
Sign up to save your podcasts
Or


የአፍሪካ ሀገራት ጠለቅ ያለ ጥያቄ በማንሳት ላይ ይገኛሉ፤ ጥያቄውም በዓለም አቀፍ መድረኮች መቀመጫ የማግኘት ብቻ ሳይሆን ደንቦቹን አብሮ የመጻፍም ጭምር ነው። በእርግጥ አፍሪካ ስለ አፍሪካ ከሚያወራ ይልቅ የሚያደምጣትና አብሯት የሚሰራ አዲስ የዓለም አቀፍ አሰራር መገንባት ትችላለች? በዛሬው የ ድራም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅታችን በዲላ ዩኒቨርሲቲ የዓለም አቀፍ ግንኙነትና ፖለቲካ ሳይንስ መምህር እና ተመራማሪ ከሆኑት ዳዊት መዝገበ (ዶ/ር) ጋር የምንወያየው በዚህ ጉዳይ ላይ ይሆናል።
አፍሪካና ካሪቢያን የባርነትና ቅኝ ግዛት ታሪካቸውን ወደ የጋራ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ኃይል መለወጥ ይችላሉ? በዛሬው ድራም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅታችን፣ በኢትዮጵያ ለ15 ዓመታት ከኖሩትና በፓን-አፍሪካኒዝም እንቅስቃሴዎች ላይ ከሚተጉት ጸሐፊና ተሟጋች ጃኔል ሆይሌት ጋር በዚህ ጉዳይ ላይ እንወያያለን።
አፍሪካ የሰው ልጅ መነሻ እንደመሆኗ የትምህርት ሥርዓቷን ከቅኝ ግዛት እሳቤ ተፅዕኖ ነፃ በማውጣት ሀገር በቀል እውቀትን የችግር መፍቻ ማድረግ ይገባታል።
"የሰው ልጅ መነሻ የሆነችው አፍሪካ የራሷን ጥበብና ፍልስፍና በሥርዓቱ መጠቀም እንዳትችል የውጭ ጫና ተፅዕኖ አሳድሮባታል […] ከንግዲህ ግን ከውጭ በተወረሱ እሳቤዎች ላይ ብቻ ጥገኛ ሆኖ መቀጠል የሚቻልበት ሁኔታ እያበቃ ይመስላል [...] ከዚህ በኋላ አፍሪካ የራሷን ችግር በራሷ መፍታት ይኖርባታል" ሲሉ ታሪክ እና የሀገር በቀል እውቀቶች ተመራማሪ አህመድ ዘካሪያ (ፕ/ር) አህመድ ዘካሪያ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።
በዛሬው የድራም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅታችን፤ የአፍሪካ ፍልስፍናዎች፣ የአስተዳደር ሥርዓቶች እና ሩሲያ ዙሪያ እናተኩራለን። ሀገር በቀል ዕውቀት ለአፍሪካ አስተዳደር መሠረት የሚሆንበትን እና የአስተሳሰብ ሉዓላዊነትን የሚያረጋግጥበትን መንገድ ከታሪክ እና የሀገር በቀል እውቀቶች ተመራማሪ አህመድ ዘካሪያ (ፕ/ር) እና በጅማ ዩኒቨርሲቲ መምህርና የኡቡንቱ የሕይወት ክህሎት ስልጠና ማዕከል መሥራች እውነቱ ኃይሉ (ዶ/ር) ጋር በመሆን እንቃኛለን።
ሙሉ መረጃውን ለማግኘት በአማርኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ያዳምጡ:
አብዛኞቹ የአፍሪካ ከተሞች ፈጣን ዕድገት እያሳዩ ቢሆንም፣ ከሚገነቡት ቤቶች ውስጥ ከሰባ በመቶ በላይ የሚሆኑት መደበኛ ባልሆኑ እና በቂ መሠረተ ልማት በማይሟላላቸው ሰፈሮች ውስጥ የሚገኙ ናቸው።
“በሚቀጥሉት አሥርት ዓመታት ወደ አፍሪካ ከተሞች ለሚፈልሱ ከ600 እስከ 900 ሚሊዮን ወጣቶች አሁን ልማታዊ ትኩረት ካልተሰጠ ጉዳቱ ከባድ ነው። መሬት ለቤት ግንባታ ውድ ግብዓት በመሆኑም የመንግሥት መሬትን በመጠቀም፣ የመሬት ማስተካከያዎችን በማድረግ እና ከግል ባለቤቶች ጋር በመተባበር የተቀናጀ ልማት እውን ማድረግ ይገባል” ሲሉ ዩኤን-ሃቢታት) ዋና ዳይሬክተር አናክላውዲያ ሮስባች ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናገሩ።
በዛሬው የድራም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅታችን፣ የአፍሪካ ከተሞች ዕጣ ፈንታ በፈተናና በዕድል መካከል ባለበት በዚህ ወቅት የኑሮ ውድነትና የአየር ንብረት ጽናት ውይይቶችን እንቃኛለን። አፍሪካ የሌሎችን ጎዳና ከመከተል ይልቅ የራሷን የከተማ ልማት ጎዳና መቅረጽ ትችላለች ወይ? ለእነዚህ ጥያቄዎች ጥልቅ ምላሽ ለማግኘት ከተባበሩት መንግስታት የሰፈራ መርሃ ግብር (ዩኤን-ሃቢታት) ዋና ዳይሬክተር አናክላውዲያ ሮስባች ጋር ያደረግነውን ቆይታ ተከታተሉ።
ሙሉ መረጃውን ለማግኘት በእንግሊዘኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ያዳምጡ:
"ጥሩ ትርጉም ቃላትን ብቻ ሳይሆን ትርጉምን፣ እሴቶችን፣ ታሪክንና ባህልን ያስተላልፋል። ለአፍሪካ ትርጉም የብዙሃን ቋንቋ ተናጋሪነት ምሰሶ ነው፤ የባህልና የቋንቋ ልዩነቶች እንዳይጋጩ በማድረግ ማህበረሰቦች ሀገር በቀል ቋንቋቸውን እያዳበሩ በሰፊው የውይይት መድረክ ላይ እንዲሳተፉ ያስችላል" ሲሉ በጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ የውጭ ቋንቋዎችና ስነ-ጽሑፍ መምህር አስቻለው ለገሰ (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።
በዛሬው የድራም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅታችን፣ የሙያዊ የትርጉም አገልግሎት የአፍሪካን ውህደት፣ ትምህርት፣ የሚዲያ ነፃነት እና የደቡብ ለ ደቡብ ትብብር ማጠናከር የሚችልባቸውን መንገዶች እንቃኛለን። በዚህ ጉዳይ ላይ ማብራሪያ እንዲሰጡን በጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ የውጭ ቋንቋዎችና ስነ-ጽሑፍ መምህር እንዲሁም የማህበራዊ ሳይንስና ሁማኒቲስ ኮሌጅ ዲን ከሆኑት አስቻለው ለገሰ (ዶ/ር) ጋር ቆይታ አድርገናል።
ሙሉ መረጃውን ለማግኘት በእንግሊዘኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ያዳምጡ:
በሩዋንዳ የጋቻቻ ፍርድ ቤቶች የህብረተሰቡን ተሳትፎና የማካካሻ ልምዶች በመጠቀም፣ ከተለመዱት የፍትህ አካላት አቅም በላይ የሆኑ ሁለት ሚሊዮን የሚጠጉ የዘር ማጥፋት መዝገቦችን በአስር ዓመት ውስጥ በብቃት መርምረዋል።
“የራሳችንን ሀገርበቀል እሳቤዎች በሙሉ በአንድ ላይ አዋቅረን ብንይዝ፣ ለሌሎችም የሚተርፍ ትልቅ እሴት እና አሰራር አለን [...] ምናልባትም አሁን ኢትዮጵያ ውስጥ የሚስተዋሉትን ቅራኔዎች ሊፈቱ እና ሊያሻግሩን የሚችሉት እነዚህ እውቀቶች ናቸው” ይላሉ የጆሃንስበርግ ዩኒቨርሲቲ የአስተዳደርና የአፍሪካ ጥናቶች ማዕከል ዳይሬክተር ሰይፈ ታደለ ኪዳኔ (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ።
በዛሬው የድራም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅታችን፣ ከአፍሪካ ውጭ የተኮረጁ የአስተዳደር ሞዴሎች ያጋጠሟቸውን መዋቅራዊ ፈተናዎች ከጆሃንስበርግ ዩኒቨርሲቲው ሰይፈ ታደለ ኪዳኔ (ዶ/ር) ጋር በጥልቀት እንቃኛለን።
ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ:
'' ቀጣናዊ የማግለል ሙከራዎች'' ቢኖሩም የዓባይ 85 በመቶ ውሃ ምንጭነቷ እና ከቀይ ባህር ጋር ያላት ታሪካዊ ቅርበት ያለ ኢትዮጵያ ንቁ ተሳትፎ በምሥራቅ አፍሪካ የሚደረግ ማንኛውም ዘላቂ የጸጥታ ወይም የንግድ ውጥን እንዳይሳካ ያደርገዋል።
“በቪየና የውል ሕግ ስምምነት አንቀጽ 34 መሠረት፣ የጋራ መግለጫው ያለ ሶስተኛ ወገን ግልጽ ፈቃድ በላዩ ላይ ግዴታዎችን መፍጠር አይችልም። ኢትዮጵያ በስብሰባው ላይ ያልተሳተፈች እና ያልፈረመች በመሆኗ፣ ጽሑፉ በኢትዮጵያ የውሃ አስተዳደር እና በህዳሴው ግድብ አሠራር ላይ ምንም ዓይነት ሕጋዊ የበላይነት የለውም” ሲሉ ከኢኮኖሚ ባለሙያው ቆስጠንጢኖስ በርሁተስፋ (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናገሩ።
የዛሬው የድራም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅታችን፤ የኤል አላሜይን የጋራ መግለጫ በዓባይ ወንዝ አስተዳደርና በቀይ ባህር ጸጥታ ላይ ይሚኖረዉን ጂኦፖለቲካዊ ፋይዳ ይዳስሳል። እንዲሁም የኢትዮጵያን ስልታዊ ምላሽና እውነተኛ የፓን-አፍሪካ ውይይት አስፈላጊነትን የመለከታል። ለዚህም ከኢኮኖሚ ባለሙያው ቆስጠንጢኖስ በርሁተስፋ (ዶ/ር) ጋር ተወያይተናል።
ሙሉ መረጃውን ለማግኘት በእንግሊዘኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ያዳምጡ:
ፕሬዚዳንት ፑቲን ዓለም ወሳኝ የእጥፋት ነጥብ ላይ መድረሷን ገልጸው፤ ዓለማችን ሰው ሰራሽ አስተውሎት (ኤአይ) ደህንነትንና የዓለም አቀፍ ኃይልን ሊቀርጽ የሚችልበት አዲስ የቴክኖሎጂ ዘመን ላይ መሆኗን አፅንኦት ሰጥተዋል።
“ምዕራባውያን ሌላ ጠንካራ አገር እንዲፈጠር አይፈልጉም፤ ቢፈጠርም በተለያየ መልኩ ያዳክሙታል። ሩሲያ ከናቶ እና ከምዕራቡ ዓለም ጋር በዩክሬን የገጠማት ጦርነት አንዱ ማሳያ ነው። በተመሳሳይ ሁኔታ አፍሪካም በኢኮኖሚና በሌሎች ዘርፎች ራሴን ልቻል የሚለ ሀገር ብቅ ቢል በተለያዩ መንገዶች ለማዳከም የሞክራሉ” ሲሉ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የሰላምና ድሀንነት ተቋም መምህርና ተመራማሪ ሙሉጌታ አየለ (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።
የዛሬው የድራም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅታችን፤ ፕሬዚዳንት ቭላዲሚር ፑቲን በቫልዳይ የውይይት ክለብ 2026 የመዝጊያ ስነ-ሰርዓት ላይ ተገኝተው ያደረጉትን ንግግር፣ ከባለብዙ ዋልታ የዓለም ሥርዓት እና ለአፍሪካ ከሚኖረው ፋይዳ አንፃር የምንቃኝበት ነው። ለዚህም በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሰላም እና ደህንነት ተቋም መምህር እና ተመራማሪ ከሆኑት ሙሉጌታ አየለ (ዶ/ር) ጋር አውርተናል።
ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ:
From the publisher's feed