የዓለም ዜና

የዓለም ዜና

Download on the App Store

የዓለም ዜና episodes

  • DW Amharic የነሐሴ 22 ቀን 2017 የዓለም ዜና
    በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጌዲዖ ዞን ራጴ ወረዳ በተከሰተ የመሬት መንሸራተት ዘጠኝ ሰዎች ሕይወታቸውን አጡ። በሶማሌ ክልል ከካሉብ እና ሒላላ በሚገኝ የተፈጥሮ ጋዝ የማዳበሪያ ፋብሪካ ለማቋቋም ያቀደ የ2.5 ቢሊዮን ዶላር ሥምምነት በኢትዮጵያ መንግሥት እና በናይጄሪያው ዳንጎቴ ግሩፕ መካከል ተፈረመ። በመቶዎች የሚቆጠሩ የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ሠራተኞች፣ የኮሚሽኑ ኃላፊ ፎልከር ቱርክ በጋዛ ጦርነት በግልጽ የዘር ማጥፋት እየተፈጸመ ነው የሚል ድምዳሜ ላይ እንዲደርሱ በደብዳቤ መጠየቃቸውን ሬውተርስ ዘገበ። አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ሩሲያ በዩክሬን ዋና ከተማ ኪየቭ ላይ የፈጸመችውን ኃይለኛ ድብደባ አወገዙ።
    10 min
  • የነሐሴ 21 ቀን 2017 የዓለም ዜና
    አርዕሥተ ዜና
    -የኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክና የሩዋንዳ መንግሥታት የስደተኞች ልዉዉጥ ለማድረግ ተስማሙ።ሁለቱ መንግሥታት የሰላም ስምምነት ቢፈራረሙም ምሥራቃዊ ኮንጎ ዉስጥ ያለዉ ዉጥረት አሁንም እንደቀጠለ ነዉ።---እስራኤል ጋዛ ሰርጥ ላይ የከፈተችዉ ጥቃት እንዲቆም የሚደረገዉ ግፊት፣ ጥሪና ተማፅዕኖ እንቀጠለ ነዉ።የአሜሪካ ፕሬዝደንት ዛሬ ሥለጋዛ የሚነጋገር ሥብሰባ ዋሽግተን ዉስጥ ያስተናግዳሉ።-የጀርመን መንግሥት ብሔራዊ የፀጥታ ምክር ቤት ለመመሥረት ወሰነ።በዩናይትድ ስቴትስና በብሪታንያ የብሔራዊ ደሕንነት ምክር ቤቶች አምሳያ ይዋቀራል የተባለዉ ምክር ቤት የሐገሪቱን የፀጥታ መርሕ ያቀናጃል፣በቀዉስ ጊዜ ፈጣን መልስ ይሰጣል
    10 min
  • የነሐሴ 19 ቀን 2017 ዓ.ም የዓለም ዜና
    የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች በዳርፉር 13 ስቪሎችን መግደላቸውን የአካባቢው የሕክምና ምንጮች ተናገሩ። ከተገደሉት አብዛኛዎቹ ሴቶች እና ሕጻናት ናቸው ተብሏል።
    ሴኔጋል አዲስ በኤምፖክስ የተያዘ ሰው ማግኘቷን የሐገሪቱ የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ። ቫይረሱ ተገኘበት የተባለው ግለሰብ ከሌላ አገር የመጣ የውጭ ዜጋ ነው ብሏል።
    እስራኤል ጋዛ ውስጥ በካንዩኑስ በሚገኝ ናስር ሆስፒታል በፈጸመችው ጥቃት ቢያንስ 15 ፍልስጤማውያንና 4 ጋዜጠኞች ተገደሉ። ከሞቱት ውስጥ የአደጋ ጊዜ ሰራተኞችም እንደሚገኙባቸው ተነግሯል።
    11 min
  • DW Amharic የነሐሴ 18 ቀን 2017 የዓለም ዜና
    ሦስት ሱዳናውያን እህትማማቾች በርካታ ሰዎች ጭኖ የሜድትራኒያን ባሕር ለማቋረጥ ከሞከረ አነስተኛ ጀልባ ላይ ሕይወታቸው አልፎ ተገኘ። የእህትማማቾቹ አስከሬን የተገኘበት ጀልባ ከሱዳን በተጨማሪ የማሊ፣ አይቮሪ ኮስት፣ ኢትዮጵያ እና ኤርትራ ሰዎች ጭኖ ነበር። የናይጄሪያ ጦር በቦርኖ ግዛት በፈጸመው ጥቃት አክራሪ ሳይሆኑ አይቀሩም የተባሉ 35 ታጣቂዎች መግደሉን አስታወቀ። ከሩሲያ ጋር የሚደረገው ጦርነት ሲያበቃ የውጪ ሀገራት ወታደሮች በዩክሬን መገኘት “ጠቃሚ” እንደሚሆን ፕሬዝዳንት ቮሎዶሚር ዜሌንስኪ ገለጹ። የእስራኤል የጦር አውሮፕላኖች እና ታንኮች የጋዛ ከተማ ምሥራቃዊ እና ሰሜናዊ አካባቢዎችን ደበደቡ።
    9 min
  • የነሐሴ 17 ቀን 2017 ዓ/ም የዓለም ዜና
    DW Amharic-የዛሬው የዓለም ዜና ግብፅ በአባይ ወንዝ ላይ የሚደረግ የአንድ ወገን እርምጃ አልቀበልም ስትል ለአፍሪካ ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚንስትሮች መግለጿን፤በጋዛ ከ25 በላይ ፍልስጤማውያን መገደላቸውን፤ወደ ዩክሬን የሰላም አስከባሪ ጦር የመላክ ሀሳብ በጀርመን ውዝግብ ማስነሳቱን የግሎባል ሳውዝ የሚባሉት ሀገራት የሩሲያ ዩክሬን ጦርነትን ለማስቆም ግፊት እንዲያደርጉ የዩክሬኑ ፕሬዚዳንት መጠየቃቸውን እንዲሁም ሰሜን ኮሪያ ከደቡብ ጋር በሚያዋስናት ድንበር ላይ በወታደሮቼ ላይ ተኩስ ተከፈተብኝ ማለቷን ያስቃኛል።
    12 min
  • የዓለም ዜና፤ ነሐሴ 16 ቀን 2017 አርብ
    አርስተ ዜና፦
    --እስራኤል ትናንት ሃሙስ በጋዛ ከተማ አዲስ የምድር ጦር ጥቃት ሰነዘረች። ጥቃቱ ትልቁ የጋዛ ከተማን ለመቆጣጠር የመጀመሪያ ምዕራፍ ነዉ ተብሏል።--የደቡብ ሱዳን ፕሬዝዳንት ሳልቫ ኪር የሀገሪቱን የፋይናንስ ሚንስትር ከስልጣን አሰናበቱ።--ኢትዮጵያ ውስጥ ጦርነት ግጭትና ኃይል የቀላቀለ ውጊያ እንዲቆም የሚጠይቅ ጉባኤ ሊካሄድ መሆኑን የኢትዮጵያ ሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ም/ቤት አስታወቀ።--በኒው ዮርክ የሚገኝ የይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት በዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ እና በድርጅታቸው ላይ የተጣለውን 500 ሚሊዮን ዶላር የገንዘብ ቅጣት ውድቅ አደረገ። ትራምፕ የፍርድ ቤቱን እርምጃ ድል ብለዉታል።
    11 min
  • የነሐሴ 15 ቀን 2017 የዓለም ዜና
    -የኢትዮጵያ መንግሥት ባለሥልጣናት ያሰሯቸዉን ጋዜጠኞች ያለምንም ቅድመ-ሁኔታ እንዲፈቱ ሁለት ዓለም አቀፍ የጋዜጠኞች ተቆርቋሪ ድርጅቶች ጠየቁ።የጋዜጠኞች መብት ተሟጋቾች እንደሚሉት ኢትዮጵያ ለነፃ ፕረስና ለጋዜጠኝነት ሥራ አደገኛ እየሆነች ነዉ።---የእስራኤል ጦር ሠሜናዊ ጋዛ ዉስጥ የሚሰሩ የሕክምና ባለሙያዎችና የርዳታ ድርጅት ሰራተኞች አካባቢዉን ለቅቀዉ ለመዉጣት እንዲዘጋጁ አሳሰበ።ጦሩ የጋዛ-ከተማን ሙሉ በሙሉ ለማስገበር እየተዘጋጀ ነዉ።---የምዕራባዉያን ሐገራት ጦር ዩክሬን ዉስጥ ይሰፈር የሚለዉን ሐሳብ ሩሲያ አጥብቃ ተቃወመች።የሩሲያ-ዩክሬንን ጦርነት ለማቆም የሚደረገዉ የዲፕሎማሲ ጥረት፣ጦርነቱም እንደቀጠሉ ነዉ።
    11 min
  • የነሐሴ 14 2017 ዓ.ም. የዓለም ዜና
    በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ዎላይታ ዞን ኪንዶ ኮይሻ ወረዳ ትናንት በደረሰ የመሬት መንሸራተት አደጋ የሞቱ አንዲት እናትና ሁለት ልጆቻቸው አስከሬን ተገኘ።
    በምዕራብ ወለጋ ዞን ሳዮ ኖሌ በተባለ ወረዳ ሦስት ሰዎች ላይ አሰቃቂ የግድያ ወንጀል የፈጸመ የፖሊስ አባል የሞት ቅጣት ተወሰነበት።
    ዩጋንዳ ሕገወጥ ስደተኞችን ከዩናይትድ ስቴትስ ለመቀበል አለመስማማቷን የሀገሪቱ ከፍተኛ ባለሥልጣን አስታወቁ።
    ጦርነት ባመሳቀላት ሱዳን የዳርፉር ግዛት ሆስፒታል በታጠቁ ግለሰቦች በተፈጸመ ጥቃት 1 ሰው መገደሉንና አገልግሎቱን ማቋረጡን ድንበር የለሽ የሀኪሞች ቡድን አስታወቀ።
    ሩሲያ እሷን ያገለለ የዩክሬን ደኅንነት ውይይት የትም አይደርስም አለች።
    12 min
  • የዓለም ዜና፤ ነሐሴ 13 ቀን 2017 ዓ.ም
    አርስተ ዜና፤
    --የኢትዮጵያ መንግሥት የሲቪል ማህበረሰብ ቡድናትን የሚመራዉን ቦርድ መዋቅር ለመቀየር አቅዷል መባሉን ዓለምአቀፉ የሰብዓዊ መብት ተከራካሪ ድርጅት« አምነስቲ ኢንተርናሽናል» አጥብቆ ተቃወመ። ድርጅቱ እንደሚለዉ ይህ ለዉጥ ስራ ላይ ከዋለ «መዋቅራዊ ነጻነትን የሚገፍ፤ እና ሙሉ በሙሉ፤ የተጠያቂነትን በር የሚዘጋ ነዉ። --በሚቀጥሉት ሁለት ሳምንታት ውስጥ የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን እና የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘለንስኪ ለዉይይት ለመገናኘት እቅድ መያዛቸዉ ተሰማ።
    ሙሉዉን ዜና ማስፈንጠርያዉን በመጫን ይከታተሉ!
    12 min

About የዓለም ዜና

From the publisher's feed

ዶይቼ ቬለ የዕለቱን ዋና ዋና ዜናዎች ከኢትዮጵያ እና ከመላው ዓለም በየቀኑ ያቀርባል። የኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ፖለቲካዊ እና ኤኮኖሚያዊ ጉዳዮችን ጨምሮ የመላው ዓለምን ውሎ የተመለከቱ ጠቃሚ መረጃዎች በሰባቱም የሣምንቱ ቀናት ከምሽቱ አንድ ሰዓት ከዶይቼ ቬለ ያድምጡ። የዶይቼ ቬለን ዜናዎች በአፕል ፖድካስት…