የዓለም ዜና

የዓለም ዜና

Download on the App Store

የዓለም ዜና episodes

  • የጥቅምት 15 ቀን 2018 ዓ/ም የዓለም ዜና
    አይቮሪኮስታዊያን ዛሬ ለፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ድምጽ ሲሰጡ ዋሉ።
    የለንደን ፖሊሶች በወሲባዊ ትንኮሳ ተፈርዶበት በእስር ላይ እያለ በስህተት የተለቀቀ የጥገኝነት ጠያቂ እያፈላለጉ ነው።
    የአውሮጳ ህብረት በቻይና ወሳኝ የጥሬ ዕቃዎች ላይ ያለውን ጥገኝነት መግታት ያስችለኛል ያለውን ርምጃ ሊወስድ ነው።
    ሩስያ ሌሊቱን በዩክሬን ባደረሰችው የሚሳኤል እና የድሮን ጥቃት በትንሹ አራት ሰዎች ተገደሉ ፤ 20 ሰዎች ቆሰሉ።
    አሜሪካ ግዙፍ የጦር አውሮፕላን ተሸካሚ መርከቧን ወደ ካሪቢያን ባህር ማስጠጋቷን ተከትሎ ከደቡብ አሜሪካዊቷ ሀገር ቮንዙዌላ ጋር ጦርነት ሊቀሰቀስ ይችላል የሚል ስጋት እየጨመረ መጥቷል።
    11 min
  • የጥቅምት 14 ቀን 2018 ዓ.ም. የዓለም ዜና
    የጥቅምት 14 ቀን 2018 ዓ.ም. የዶቼቬለ አርዕስተ ዜና
    ዶቼቬለ ከኢትዮጵያ የሚሰሩ 9 ዘጋቢዎቹ በኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሀን ባለሥልጣን መታገዳቸውን ተቃወመ፤ የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት በዘጋቢዎቹ ላይ የተጣለውን እገዳም በአስቸኳይ እንዲያነሱ ጥሪ አቀረበ።
    የዩናይትድ ስቴትስ፣ የሳዑዲ አረብያ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶችና የግብጽ ተወካዮች ከሱዳን ተፋላሚ ኃይላት ጋር ሰብዓዊ ስምምነት ላይ እንዲደርሱ ግፊት ለማድረግ ዛሬ ዋሽንግተን ውስጥ ይወያያሉ ተብሎ ይጠበቃል።
    ኤም 23 የተባለው ታጣቂ ቡድን ቢያንስ 500 ኪሎ ግራም ወርቅ ከምሥራቅ ኮንጎው የማዕድን ማውጫ ዘርፏል ተብሎ መከሰሱን አስተባበለ።
    10 min
  • የጥቅምት 13 ቀን 2018 ዓ.ም. የዓለም ዜና
    የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለሥልጣን ኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ የዶቼ ቬለ ዘጋቢዎችን ለጊዜው ማገዱን በዛሬው ዕለት በደብዳቤ አስታወቀ።
    ከሁለት ዓመት በላይ በዘለቀው የሱዳን ጦርነት ሕዝቡ አሳሳቢ የሰብአዊ ቀውስ እየተጋፈጠ እንደሚገኝ የተመ የሕጻናት መርጃ ድርጅት ዩኒሴፍ አመለከተ።
    በመላው ዓለም ከሚካሄዱት ግጭቶች 40 በመቶው አፍሪቃ ውስጥ እንደሆነ ዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ኮሚቴ ገለጸ።
    የአውሮጳ ሕብረት በዛሬው ዕለት ሩሲያ ላይ ተጨማሪ ማዕቀቦችን ጣለ።
    10 min
  • የጥቅምት 12 ቀን 2018 የዓለም ዜና
    -የጀርመን መራሔ መንግሥት ፍሪድሪሽ ሜርስ ሥደተኞችን የሚያጥላላ መልዕክት ማስተላለፋቸዉ የቀሰቀሰዉ ቁጣና ተቃዉሞ እንደቀጠለ ነዉ።የሜርስን መግለጫ፣ ፖለቲከኞች፣ የመብት ተሟጋቾችና የኤኮኖሚ ባለሙያዎች ነቅፈዉታል።--የሩሲያ ጦር ኃይል የኑክሌር ጦር መሳሪያ ልምምድ ጀመረ።ልምምዱ የኑኬሌር አረር መሸከም የሚችሉ ሚሳዬሎችን፣ መርከቦችንና አዉሮፕላኖችን ያካተተ ነዉ።---የእስራኤል ጠቅላይ ሚንስትር ቢኒያሚን ኔታንያሁ እስራኤል በዩናይትድ ስቴትስ ቁጥጥር ሥር የምትገኝ ሐገር አይደለችም አሉ።ኔታንያሁ የአሜሪካ ምክትል ፕሬዝደንትን ከማነጋገራቸዉ በፊት ዛሬ እንዳሉት እስራኤል የራስዋን ፀጥታ በሚመለከት የምትወስነዉ ራስዋ ናት።
    11 min
  • የማክሰኞ ጥቅምት 11 ቀን፣ 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና
    አ.አ፥ በባቡር አደጋ ኢትዮጵያ ውስጥ ቢያንስ 14 ሰዎች መሞታቸው ተገለጠ፤ ገዋኔ፥ ነዋሪዎች በተቃውሞ የኢትዮጵያ ጅቡቲን አውራ ጎዳና መንገድን ዘግተው ነበር ተባለ፤ ፓሪስ፥ የፈረንሣይ የቀድሞ ፕሬዚደንት ታሰሩ፤ ዋሽንግተን፥ዶናልድ ትራምፕ የመካከለኛው ምሥራቅ አጋሮቻቸው ወደ ጋዛ ጦር ለመላክ ዝግጁ ናቸው አሉ፤ ጋዛ፥ ነዋሪዎች የተኩስ አቁሙ እንዳይጣስ ሥጋት ገብቷቸዋል ።
    10 min
  • የጥቅምት 10 ቀን 2018 ዓ.ም. የዓለም ዜና
    • የቀድሞው የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት የተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስ ሥርዓተ ቀብር ዛሬ ተፈጸመ። • እስራኤል ትናንት እሁድ ከሐማስ ለተሰነዘረ ጥቃት አጸፋ ነው ካለችው ብርቱ የአየር ጥቃት በኋላ የጋዛ የተኩስ አቁም ተግባራዊነቱ እንደሚቀጥል የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ተናገሩ ። የአውሮጳ ህብረት በበኩሉ የጋዛ የተኩስ አቁም ገቢራዊነት እስኪረጋገጥ በእስራኤል ለመጣል ያሰበውን ማዕቀብ በይደር አቆያለሁ ብሏል። • የጣልያን የባሕር ድንበር ጠባቂዎች ላምፔዱሳ ደሴት አቅራቢያ 91 ሰዎች ከመስጠም መታደጋቸውን አስታወቁ ።
    11 min
  • የጥቅምት 9 ቀን 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና
    እስራኤል በደቡባዊ ጋዛ የአየር ጥቃት መፈጸሟን አስታውቀች። ኢራን ለእስራኤል ይሰልል ነበር ብላ የወነጀለችው አንድ ግለሰብ በዛሬው ዕለት በስቅላት መቅጣቷን ተሰማ። ዩክሬይን ሌሊት ለዛሬ አጥቢያ በሩስያ የሳማራ ግዛት ላይ በፈጸመችው የድሮን ጥቃት የሩስያ የነዳጅ ማጣሪያ ማውደሟን አስታወቀች። በሺዎች የሚቆጠሩ አሜሪካውያን በዋሽንግተን ዲሲና ሌሎች ከተሞች አደባባይ ወጥተው የአሜሪካው ፕረዚደንት ዶናልድ ትራምፕን የሚቃወም ሰልፋ አድርገዋል።
    10 min
  • የጥቅምት 08 ቀን 2018 የዓለም ዜና
    በኪሱሙ የራይላ ኦዲንጋ መታሰቢያ ዝግጅት ላይ በርካታ ሰዎች መቁሰላቸውን የኬንያ ቀይ መስቀል ባለሥልጣናት ተናገሩ። የፈረንሳዩ ቢኤንፒ ፓሪስባስ ዩናይትድ ስቴትስ ሱዳን ላይ የጣለችውን ማዕቀብ በመተላለፍ በሰጠው የባንክ አገልግሎት የኦማር አል-በሽር መንግሥት የዘር ማጥፋት እንዲፈጽም ረድቷል በሚል በአሜሪካ ፍርድ ቤት ጥፋተኛ ተባለ። በእስራኤል እና በሐማስ ጦርነት የተገደሉ ፍልስጤማውያን ቁጥር ከ68,000 በላይ መድረሱን የጋዛ የጤና ሚኒስቴር ዛሬ ቅዳሜ አስታወቀ። ኢራን ከአስር ዓመታት በፊት በኑክሌር መርሐ-ግብሯ ላይ ከልዕለ-ኃያላኑ የተፈራረመችው ሥምምነት በማብቃቱ በውሉ በተካተቱ ገደቦች እንደማትገዛ አስታወቀች።
    9 min
  • የጥቅምት 7 ቀን 2018 የዓለም ዜና
    -ትግራይ ዉስጥ ለሁለት ዓመት በተደረገዉ ጦርነት ከ152 ሺሕ በላይ የክልሉ ሴቶች መደፈራቸዉን «የትግራይ ጄኖ ሳይድ» የተባለዉ ኮሚሽን አስታወቀ።ኮሚሽኑ በ166 ገፅ በሰነደዉ ጥናቱ በትግራይ ሴቶች ላይ ከተፈፀመዉ አጠቃላይ ፆታዊ ጥቃት 90 በመቶዉን ያደረሱት የኤርትራና የኢትዮጵያ ጦር ኃይላት ባልደረቦች ናቸዉ ይላል።----ባለፈዉ ሮብ የሞቱት የኬንያ የረጅም ጊዜ ዕዉቅ ፖለቲከኛ የራይላ ኦዲንጋ አስከሬን ዛሬ በይፋ ተሸኘ።---የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕና የሩሲያዉ አቻቸዉ ቭላድሚር ፑቲን የዩክሬን ጦርነት ሥለሚቆምበት ብልሐት በቅርቡ ፊት ለፊት ተገናኝተዉ ለመነጋገር ተስማሙ።
    11 min
  • የጥቅምት 6 ቀን 2018 ቀን የዓለም ዜና
    የጥቅምት 6 ቀን 2018 ቀን አርዕስተ ዜና
    በአማራ ክልል ምሥራቅ ጎጃም ዞን የእነማይ ወረዳ ምክትል አስተዳዳሪና የሥራና ክህሎት ጽ/ቤት ኃላፊ የነበሩት አቶ አዲሱ ተሻለ ዛሬ ጠዋት በተተኮሰባቸው ጥይት ህይወታቸው ማለፉን የወረዳው የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ባሰራጨው ዘገባ አስታውቋል።
    የአፍሪቃ ሕብረት ማዳጋስካር ዉስጥ ተደረገ ያለዉን መፈንቅለ መንግሥት አወገዘ።ሕብረቱ ትናንት የማዳጋስካር ጦር ኃይል የሐገሪቱን የመንግሥትነት ሥልጣን መያዙን ተቃዉሟል።
    በአሁኑጊዜ በዓለማችን ቁጥሩ 14 ሚሊዮን የሚጠጋ ህዝብ በከባድ ረሀብ እየተሰቃዩ ነው ሲል የዓለም ምግብ ድርጅት አስታወቀ።
    11 min

About የዓለም ዜና

From the publisher's feed

ዶይቼ ቬለ የዕለቱን ዋና ዋና ዜናዎች ከኢትዮጵያ እና ከመላው ዓለም በየቀኑ ያቀርባል። የኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ፖለቲካዊ እና ኤኮኖሚያዊ ጉዳዮችን ጨምሮ የመላው ዓለምን ውሎ የተመለከቱ ጠቃሚ መረጃዎች በሰባቱም የሣምንቱ ቀናት ከምሽቱ አንድ ሰዓት ከዶይቼ ቬለ ያድምጡ። የዶይቼ ቬለን ዜናዎች በአፕል ፖድካስት…