የዓለም ዜና

የዓለም ዜና

Download on the App Store

የዓለም ዜና episodes

  • የመስከረም 26 ቀን 2018 ዓ/ም የዓለም ዜና
    • የኢትዮጵያን የባህር በር ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ መንግስት ከቀጣናው ሃገራት ጋር በዲፕሎማሲያዊ መንገድ እንደሚሰራ የኢፌድሪ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀስላሴ ተናገሩ ።
    • እስራኤል እና የፍልስጥኤማዉያኑ ታጣቂ ቡድን ሃማስ የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ለጋዛ ዕልቂት ማብቂያ ባቀረቡት የሰላም ሃሳብ አፈጻጸም ላይ ግብጽ ውጥ ቀጥተኛ ያልሆነ ድርድር ጀመሩ ።
    • አዲሱ አዲሱ የፈረንሳይ ጠቅላይ ሚንስትር ሴባስቲያን ሊኮርኑ አንድ ወር ሳይሞላቸው ዛሬ ስልጣናቸውን በፈቃዳቸው ለቀቁ።
    • ዓለማቀፉ የወንጀል መዳኛ ፍርድ ቤት አይ ሲ ሲ በሱዳን የሚሊሻ መሪ አሊ ሙሐመድ አሊ አብዱልራህማን የጥፋተኝነት ብይን ሰጠ።
    12 min
  • የመስከረም 25 ቀን 2018 የዓለም ዜና
    በሞቃዲሾ በሚገኘው ጎድካ ጂልኮው እስር ቤት ላይ ትላንት ቅዳሜ ጥቃት የፈጸሙ ሰባት የአል-ሸባብ አባላት መገደላቸውን የሶማሊያ መንግሥት አስታወቀ። እስራኤል እና ሐማስ የጋዛ ጦርነት በሚያበቃበት እና ታጋቾች በሚለቀቁበት መንገድ ላይ ነገ ሰኞ በግብጽ ሊደራደሩ ነው። ሩሲያ በሚሳይሎች እና ድሮኖች በዩክሬን ላይ በፈጸመችው ጥቃት ቢያንስ አምስት ሰዎች መገደላቸውን ፕሬዝደንት ቮሎዶሚር ዜሌንስኪ አስታወቁ። በሺር አል አሳድ ከሥልጣን ከተባረሩ ወዲህ በሶርያ ለመጀመሪያ ጊዜ ለሀገሪቱ ምክር ቤት ምርጫ ሲካሔድ ዋለ።
    8 min
  • የመስከረም 24 ቀን 2018 ዓ/ም የዓለም ዜና
    ግብፅ ለገጠማት የጎርፍ መጥለቅለቅ ኢትዮጵያን ተጠያቂ አለች፤ኢትዮጵያ ለግብፅ ወቀሳ ምላሽ ሰጠች፤ኢሬቻ ሆራ-ፊንፊኔ በአዲስ አበባ ለ7ኛ ጊዜ ተከበረ፤አንድ ቱኒዚያዊ በፕሬዚዳንቱ ላይ በኦንላይ ትችት ስላቀረቡ የሞት ፍርድ ተበየነባቸው፤የእስራኤል ጦር በጋዛ ከትራምፕ የተኩስ አቁም ጥሪ በኋላ ዘመቻውን ቀጥሏል፤የጀርመን ሙንሽን የአውሮፕላን ማረፊያ ስራ ጀመረ
    13 min
  • የመስከረም 23 ቀን 2018 ዓ/ም የዓለም ዜና
    • በምዕራብ ሱዳን በከበባ ውስጥ በምትገኘው የኤል ፋሽር ከተማ የፈጥኖ ደራሽ ወይም የአር ኤስ ኤፍ ኃይሎች ባደረሷቸው ጥቃቶች በአስር ቀናት ውስጥ 91 ሰላማዊ ሰዎች ተገደሉ ።
    • የዓለም የምግብ ድርጅት (WFP) የከፋ ነው የተባለ የገንዘብ እጥረት ማጋጠሙን ተከትሎ በሶማሊያ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ለረሃብ መጋለጣቸውን አስታወቀ።
    • የማዳጋስካሩ ፕሬዚዳንት አንድሪ ራጆኡሊና ስልጣን ለመልቀቅ ዝግጁ አይደለሁም አሉ።
    • ጋዛ ውስጥ ለሚገኙ ፍልስጥኤማዉያን የርዳታ ቁሳቁስ ይዘው በአጀብ ወደ ጋዛ ይጓዙ ከነበሩ በርካታ ጀልባዎች ውስጥ የመጨረሻዎቹ በእስራኤል ጦር ኃያል መጠለፋቸውን አስተባባሪዎቹ አስታወቁ።
    12 min
  • የመስከረም 22 ቀን፣ 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና
    በጎዴ የአፈር ማዳበሪያ እና የነዳጅ ማጣሪያ ለመገንባት የመሠረት ድንጋይ ተቀመጠ ፤ ሁለት የኬንያ አንቂዎች ዩጋንዳ ውስጥ ታገቱ ፤ ሞሮኮ 3 ሰዎች በፖሊስ ተገደሉ፤ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ: በኢቦላ በሽታ ከ 40 በላይ ሰዎች ሞቱ፤ ማንችስተር አንድ ሙክራብ ላይ በተሰነዘረ ጥቃት ሁለት ሰዎች ተገደሉ፤ የትራምፕ አስተዳደር የበጀት እገዳ
    10 min
  • የማክሰኞ መስከረም 21 ቀን፣ 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና
    ሸንኮራ፥ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን ዛሬ በደረሰ አደጋ ከ30 በላይ ሠዎች ሞቱ፤ ቡታጀራ፥ ሁከትና ብጥብጥ አንስተዋል ሲል ፖሊስ የጠረጠራቸውን 47 ሰዎች በቁጥጥር ማዋሉን ዐሳወቀ፤ ኪንሻሳ፥ የኮንጎ ወታደራዊ ፍርድ በቀድሞ የአገሪቱ ፕሬዚደንት ላይ ቤት የሞት ፍርድ በየነ፤ ሙይንሽን፥ በቦንብ ጥቃት ሥጋት ለሰአታት ተቋርጦ የነበረው ኦክቶበርፌስት እንደገና ተከፈተ፤ ቤርሊን፥የሉፍታንዛ አውሮፕላን አብራሪዎች አድማ ሊጠሩ እንደሚችሉ አስጠነቀቁ
    13 min
  • የማክሰኞ መስከረም 20 ቀን፣ 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና
    አ.አ፥ የኢትዮጵያ የመዋዕለ-ንዋይ ፍሰት ኹኔታ፦ «ለአሜሪካ እና ሌሎች የውጭ ንግዶች ፈታኝ» መሆኑ ተገለጠ፤ አንታናናሪቮ፥ ማዳጋስካር በተቃውሞ ሰልፍ 22 ሰዎች ተገደሉ፤
    ፓሪስ፥ በፈረንሣይ የደቡብ አፍሪቃ የቀድሞ አምባሳደር ሆቴል ውስጥ ሞተው ተገኙ፤ጋዛ፥ሐማስ በዶናልድ ትራምፕ የቀረበውን ባለ 20 ነጥብ የጋዛ ምክረ-ሐሳብ እያጤነበት ነው፤ ዶሓ፥ በጋዛ ተኩስ አቁም ምክረ-ሐሳብ ላይ አስተያየት እየተሰጠ ነው
    10 min
  • የመስከረም 19 ቀን 2018 ዓ/ም የዓለም ዜና
    • የኢትዮጵያ ታላቁ የህዳሴ ግድብ በሱዳን የከፋ የጎርፍ አደጋ እንዳይከሰት ተከላክሏል ሲሉ የውሃ ሃብት ሚንስትሩ ሃብታሙ ኢተፋ ተናገሩ ።
    • በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምሥራቅ ጉራጌ ዞን ቡታጅራ ከተማ ትናንት እሁድ ለተቃውሞ አደባባይ የወጡ ወጣቶች ከፀጥታ አስከባሪዎች ጋር ግጭት ገብተው 3 ሰዎች ሲገደሉ ሌሎች አራት ሰዎች ቆሰሉ ።
    • የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ 18 በመቶ የነበረውን የባንኮች ዓመታዊ የብድር ዕድገት ጣሪያ ወደ 24 ከመቶ ከፍ ማድረጉን አስታወቀ።
    12 min
  • የመስከረም 18 ቀን 2018 ዓ/ም የዓለም ዜና
    • በአማራ ክልል በሰሜን እና ደቡብ ወሎ ዞኖች በመንግስት የጸ,ጥታ ኃይሎች እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል ግጭት መባባሱን ናዋሪዎች ተናገሩ ።
    • የኢትዮጵያ የመከላከያ ሰራዊት «ባንዳ » ያላቸው ኃይሎች የኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅም እውን እንዳይሆን ለማደናገር» ይጥራሉ ሲል ከሰሰ።
    • በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምሥራቅ ጉራጌ ዞን ቡታጅራ ከተማ ዛሬ ለተቃውሞ አደባባይ የወጡ ወጣቶች ከፀጥታ አስከባሪዎች ጋር ባደረጉት ግጭት ሰዎች ሳይቆስሉና ሳይሞቱ እንዳልቀረ የከተማዋ ነዋሪዎች ገለጹ ፡፡
    • አሜሪካ በጋና ላይ የጣለችውን የቪዛ ገደብ ማሻሻሏን የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።
    14 min
  • የመስከረም 17 ቀን 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና
    የጋምቤላ ክልል መንግስት ለ128 ታራማዎች ይቅርታ ማድረጉን አስታወቀ። የቀድሞው የሶሪያ ፕረዚደንት ባሽር አል አሳድ የእስር ትዕዛዝ እንደወጣባቸው የሐገሪቱ ባለስልጣናት አስታወቁ። ከፈረንሳይ በእንግሊዝ የባሕር ወሽመጥ በላስቲክ ጀልባ አቋርጠው ወደ እንግሊዝ ለመሻገር ከሞከሩ ስደተኞች መካከል 2 ሴቶች መሞታቸውን
    13 min

About የዓለም ዜና

From the publisher's feed

ዶይቼ ቬለ የዕለቱን ዋና ዋና ዜናዎች ከኢትዮጵያ እና ከመላው ዓለም በየቀኑ ያቀርባል። የኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ፖለቲካዊ እና ኤኮኖሚያዊ ጉዳዮችን ጨምሮ የመላው ዓለምን ውሎ የተመለከቱ ጠቃሚ መረጃዎች በሰባቱም የሣምንቱ ቀናት ከምሽቱ አንድ ሰዓት ከዶይቼ ቬለ ያድምጡ። የዶይቼ ቬለን ዜናዎች በአፕል ፖድካስት…