Sign up to save your podcastsEmail addressPasswordRegisterOrContinue with GoogleAlready have an account? Log in here.
From the heart of ancient kingdoms to the pulse of modern cities, a new rhythm echoes across the continent. Africa is rising — a formidable force shaping the world’s future. For generations, Africa ha... more
FAQs about Drum of Changes:How many episodes does Drum of Changes have?The podcast currently has 38 episodes available.
April 11, 2026ለዘላቂ ሰላም ወይስ ለዳግም ጦርነት ዝግጅት? የኢራን-አሜሪካና እስራኤል የሁለት ሳምንት የተኩስ አቁም እንቆቅልሽ“ኢራን እና አሜሪካ መሰረታዊ የግጭት መንሳኤ የሆኑ ጉዳዮችን በተመለከተ መግግባባት ላይ ከደረሱ ወደ ዘላቂ ሰላም ሊመጡ ይችላሉ። ነገር ግን እነዚህን መሰረታዊ መንሳኤዎች መፍታት ከልቻሉ፣ ይህ የሁለት ሳምንት ጊዜያዊ የተኩስ አቁም ስምምነት ጊዜ በመግዛት አቅም አሰባስበው ዳግም ወደጦርነት ለመመለስ የሚያስችላቸውን ሁኔታ እየፈጠሩ ሊሆን ይችላል" ሲሉ በውጭ ጉዳይ ኢንስቲቲዩት የመካከለኛው ምስራቅ ከፍተኛ ተመራማሪ መሐመድ ሰኢድ (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናገሩ።በዛሬው የድረም ኦቭ ቼንጅስ ጉዳያችን በፈርጆቹ መጋቢት 8፣ 2026 ኢራን እና አሜሪካ የተስማሙበትን የሁለት ሳምንት የተኩስ አቁም ስምምነት ስፋት ይቃኛል። በውጭ ጉዳይ ኢንስቲቲዩት ከፍተኛ ተመራማሪ መሐመድ ሰኢድን (ዶ/ር) አነጋግረናል። በሁለተኛው ክፍል ደግሞ በፈርጆቹ መጋቢት 7፣ 2026 በሆርሙዝ ሰርጥ የመጓጓ ነፃትን ለማስከበር የኃይል አማራጭን ለመውሰድ የጸጥታው ምክር ቤት ቀርቦ የነበረውን ረቂቅ የውሳኔ ሐሳብ በሩሲያና ቻይና ድምጽን በድምጽ የመሻር መብት ውድቅ መሆኑን እንመለከታለን። ይህ ሁኔታ አቅሙ እየተዳከመ ስለመጣው የምዕራቡ ዓለም ሁኔታ ምን ይነግረናል? የእዮብዘር ዘውዴ፣ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነቶች መምህር በዚህ ጉዳይ ዙሪያ አስተያየታቸውን አጋርተዉናል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ:...more1hPlay
April 07, 2026አፍሪካን የመበየን አባዜ፤ የምዕራባውያን የጥናት ተቋማት የኒዮ-ኮሎኒያሊዝም መሣሪያነት“የምዕራባውያን ስረዓቶች በአመፃ የታጀቡ ናቸው። ዛሬ በዓለም ዙሪያ ያሉትን ብዙ ግጭቶች ብንመለከት፣ በአንድ ወይም በሌላ መልኩ የምዕራባውያን እጅ አለበት። ይህንን ሁኔታ በተመሳሳይ ቀውስ ውስጥ ሁለት ሚና ይዞ መገኘት እለዋለሁ። ችግር ፈጣሪዎች ለችግሩ ስም ያወጡለታል፣ ለፈጠሩት ችግር ደግሞ መፍትሄ ፈጣሪዎች ሆነው ይመጣሉ። ይህ ምዕራባውያን መገለጫ ነው” ሲሉ በደቡብ አፍሪካው ዩኒቨርሲቲ የድህረ ምረቃ ምርምር ባልደረባ ቺዶካሼ ንዬሬ (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግሩ።በዛሬው የድረም ኦቭ ቼንጅስ ቀዳሚው ጉዳያችን አፍሪካ የምትታይበትን እይታ የሚቀርፀው ማነው ስንል እንተይቃለን። ለዚህም በደቡብ አፍሪካ ዩኒቨርሲቲ የታቦ ምቤኪ የህዝብ እና ዓለም አቀፍ ጉዳዮች የድህረ ምረቃ ምርምር ባልደረባ ቺዶካሼ ንዬሬን (ዶ/ር) አነጋግረናል። ሁለተኛ ጉዳያችን ደግሞ 10ኛው የኢትዮ ጤና ኤግዚቢሽን እና ኮንግረስ 2026 ላይ የሚያተኩር ይሆናል።ሙሉ መረጃውን ለማግኘት በእንግሊዘኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ያዳምጡ:...more1h 0minPlay
April 01, 2026የአውሮፓ አይሁዶችን በኢትዮጵያ ለማስፈር ተይዞ የነረው ውጥና የኢትዮጵያ ምላሽ“እርግጥ ነው፣ ሐሳቡ [የአውሮፓ አይሁዶችን በኢትዮጵያ ማስፈርን] በተመለከተ ለንጉሠ ነገሥት ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ የተላከው ደብዳቤ እንግሊዝ እና አሜሪካ መንግሥት ድጋፍ ነበረው። ይሁን እንጂ የኢትዮጵያ መንግሥት በአንድ አገር ውስጥ ሌላ አገር ለመፍጠር የሚያስችል ይሁንታ ለመስጠት ፈቃደኛ አልሆነም፤ ምክኛቱም ይህንን መፍቀድ የአገሪቱን ሉዓላዊነት አሳልፎ የሚሰጥ ነውና” ሲሉ ዓለም አቀፍ የፖሊሲ አማካሪው ቆስጠንጢኖስ በርኸተሰፋ (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።በዛሬው የድረም ኦቭ ቼንጅስ ቀዳሚው ጉዳያችን ወቅታዊውን የመካከልኛው ምስራቅ ሁኔታ መነሻ አድርገን በኢትዮጵያ የቀድሞው ሐረር ጠቅላይ ግዛት የአውሮጳ አይሁዶችን ለማስፈር ተይዞ የነበረው ውጥን እና የኢትዮጵያን ምላሽ ያስቃኘናል። በቀደመው ጊዜ ዓለም አቀፍ የፖሊሲ አማካሪ እና የምጣኔ ሀብት ባለሙያ ቆስጠንጢኖስ በርኸተሰፋ (ዶ/ር) አነጋግረናቸዋል። የሃርቫርድ ዩኒቨርሲቲ የህዝብ ጤና ባለሙያ እና ምሁር እንዲሁም ተመራማሪ የሆኑትን ኃይሉ ታምሩን (ዶ/ር) አነጋግረን ሰው ሰራሽ አስተውሎ በአፍሪካ የጤና ምርምርን ከማገዝ አንፃር የሚኖረዉን ሚና ቃኝተናል።ሙሉ መረጃውን ለማግኘት በእንግሊዘኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ያዳምጡ:...more1h 0minPlay
March 30, 2026የፈውስ ክር:- በሚገባው ልክ ያልታወቀው በገናበገና በመንፈሳዊ ዝማሬዎች ውስጥ ካለው ቦታ ባለፈ፣ ለመንፈሳዊ ፈውስነት መዋል የሚችል ጥንታዊ እና ጥልቅ ሚስጥር ያለው ማሳሪያ ነው።“ዘመናዊ የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎች ከጊዜ ወደ ጊዜ ከተፈጥሮ ውጪ የሆኑ ንዝረቶችን ያመነጫሉ ... ይህ ደግሞ የሰዎችን አዕምሮ ሎም አካል ሊጎዳ ይችላል። ይሁን እንጂ በገና በተቃራኒው ከዚህ በተለየ መልኩ ጥቅም ይሰጣል ... የውስጥ ሰላምን እና እርጋታን የሚያጎናፅፉ ንዝረቶችን ያመነጫል” ሲሉ ፕሮፌሰር ብረሃኑ ግዛው ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።በዛሬው የድረም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅታችን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ውስጥ ካሉ ጥንታዊ እና የጥልቅ መንፈሳዊ ዝማሬ ማጀቢያዎች መካከል በገና እንቃኛለን። በገና ለመንፈሳዊ ፈውስ መዋል ስለመቻሉም እናነሳለን። ለዚህም ብፁዕ አቡነ ፊሊጶስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የደቡብ ኦሞ ሀገረ ስብከት ሓላፊ እና የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ዩኒቨርሲቲ ጠባቂ፣ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ግዛው የድምፅ ኢንጅነር፣ አቶ ካሳሁን ሓይለማሪያም የማሕበረቅዱሳን ሰብሳቢ፣ እንዲሁም ብሌን ዮሴፍ የሙዚቃ መምህርት እና ባለሞያን አነጋግረናል። ሙሉ መረጃ ለማግኘት በእንግሊዘኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራምን ያዳምጡ: ...more1h 0minPlay
March 26, 2026የሕዝብ ቁጥር ፖሊሲ እንደ ጂኦፖለቲካ መሣሪያ፡- ‘የኪሲንጀር ሪፖርት’ እና የደቡቡ ዓለም እውነታ“የህዝብ ቁጥር መጨመርን በመግታት ላይ ብቻ አላተኮሩም [ምዕራባውያን]። በአዳጊ ሀገራት ውሰጥ የህዝብ ቁጥር መጨመርን በመግታት፣ የሀገራቱን ሀብት ለመበዝበዝ የሚያመች ስትራቴጂ እየከተሉ ነበር። ይህ ያፈጠጠ የብዝበዛ አካሄድ ነው። ምክንያቱም በእነዚህ ሀገራት አነስተኛ የህዝብ ቁጥር መኖር ማለት ለምዕራቡ ዓለም በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚ፣ በማህበራዊ እና በቴክኖሎጂ ዘርፎች ላይ ቁጥጥር ወይም ተጽዕኖ እንዲያሳድሩ ቀላል ይሆንላቸዋል” ሲሉ በዲላ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነቶች መምህሩ ዳዊት መዝገበ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።በዛሬው የድረም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅታችን እ.ኤ.አ. በ1974 በአሜሪካ ብሔራዊ ደህንነት ምክርቤት የተዘጋጀውንና ‘የኪሲንጀር ሪፖርት’ በመባል የሚታወቀውን ሰነድ በማዳሰስ ላለፉት አስርት ዓመታት የምዕራቡ ዓለም በተለይም በተመረጡ 13 የደቡቡ ዓለም ሀገራት ላይ ትኩረት በማድረግ፣ የህዝብ ቁትራቸው እንዳያድግ ሲከተለው የነበረውን ስትራቴጂ እንፈሻለን። በዲላ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነቶች መምህሩ ዳዊት መዝገበ ጋር ቆይታ በማድረግ ይህንን ሰነድ ፈትሸነዋል።ሙሉ መረጃውን ለማግኘት በእንግሊዘኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ያዳምጡ:...more1h 0minPlay
March 24, 2026ካሳ እና ፍትህ፡ በፓን አፍሪካዊ ማህደረ ትውስታ እና በዓለም አቀፍ የኃይል ፖለቲካ መካከል“አፍሪካ የራሷን ታሪክ፣ የራሷን እውነታ ለዓለም የምትነግርበት ድምፅ ይኖራት ዘንድ ፍፁም አስፈላጊ ነው። ምክኛቱ ደግሞ እስከዛሬ ድረስ አፍሪካን ብሎም የአፍሪካን ታሪክ በራሳቸው መንገድ ሲተርኩ ስለአፍሪካ ሲናገሩ የቆዩት አውሮፓውያን ናቸውና። ከአፍሪካ ውጭ [በአሜሪካ] እንዳደገች አንዲት ጥቁር ሰው እውነቱን ለመናገር ስለአፍሪካ መልካም ነገር ሰምቼ አላውቅም” ሲሉ ፓናፍሪካኒስቷ ጃኔል ሆይሌት ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።በዛሬው የድረም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅታችን የባሪያ ንግድ፣ የቅኝ ግዛት እና መዋቅራዊ ብዝበዛ በጥቁር ሕዝቦች ላይ ጥሎ ስላለፈው አሻራ እንቃኛለን። ጨምረንም መላው የጥቁር ሕዝቦች ለፍትህ እና ካሳ የሚያደርጉትን የትግል ጉዞ እንመለከታለን። በዚህ ጉዞ ውስጥም ለጥቁር ሕዝቦች የቆሙ ተቋሟት ዛሬም ድረስ ከቀጠለው የቀድሞ ቅኝ ገዥዎች ግብዝነት ጋር የሚያደርጉትን ትግል እንፈትሻለን። ለዚህም ታዲያ ኑሯቸውን በአዲስ አበባ ያደረጉት ጥቁር አሜሪካዊቷ ፓናፍሪካኒስት፣ ደራሲ እና ወደ አፍሪካ የመመለስ ንቅናቄ አንቂ ጃኔል ሆይሌትን ጋብዝን በእነዚህ ጉዳዮች ዙሪያ ሐሳባቸውን አጋርተዉናል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት በእንግሊዘኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራሙን ያዳምጡ:...more1h 0minPlay
March 18, 2026በአፍሪካ የጤና ሉዓላዊነትን የመቀዳጀት ትርጉም እና አስፈላጊነት - መልከ ብዙው ትግልየኮቪድ-19 ወረርሽኝ ያለጠው እውነታ ቢኖር አፍሪካ ዛሬም ድረስ የመድኃኒት አቅርቦት ፍላጎቷ በምዕራባውያን መድኃኒት አቅራቢ ኩባንያዎች በጎ ፈቃድ ላይ የተመሰረተ መሆኑን ነው።“የምዕራቡ ዓለም የአፍሪካን የሕዝብ ቁጥር ለመቀነስ ከሚፈልግባቸው ምክንያቶች መካከል ዘረኛ ፖሊሲው አንደኛው ነው [...] ሌላኛው ምክንያት ደግሞ ብዙ ወጣት ትውልድ ያላት አፍሪካ የዓለምን ሀብት ለመቆጣጠር ለያዙት ግብ እንቅፋት ትሆናለች የሚል ነው [...] ብሪክስ አፍሪካ ስለአፍሪካ የምታስብበት ብሎም አፍሪካ የራሷን ጥቅም ማስጠበቅ የምትችልበት ጠንካራ ህብረት ነው” ሲሉ የበርካታ ሽልማቶች አሸናፊ ደቡብ አፍሪካዊቷ የማህበረሰብ ጤና ባለሞያ ሻኪራ ቹናራ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።በዛሬው የድረም ኦቭ ቼንጅስ ቀዳሚው ትንቅራችን በአፍሪካ የጤና ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ አጣዳፊ ጉዳይ ስለመሆኑ ያስቃኘናል። በዚህ ጉዳይ ላይ ደቡብ አፍሪካዊቷ የበርካታ ሽልማቶች አሸናፊ እና የማህበረሰብ ጤና ባለሞያዋ ሻኪራ ቹናራን አነጋግረናል። ተከታዩ ጥንቅራችን ደግሞ፣ በአፍሪካ ሌላኛውን የሉዓላዊነት ገፅታ ያስቃኘናል። በዚህ ጉዳይ ላይ አቶ ምስጋናው እያሱ፣ በፕላን እና ልማት ሚኒስቴር የአየር ንብረት ፋይናንስ አማካሪ እንዲሁም ኮሚሽነር ሞሰስ ቪላካቲ፣ በአፍሪካ ህብረት የግብርና፣ የገጠር ልማት፣ የሰማያዊ ኢኮኖሚ እና ዘላቂ አካባቢ ኮሚሽነር ጋር አጠር ያለ ቆይታ አድርገናል ።ሙሉ መረጃዉን ለማግኘት በእንግሊዘኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ያዳምጡ:...more1h 0minPlay
March 11, 2026የኩባ ውለታና የአፍሪካ ምላሽ ? ጊዜ ያነሳው ጥያቄኩባ ለአፍሪካ የነፃነት እና የሉዓላዊነት ትግል የከፈለችው መስዕዋትነት የአህጉሪቱ የማይረሳ የታሪክ አንዱ ገጽ ነው።“ኩባ [...] የህልውና ፈተና በገጠመን ወቅት መስዋዕትነት በመክፈል ከጎናችን ቆማለች፤ አፍሪካውያን ግን በተዋለልን ልክ ለኩባ ደርሰንላታል ወይ?” ሲሉ የኢትዮ-ኩባ ወዳጅነት ማህበር አስተባባሪ አቶ አበበ አያሌው ይጠይቃሉ።ከየካቲት 29 እስከ መጋቢት 5/2018 ዓ.ም. “ህብረት ከግላኮማ ነፃ ለሆነች ዓለም” በሚል ጭብጥ የዓለም የግላኮማ ሳምንት ይከበራል። “ግላኮማ ታማሚዎች ሳያውቁት የማይቀለበስ የዓይነ ስውርነት የሚያስከትል በሽታ ቢሆንም፣ የግንዛቤ እጥረት ሁኔታውን አክብዶታል” ሲሉ የግላኮማ ስፔሻሊስቷ ዶ/ር አበባ ተክለጊዮርጊስ ለስፑትኒክ አፍሪካ ገልጸዋል።በዛሬው የ ድሪም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅታችን፣ ስለ ግላኮማ በሽታ ከስፔሻሊስትና ተባባሪ ፕሮፌሰር ዶ/ር አበባ ተክለጊዮርጊስ ጋር እንመክራለን። በሁለተኛው ክፍላችን ደግሞ፣ ስለ ኩባ የታሪክ መስዋዕትነት ከኢትዮ-ኩባ ወዳጅነት ማህበር አስተባባሪ አቶ አበበ አያሌው ጋር እንቆያለን።ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ:...more1h 0minPlay
March 05, 2026የመካከለኛው ምስራቅ ቀውስ:- የአፍሪካ አገራትን እንዴት ሊጎዳ ይችላል ?የመካከለኛው ምስራቅ ውጥረት የነዳጅ ዋጋን ብሎም የዋጋ ግሽበትን እያባባሰ ባለብት ሁኔታ አፍሪካ ቆማ መመልከት አትችልም። አማራጭ የኃይል አቅርቦት ላይ ማተኮር፣ ቀጣናዊ ትስስርን ማፋጠን ግድ ይላታል።“ለአፍሪካ ይህ በጣም መጥፎ ዜና ነው። የነዳጅ ምርቶችን ወደ አገር ውስጥ የሚያስገቡ አብዛኞቹ አገራት እንዲህ ዓይነቱን ጫና ለቋቋም እጅጉን ይቸገራሉ። [...] ስለዚህ የአፍሪካ አገራት ስለ አማራጭ የኃይል ምንጮች የሚያስቡበት ጊዜ አሁን ነው።እንደሚታወቀው አፍሪካ ብዙ አማራጮች አሏት”ሲሉ ዓለም አቀፍ የፖሊሲ አማካሪው ቆስጠንጢኖስ በርኸተስፋ(ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።በዛሬው የድረም ኦቭ ቼንጅስ ቀዳሚ ዝግጅታችን አሜሪካ እና እስራኤል በኢራን ላይ የከፈቱትን የጦር ዘመቻ ተከትሎ በአፍሪካ ላይ የሚመጣውን ሁለንትናዊ ጫና እና መፍትሄዎቹን በተመለከተ ዓለም አቀፍ የፖሊሲ አማካሪዉ ቆስጠንጢኖስ በርኸተስፋ (ዶ/ር) አነጋግርናል። በሁለተኛው ጥንቅራችን ደግሞ መጋቢት 17-18 በአዲስ አበባ የሚካሄደውን አራተኛውን “በኢትዮጵያ ኢንቨስት ያድርጉ” ዓለም አቀፍ የኢንቨስትመንት ፎረምን በተመለከተ ከኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ዘለቀ ተመስገን (ዶ/ር) ጋር ያደረግነውን ቆይታ ታደምጣላችሁ።በእንግሊዘኛ ቋንቋ የቀረበውን ሙሉ መረጃ ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ:...more1h 0minPlay
February 25, 2026የሩሲያ ቀይ መስመር :- የፈረንሳይ እና ብሪታንያ ዩክሬንን የኒዩክሌር ጦር መሳሪያ የማሰታጠቅ ፍላጎትፈረንሳይ እና ብሪታኒያ ለዩክሬን የኒዩክሌር ጦር መሳሪያ ለማስታጠቅ መንቀሳቀሳቸውን የሩሲያ የውጭ መረጃ ደህንነት ይፋ አድርጓል።"ምዕራባውያን ሩሲያን ወደ አቅም አልባ ትንንሽ ግዘቶች የመከፋፈል እቅዳቸው የቆየ ነው […] ከሰሞኑ ለዩክሬን የኒዩክሌር ጦር መሳሪያ ለማስታጠቅ ማሰባቸው ይህ እቅዳቸው በመክሸፉ ተስፋ የመቁረጣቸው ማሳያ ነው" ሲሉ የዓለም አቀፍ ግንኙነቶች መምህሩ ዳዊት መዝገበ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።በዛሬው የድረም ኦቭ ቼንጅስ ልዩ ዝግጅታችን፣ የፈረንሳይ እና ብሪታንያ ለዩክሬን የኑክሌር ጦር መሳሪያ ለማስታጠቅ መዘጋጀታቸው ምን ዓለም አቀፍ ትርጓሜ አለው ስንል በዲላ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነቶች መምህር የሆኑት ዳዊት መዝገበን አነጋግረናል።በእንግሊዘኛ ቋንቋ የቀረበውን ሙሉ መረጃ ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ:...more1h 0minPlay
FAQs about Drum of Changes:How many episodes does Drum of Changes have?The podcast currently has 38 episodes available.