳዑዲ አረቢያ 2 ኢትዮጵያውያንን በሞት ቀጣች። የሳዑዲ አረቢያ የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር ሁለቱ የኢትዮጵያ ዜጎች በሞት የተቀጡት አደንዛዥ እጽ በማዘዋወር ተከሰው መሆኑን ትናንት መናገሩን የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት ዘግቧል።ኢትዮጵያውያኑ ሀሽሽ የተባለውን አደንዛዥ እጽ በማዘዋወር በፍርድ ቤት ጥፋተኛ ተብለዋል ።
    ከጎርጎሮሳዊው ግንቦት መጨረሻ ወዲህ በጋዛ እርዳታ ለማግኘት ከሞከሩ ሰዎች ወደ 800 የሚጠጉት እንደተገደሉ የተመድ ዛሬ አስታወቀ።
    አሜሪካን በተመድ ድርጅት ልዩ ባለሞያ ላይ ማዕቀቦች ለመጣል መወሰኗ ክፉኛ እንዳሳዘነው የአውሮጳ ኅብረት ዛሬ አስታወቀ።
    12 min
  • የዓለም ዜና፤ ሐምሌ 3 ቀን 2017 ዓ.ም ሐሙስ
    አርስተ ዜና፤
    --የዩክሬይኑ ፕሬዚዳንት ዜሌንስኪ ሩስያ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰው አልባ አውሮፕላኖችንና ሚሳኤሎችን ትናንት ወደ ኪይቭ ዩክሬን ካስወነጨፈ በኋላ ሩስያ ላይ ጠንካራ ማዕቀብ እንዲጣል ጠየቁ።--በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን ሳላማጎ ወረዳ ሦስት ሰዎች በአፈር ናዳ ተቀብረው ሕይወት አለፈ፡፡
    --የኬንያዉ ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ «ስርዓት አልበኝነት» በቸልታ አይታለፍም ሲሉ ዝምታቸውን ሰበሩ። የሰዎችን ንብረት የሚያቃጥል እግሩ ላይ በጥይት ይመታል ፤ ህመሙ ሲያገግም ፍርድ ቤት እንደሚቆም ተናግረዋል።--የፍልስጤሙ ሽምቅ ተዋጊ ቡድን ሃማስ አስር የእስራኤል ታጋቾችን ለመልቀቅ መስማማቱ ተሰማ።
    11 min

About የዓለም ዜና

From the publisher's feed

ዶይቼ ቬለ የዕለቱን ዋና ዋና ዜናዎች ከኢትዮጵያ እና ከመላው ዓለም በየቀኑ ያቀርባል። የኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ፖለቲካዊ እና ኤኮኖሚያዊ ጉዳዮችን ጨምሮ የመላው ዓለምን ውሎ የተመለከቱ ጠቃሚ መረጃዎች በሰባቱም የሣምንቱ ቀናት ከምሽቱ አንድ ሰዓት ከዶይቼ ቬለ ያድምጡ። የዶይቼ ቬለን ዜናዎች በአፕል ፖድካስት…