የዓለም ዜና

የዓለም ዜና

Download on the App Store

የዓለም ዜና episodes

  • የነሐሴ 2 ቀን 2017 የዓለም ዜና
    -የኢትዮጵያ ሕዝብ የሚደርስበትን እልቂት ለመግታት በሥልጣን ላይ ያለዉን መንግስት በሠላማዊ፣ ዴሞክራሲያዊና ሕዝባዊ ትግል መቀየር እንዳለበት የሐገሪቱ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ስብስብ ጥሪ አደረገ።--የትግራይ ክልል ገዢ ፓርቲ ህወሓት ከኤርትራ መንግስት ጋር ግንኙነት መጀመሩን በይፋ አረጋገጠ።የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከሕጋዊ ፓርቲነት ያገደዉ የህወሓት ሊቀመንበር ዶብረፅዮን ገብረ መድሕን የኢትዮጵያ ፌደራዊ መንግሥትን ወቅሰዋል።--እስራኤል ያወደመቻትን የጋዛ ሰርጥ ርዕሠ-ከተማ ጋዛ ከተማን በጦር ሐይል ለመቆጣጠር መወሰኗ ከዉጪም ከዉስጥም ዉገዝትና ተቃዉሞ ገጥሞታል።
    12 min
  • የነሐሴ 1 ቀን 2017 ዓ.ም. የዓለም ዜና
    የነሐሴ 1 ቀን 2017 ዓ.ም. አርዕስተ ዜና
    ከሶማሊያ ተነስተው ወደ የመን በጀልባ በመጓዝ ላይ ከነበሩ ስደተኞች መካከል 7 ኢትዮጵያውያን በረሀብ እና በውኃ ጥም መሞታቸውን የተመ የፍልሰተኞች ጉዳይ ድርጅት IOM አስታወቀ።
    የሱዳን ጠቅላይ ሚኒስትር ካሚል ኢድሪስን ያነጋገሩት የግብጹ ፕሬዝዳንት አብዱል ፈታህ አልሲሲ ግብጽ የሱዳንን አንድነት፣ ሉዓላዊነት እና የግዛት አንድነት የሚደግፍ ጽኑ አቋም እንዳላት አረጋገጡ።
    የሩስያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ስለዩክሬን ከትራምፕ ጋር እንደሚነጋገሩ አረጋገጡ። ጉባኤው መቼና የት እንደሚካሄድ፣ የዩክሬን ፕሬዝዳንት ቮሎዶሚር ዜሌንስኪ መሳተፍ አለመሳተፋቸውም አልተነገረም።
    11 min
  • የሐምሌ 30 ቀን 2017 ዓ.ም. የዓለም ዜና
    በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን በጃራ የሀገር ውስጥ መጠለያ ጣቢያ ንፋስ ቀላቅሎ በጣለ ዝናብ 28 ሰዎች መጎዳታቸው፤ የተፈናቃዮቹ መጠለያም መውደሙ ተነገረ።
    የተመድ እስራኤል በጋዛ የምታካሂደውን ዘመቻ ማስፋፋቷ ለበርካቶች እልቂት ምክንያት ሊሆን ይችላል ሲል አስጠነቀቀ። የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ሀገራቸው ጋዛ ውስጥ ሃማስን ሙሉ ለሙሉ ማሸነፍ ይኖርባታል እያሉ ነው።
    ወደ ሞስኮ የተጓዙት የአሜሪካው ፕሬዝደንት ልዑክ ስቲቭ ዊትኮፍ ከሩሲያው ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር ለሰዓታት መነጋራቸው ተገለጸ።
    የጀርመን ካቢኔ በሕገ-ወጥ ሥራ ላይ መሰማራትና ሕገወጥ የገንዘብ ውዝውርን ለመቆጣጠር የሚያስችል ረቂቅ ሕግ ዛሬ አፀደቀ።
    11 min
  • የሐምሌ 29 ቀን 2017 የዓለም ዜና
    -ኢትዮጵያዉያን በሕገ-ወጥ መስመሮች ወደ ዉጪ እንዳይጓዙ በዤኔቭ የኢትዮጵያ ኤምባሲ መከረ።ኤምባሲዉ ባለፈዉ ዕሁድ የአደን ባሕረ ሰላጤን ለማቋረጥ ሲሞክሩ 76 ኢትዮጵያዉያን ስደተኞች በመሞታቸዉ ሐዘኑን ገልጧልም።--ሩዋንዳ ከዩናይትድ ስቴትስ የሚባረሩ 250 ስደተኞችን ልትቀበል ነዉ።የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንት የዶናልድ ትራምፕ መስተዳድር «ሕገ ወጥ» እና «የመጥፎዎች መጥፎ» የሚላቸዉን ስደተኞች ወደ ሶስተኛ ሐገራት እያባረረ ነዉ።--የእስራኤል ጠቅላይ ሚንስትር የቢኒያሚን ኔታንያሁ መንግሥት ጋዛ ዉስጥ የከፈተዉን ጦርነት ለማጠናከርና ጋዛን ሙሉ በሙሉ ለመግዛት አቅዷል መባሉን የተለያዩ የእስራኤል የቀድሞ ባለሥልጣናት ተቃወሙት።
    10 min
  • የሐምሌ 28 ቀን 2017 ዓ.ም. የዓለም ዜና
    የሐምሌ 29 ቀን 2017 ዓ.ም. አርዕስተ ዜና
    ኢትዮጵያውያን የሚያመዝኑባቸውን ስደተኞች የጫነች ጀልባ በአደን ባህረ ሰላጤ ሰጥማ ቢያንስ 68 ስደተኞች መሞታቸውን የተባበሩት መንግሥታት የፍልሰተኞች ጉዳይ ድርጅት በምህጻሩ IOM አስታወቀ። የየመን ባለሥልጣናት በበኩላቸው በአደጋው ቢያንስ 76 ስደተኞች ሞተዋል ብለዋል።
    በአማራ ክልል ሰሜን ጎንደር ዞን ደባርቅ ወረዳ የሚገኙ ተፈናቃዮች በእርዳታ እጦት ሠዎች እየሞቱ ነው፣ አብዛኛዎቹም ለልመና ወጥተዋል ሲሉ ለዶቼቬለ ተናገሩ ።
    ጋዛ ውስጥ የታገቱት ሰዎች ይዞታ ዋነኛ ዓለም አቀፍ አጀንዳ መሆን አለበት ስትል እስራኤል አሳሰበች።
    12 min
  • DW Amharic የሐምሌ 27 ቀን 2017 የዓለም ዜና
    በሰሜን ምዕራብ ናይጄሪያ ታጣቂዎች ከ50 በላይ ሰዎችን በጅምላ አገቱ። ሩሲያ በዩክሬን ቁጥጥር ሥር በሚገኙት የዶኔትስክ እና ኼርሶን ግዛቶች በሣምንቱ መገባደጃ በፈጸመችው ድብደባ ሰባት ሰዎች መገደላቸውን የአካባቢው ባለሥልጣናት ዛሬ እሁድ አስታወቁ። የፍልስጤም ቀይ ጨረቃ ማኅበር በኻን ዩኒስ በሚገኝ ዋና መሥሪያ ቤቱ ላይ በተፈጸመ ጥቃት አንድ ሠራተኛው ሲገደል ሌሎች ሦስት መቁሰላቸውን አስታወቀ። የአውሮፓ ኅብረት የውጪ ጉዳይ ኃላፊ ካያ ኻላስ በሐማስ እጅ የሚገኘው እስራኤላዊ ታጋች ሁኔታ "አስደንጋጭ" ሲሉ አወገዙ። በምሥራቃዊ ሩሲያ ካምቻትካ ግዛት የሚገኝ እሳተ ገሞራ ከ600 ዓመታት ገደማ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ፈነዳ።
    8 min
  • የሐምሌ 25 ቀን 2017 የዓለም ዜና
    -የኢትዮጵያ መንግሥትና ህወሓት የዳግም ጦርነት ፉከራና ዝግጅታቸዉን እንዲያቆሙ የሚደረገዉ ጥሪና ግፊት እንደቀጠለ ነዉ።ከዚሕ ቀደም ተደጋጋሚ ሙከራ ባደረጉት ሽማግሌዎች ላይ የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብቶች ጉባኤ (ኢሰመጉ) ጥሪም ታክሎበታል።-----እስራኤል ላስራበችዉ ለጋዛ ሕዝብ የተለያዩ መንግሥታት የምግብና የመድሐኒት ርዳታ ከዓየር እየተጣሉ ነዉ።የአሜሪካዉ ልዩ መልዕክተኛ ደቡባዊ ጋዛን ሲጎበኙ፣ የጀርመን ዉጪ ጉዳይ ሚንስትር ደግሞ የእስራኤል ሰፋሪዎች ፍልስጤማዉያንን መግደል፣ማቁሰልና ማጥቃታቸዉን አዉግዘዋል።-የሩሲያና የቻይና የባሕር ኃይላት የስድስት ቀናት የጋራ ወታደራዊ ልምምድ ዛሬ ጀመሩ።
    12 min
  • የሐምሌ 24 ቀን 2017 ዓም የዓለም ዜና
    የሐምሌ 24 ቀን 2017 ዓም አርዕስተ ዜና
    የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በሲዳማ ፌዴራሊስት ፓርቲ ላይ ያሳለፈውን ውሳኔ ሻረ።
    የአንጎላ መንግሥት የነዳጅ ዘይት ዋጋ ለመጨመር መወሰኑ በዚህ ሳምንት ባስነሳው ተቃውሞ ቢያንስ 22 ሰዎች መገደላቸውን አሳወቀ።
    ጀርመን ለፍልስጤም የመንግሥትነት ዕዉቅና መሰጠት ያለበት የሁለት መንግስታት መፍትሔ ድርድር ሲያበቃ ነው ብላ እንደምታምን አሳወቀች ።ይሁንና እስራኤል በኃይል የያዘችዉን የፍልስጥም ግዛት ለመጠቅላል የእስራኤል ሁለት ሚንስትሮች ያሰሙት ዛቻ የተናጥጠል የዕዉቅና እርምጃ እንድትወስድ ሊያደርጋት እንደሚችል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ ጠቁመዋል።
    12 min
  • የሐምሌ 23 ቀን 2017 የዓለም ዜና
    -የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ምክር ቤት ክልሉ ከኦሮሚያ ክልል ጋር በይገባኛል የሚወዛገብባቸዉን አካባቢዎች ይዞታ በተመለከተ በቅርቡ ያሳለፈዉ ዉሳኔ የኦሮሚያ ክልል ነዋሪዎችና የፖለቲካ ፓርቲን ተቃዉሞ ቀስቅሷል። ---የሱዳን ተፋላሚ ኃይላትን ለማደራደር ታስቦ የነበረ የአራት ሐገራት የሚኒስትሮች ስብሰባ በግብፅና በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ልዩነት ምክንያት ተሰረዘ።--በረሐብ ለሚሳቃየዉ የጋዛ ሕዝብ የሰብአዊ ርዳታ የጫኑ ከ200 በላይ ካሚዮኖች ዛሬ ከተቀረዉ ዓለም ወደ ተቆራረጠችዉ የፍልስጤሞች ግዛት ገቡ።የአዉሮጳ መንግስታት ደግሞ ለጋዛ ፍልስጤማዉያን ከየር ሰብአዊ ርዳታ ለመጣል እየተዘጋጁ ነዉ።የዜናዉ መልዕክት የእስካሁኑ ነበር።
    10 min

About የዓለም ዜና

From the publisher's feed

ዶይቼ ቬለ የዕለቱን ዋና ዋና ዜናዎች ከኢትዮጵያ እና ከመላው ዓለም በየቀኑ ያቀርባል። የኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ፖለቲካዊ እና ኤኮኖሚያዊ ጉዳዮችን ጨምሮ የመላው ዓለምን ውሎ የተመለከቱ ጠቃሚ መረጃዎች በሰባቱም የሣምንቱ ቀናት ከምሽቱ አንድ ሰዓት ከዶይቼ ቬለ ያድምጡ። የዶይቼ ቬለን ዜናዎች በአፕል ፖድካስት…