እንደ ኮሮና ቫይረስ ያሉ ወረርሽኞች በሚነሱበት ጊዜ ቀጥተኛ ጉዳታቸው ብዙ ነው ። በ ሚድል ኤጅስ ዘመን (Middle Ages ) የተነሳው ጥቁር ሞት (Black Death ) ከ 30-50 ሚልየን ሰዎች እንደሞቱ ይገመታል። በቅርብ ደግሞ የ HIV pandemic ምክንያት ከ1981 ጀምሮ ከ35 ሚልየን በላይ ሰዎች ሞተዋል።
የኮሮና ቫይረስም አሁን በአለም ላይ ከአንድ ሚልየን በላይ ሰዎችን ይዟል። እና ከ 50000 በላይ ሰዎች ደግሞ
ለሞት ተዳርገዋል። የኢኮኖሚ ጉዳቱ ደግሞ በጣም ከፍተኛ ነው።
አሁን ማንሳት የፈለግነው ደግሞ በዚህ ወረርሽኝ ምክንያት እንዴት ሌሎች ዘላቂ ህመም ያላቸው ሰዎች በ ክትትል ማነስ ሊጎዱ እንደሚችሉ ነው። በ 2015 የተሰራ ጥናት እንደሚያሳየው ሰዎች በ ተላልፊ በሽታው ላለመያዝ ባላቸው ፍራቻ ፣ በ ሆስፒታሎች በአዲስ በሽተኞች መጣበብ ፣ የገንዘብ እና ሌሎች የህክምና ዕቃ መሳሪያዎች ለ ወረርሽኝ መቆጣጠሪያ መዋላቸው የ አነዚህን ህመምተኞች ሕክምና በጣም ይጎዳዋል።
ለምሳሌ በ 2014 በ ምዕራብ አፍሪካ የተነሳው የ ኢቦላ ወረርሽኝ ቀጥታ ካመጣው ሞት በተጨማሪ ወደ 11,300 ሰዎች የህክምና ክትትል በማጣት ሞተዋል። በነዚህ ሃገራት ያለው የክትባት ስርጭት መጠን ከ 30% በላይ መቀነሱ ታይቷል።
ስለዚህ እነዚህ ተጨማሪ ህመም ያላቸው ሰዎች ሕክምናቸውን የሚያገኙበት መንገድ መመቻቸት አለበት። የተለያዩ የህክምና ተቋማት ይሄንን ክፍተት ለመሙላት ምን እያደረጉ እንደሆነ በዚች አጭር የጤና ወግ ውይይታችን እናያለን ።
በ ኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ሌላ ዘላቂ የሆነ የጤና ያለባቸው ሰዎች ሕክምና እንዳይቃረጥ መስራት አለብን