Drum of Changes

Drum of Changes

Download on the App Store

Drum of Changes episodes

  • ጥበብ ወደመነሻ ለመድረስ፣ ጠበብ ሰላም ሰላምን ለማምጣት
    በዛሬው የድራም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅታችን መነሻችንን ማወቅ ማንነታችንን ለመገንባት የሚኖረውን ሚና እንቃኛለን። ጥበብ ይህንን ማንነት ለትውልድ ለማሻገር፣ ሰላምን ለማፅናት እና ሕዝቦችን ለማስተሳሰር ያላውን ድርሻ ከሰዓሊና የ«ኢትዮጲስ» ልጆች ፕሮግራም መስራች አርቲስት ሳምሶን መረሳ (ቲቶ) ጋር እንወያያለን።
    1 hr 1 min
  • ወደ ቀድሞው ዘመን፣ በዛሪው ዘመን ቴክኖሎጂ መመለስ
    በዛሬው የድራም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅታችን የኢትዮጵያን ጥንታዊ ጽሑፎች እና የታሪክ መጻሕፍት ወደ ዲጂታል የመቀየር ሂደት እንዲሁም የዘመናት ዕውቀት ከጥንታዊ ብራናዎች እና ከሩቅ መዛግብት ወደ ዲጂታል ዓለም ሲሸጋገር የሚያስከትለውን ውጤት እንቃኛለን። ለዚህም ማህበራዊ አንትሮፖሎጂስት አሉላ ፓንክኸርስትን (ዶ/ር) ጨምሮ ሌሎች ምሁራን ጋር ቆይታ አድርገናል።
    1 hr 1 min
  • በደቡብ-ደቡብ ትብብር ፓን-አፍሪካዊ እድገትን ማፋጠን
    የዛሬው ድራም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅታችን ትኩረት በደቡብ-ደቡብ ትብብር ላይ ነው። በማደግ ላይ ያሉ ሀገራት አጋርነት የአፍሪካን ኢንዱስትሪያላይዜሽን ማፋጠን የሚችልበትን እና ለምዕራባውያን ማዕቀፎች አማራጭ የሚሆንበትን መንገድ ከዲላ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነቶች መምህርና ተመራማሪ ዳዊት መዝገበ ጋር እንቃኛለን።
    1 hr 1 min
  • ከድንጋይ ወደ ሀብት፡ የአፍሪካ የእሴት አብዮት
    የዛሬው ድራም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅት የአፍሪካ ሀገራት ያልተቀነባበሩ ማዕድናትን ወደ ውጭ መላክ የመከልከል እንቅስቃሴዎችን ይቃኛል። በዚህም አፍሪካ ሀብቷን በሀገር ውስጥ በማስቀረት እሴት መፍጠር መጀመሯን እንመለከታለን። በጉዳዩ ላይ የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ የማህበራዊ ኢኮኖሚ ጉዳዮች ተመራማሪ እና ዓለም አቀፍ ጉዳዮች ተንታኝ መሐመድ ኢብራሂም ማብራሪያ ሰጥተዋል።
    1 hr 1 min
  • የአፍሪካ አረንጓዴ ጎህ፡ የማዕድን እሴትና የኢኮኖሚ ሉዓላዊነት
    የዛሬው ድራም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅታችን በሁለት አህጉራዊ ጉዳዮች ላይ ያተኩራል። የመጀመሪያው፣ አፍሪካ ከአዳዲስ ዓለም አቀፍ ጥምረቶች እና ከሻንጋይ የትብብር ድርጅት የምታገኛቸውን ትምህርቶች ከወራቤ ዩኒቨርሲቲው የምጣኔ ሀብት መምህር መሐመድ ኢሳ ጋር የምንዳስስበት ነው። ሁለተኛው ደግሞ፣ አፍሪካ ልማትና የድህነት ቅነሳን ሳታስተጓጉል ወደ ንጹሕ የኃይል አማራጭ የምታደርገውን ሽግግር ይመለከታል። በጉዳዩ ላይ ሪቻርድ ሚዩንጊ   (ዶ/ር) እና ከተባበሩት መንግሥታት የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን ማሪት ቅጣው አስተያየታቸውን ሰጥተውበታል።
    1 hr 1 min
  • የመካከለኛው ምስራቅ ግጭት እና በአፍሪካ ሴቶች ላይ የሚያሳድረው ተፅዕኖ
    በዛሬው የድራም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅታችን በሩቅ የሚከሰቱ ግጭቶች ከዳካር እስከ ናይሮቢ የቤተሰብ ወጪንና የገበያ እንቅስቃሴን እንዴት እየቀየሩ እንደሆነ ከታዋቂ የመብት ተሟጋች ጋር ዳስሰናል። የዓለም አቀፍ አደጋዎችን አህጉራዊ ተፅዕኖና የሴቶችን የኢኮኖሚ ጫና በጥልቀት የምንመረምርበትን ዝግጅት እንድትከታተሉ እንጋብዛለን። ለዚህም ናይጄሪያዊቷን የመብት ተሟጋች ፋዴኬሚ አኬንፌዳሪንን አነጋግረናል።
    1 hr 1 min
  • ከኔቶ ባሻገር፡ ደህንነት፣ ሉዓላዊነት እና አፍሪካ እየተለወጠ ባለው ዓለም ውስጥ ያላት ቦታ

    አሜሪካን ማዕከል አድርጎ የሚንቀሳቀሰው የኢንዶ-ፓስፊክ ስትራቴጂ ኔቶን ወደ አዲስ የውድድር አውድ እንዲገባ እያደረገው ይገኛል። ይህ ደግሞ መረጋጋትን ሳይሆን አዲስ ቅራኔን ብቻ ነው የሚጋብዘው።

    “አሁን እኮ የኔቶ ዓላማ የጂኦ-ፖለቲካዊ ተጽዕኖ መፍጠሪያ እና ማሰፋፊያ ወደ መሆን አዘንብሏል [...] የአፍሪካ ሉዓላዊነት የሚረጋገጠው በኢኮኖሚ ነፃነት እና በራሷ የንግድ ማዕቀፎች እንጂ ከውጭ በሚመጡ ውሱን እርዳታዎች ብቻ አይደለም […] እኛ አፍሪካውያን የምንፈልገው አካታች የዓለም ሥርዓትን እንጂ አዲስ የቀዝቃዛ ጦርነት ውጥረት አይደለም” በማለት በኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ የዓለም አቀፍ ግንኙነት እና ዲፕሎማሲ መምህር እንዳለ ንጉሴ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።

    የዛሬው ድራም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅታችን ኔቶ ወደ እስያ-ፓስፊክ የሚያደርገው ስትራቴጂካዊ መስፋፋት ከብሪክስ እያደገ ከመጣው ባለብዙ ዋልታ አስተሳሰብ ጋር እንዴት እንደሚጣጣም በዋናነት ይዳስሳል። መምህር እና ተመራማሪ እንዳለ ንጉሴ በዚህ ጉዳይ ላይ ወቅታዊ ማብራሪያ የሚሰጡን ዕንግዳችን ናቸው።

    ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ:

    1 hr 1 min
  • በብራና የተጻፈ፡ የኢትዮጵያ ሕያው የሥልጣኔ መዝገብ
    የዛሬው የ ድራም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅታችን ትኩረት ከነሓሴ 28፣ 2018 ዓ.ም. እስከ መስከረም 3፣ 2019 ዓ.ም. በአዲስ አበባ በመካሄድ ላይ ባለው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የብራና መጻሕፍት ዓለም አቀፍ ኤግዚቢሽን ላይ ነው። በዚሁ ጉዳይ ላይ የሐመር ብርሃን የብራና መጻሕፍት ሥራ ድርጅት የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ትንሳኤ ተስፋሚካኤልን እና የፕሮጀክት ማናጀሯን ቃልኪዳን ብርሃኑን አነጋግረናል።
    1 hr 1 min
  • ከቃል ኪዳን ወደ ትግበራ ኃይል፡ የአፍሪካ የአየር ንብረት አጀንዳ
    በዛሬው የድረም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅታችን ከባድ ድርቅና ጎርፍ የዜጎችን የዕለት ተዕለት ኑሮ ከመፈተኑ ጀምሮ፣ እስከ ታላላቅ የድርድር መድረኮች ቃላት ከድርጊት የሚበልጡበትን አዝማሚያ ጨምሮ፣ አፍሪካ የአየር ንብረት ሉአላዊነቷን ለማስከበር የምታደርገውን የረጅም ጊዜ ትግል ታላቅ ታሪክ አካል አድርገን እናቀርበዋለን። ዝግጅቱን ከ 14ኛው የአፍሪካ የአየር ንብረት ለውጥና ልማት ጉባኤ አንጻር የምናቀርበው ሲሆን፣ በጉባኤ ላይ ተገኝተን ዮሴፍ አመሓን (ዶ/ር)፣ በተባበሩት መንግስታት የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን የአየር ንብረት ተማራማሪ ጨምሮ የተለያዩ ተሳታፊዎችን አውርተናል።
    1 hr 1 min
  • የአፍሪካ የሰላም መዋቅር፡ የአፍሪካ ህብረትን ሚና ማጠናከር
    የዛሬው የድረም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅታችን ሦስት ጉዳዮችን ይዳስሳል። በቀዳሚው ጉዳዩ የአፍሪካ ህብረት ከዲፕሎማሲ ውይይት ወደ የዜጎችን ደህነት ጥበቃ የሚቀይርበትን እና የፋይናንስ ጥገኝነትን በመቀነስ የሰላም ስልታዊ አቅሙን የሚያጠናክርበትን መንገድ ይቃኛል። በሁለተኛ ጉዳዩ ኢትዮጵያ የ 2029 ኙን የአፍሪካ ዋንጫ ለማዘጋጀት ያቀረበችውን ጥያቄ ይዳስሳል። ለዚህም የብሔራዊ እግር ኳስ ፌዴሬሽኑን ፕሬዝደንት ኢሳያስ ጂራ አነጋግሯል። በሦስተኛው ጉዳዩ ደግሞ ጳጉሜን 1 የጀመረውንና እስከ ጳጉሜን 5 የሚዘልቅዉን ፌስቲቫል ይቃኛል።
    1 hr 1 min

About Drum of Changes

From the publisher's feed

From the heart of ancient kingdoms to the pulse of modern cities, a new rhythm echoes across the continent. Africa is rising — a formidable force shaping the world’s future. For generations, Africa…