
Sign up to save your podcasts
Or


"አፍሪካ ከዚህ ጉባኤ [ከ ሴንት ፒተርስበርግ ኢንተርናሽናል ኢኮኖሚክ ፎረም] ትጠቀማለች [...] አሜሪካ በኢራን፣ በሩሲያ እና በሌሎች ሀገራት ላይ የጣለቻቸው ማዕቀቦ ምዕራባውያኑ በፋይናንስ አስተዳደር ረገድ እምነት የሚጣልባቸው አጋሮች ሊሆኑ እንደማይችሉ እያሳየ ጉዳይ ነው። በዚህም ምክንያት ሀገራት የዕዳ ቀውስን ለመፍታት ጨምሮ ለራሳቸው የሚበጀ የተሻለ ጎዳናነ መሻት ይኖርባቸዋል [...] ጉባኤው ከዚህ አንፃር ፋየዳው የጎላ ነው" ሲሉ የፖሊሲ አማካሪ እና የምጣኔ ሀብት ባለሙያው ቆስጠንጢኖስ በርኸተስፋ (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።
የዛሬው የድረም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅታችን ቀዳሚው ጉዳይ እ.ኤ.አ. ከ ሰኔ 3 እስከ 6 በሩሲያዋ ሴንት ፒተርስበርግ እየተካሄደ ባለው ሴንት ፒተርስበርግ ኢንተርናሽናል ኢኮኖሚክ ፎረም 2026 ላይ ያተኩራል፡፡ ''ለአፍሪካስ ምን አማራጮችን ይዞ ይመጣል?'' ስንል እንጠይቃለን። በጉዳዩ ላይ የፖሊሲ አማካሪ እና የምጣኔ ሀብት ባለሙያውን ቆስጠንጢኖስ በርኸተስፋ (ዶ/ር) አነጋግረናል። በሁልተኛው ጉዳያችን ደግሞ የታንዛንያ ፕሬዝደንት ሳሚያ ሱሉሁ ሀሰን የሩሲያ ጉብኝት አንድምታዎች በስፋት እንዳሰሳለን። ለዚህም ታንዛንያውያን የምጣኔ ሀብት እና የዓለም አቅፍ ፖለቲካ ተንታኞችን አነጋገርናል።
ሙሉ መረጃውን ለማግኘት በእንግሊዘኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ያዳምጡ:
ሙሉ መረጃውን ለማግኘት በእንግሊዘኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ያዳምጡ:
የአፍሪካ ቀን የአሁኑ የአፍሪካ ህብረት በፈረንጆቹ ሚያዝያ 25፤ 1963 የተመሰረተበትን ቀን የሚዘክር እለት ነው፤ በየዓመቱም ይከበራል።
“የቀድሞው የአፍሪካ አንድነት ድርጅት፤ የአሁኑ የአፍሪካ ህብረት ምስረታ ወቅት የነበረው የአንድነት መንፈስ በዛሬዪቱ ተቀዛቅዟል [...] የአፍሪካ ነፃነት ቀንም የፍሪካን ነፃነት እያከበርን፣ ስለአፍሪካ እጣፈንታ ኮስተር ብለን የምንወያይበት እለትም ሆኖ ማለፍ ነው ያለበት”ሲሉ የአፍሪካ ዴይ ኢኒሼቲቭ ሶሳይቲ ኦርጋናይዜሽን መስራች እና ዋና ዳይሬከተር አሮን ስይፉ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።
በዛሬው የድረም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅታችን ታዲያ፣ የነፃዪቱ አፍሪካ ተላሚዎች፣ አባቶች ያለሟትን አፍሪካ ዛሬ ካለችበት ሆነን እንቃኛታለን። አሮን ሰይፉ፣ የአፍሪካ ዴይ ኢኒሼቲቭ ሶሳይቲ ኦርጋናይዜሽን መስራች እና ዋና ዳይሬከተር በመረጥነው ርእስ ዙሪያ ሀሳባቸውን አጋርተውናል።
ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ሙሉ ፕሮግራሙን ይከታተሉ ፡
ሙሉ መረጃውን ለማግኘት በእንግሊዝኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ያዳምጡ:
• ዓለም አቀፍ ፍትህ ወይንስ የምዕራባውያን የበላይነት መጠቀሚያ? — ከዓለም አቀፍ ግንኙነት ምሁሩ ፕሮፌሰር ኤሊ ጂርጂ ኤልያስ ጋር።
• የአፍሪካ ከተሞች የወደፊት ዕጣ ፈንታና የቤት ልማት ፈተናዎች — ከዩኤን-ሀቢታት (UN-Habitat) ዋና ዳይሬክተር አናክላውዲያ ሮስባክ ጋር።
• የመድኃኒት ዋስትና እና የአፍሪካ ሉዓላዊነት — ከኢትዮጵያ መድኃኒትና የሕክምና መገልገያ አቅራቢዎች ማኅበር ፕሬዝዳንት ዶ/ር ዳንኤል ዋክቶሌ ጋር።
ሙሉ መረጃውን ለማግኘት በእንግሊዝኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ያዳምጡ:
“ዋይልድቤሪስ ጀማሪ ኩባንያ አይደለም። ከ20 ዓመታት በላይ ሲሰራ የቆየ ነው […] የኢትዮጵያ ምርቶች ለዓለም አቀፍ ገበያዎች እንዲደርሱ ያስችላል […] ክፍያዎችን በተመለከተም ከየአገራቱ ገበያ ጋር የሚጣጣሙ ይሆናል፤ ለምሳሌ በአሁኑ ወቅት ግብይት በኢትዮጵያ ብር መፈጸም እንዲቻል ከአገር ውስጥ የፋይናንስ ተቋማት ጋር በመተባበር ግብይቶችን ለማመቻቸት ትኩረት ሰጥተን እየሰራን እንገኛለን።” ሲሉ የዋይልድቤሪስ የኢትዮጵያ ተወካይ ብሩክ ገነነ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።
በዛሬው የድረም ኦቭ ቼንጅስ ልዩ ዝግጅታችን፣ ትልቁ የሩሲያ የኤሌክትሮኒክ መገበያያ መድረክ ዋይልድቤሪስ ወደ ኢትዮጵያ ገበያ መቀላቀሉን መነሻ በማድረግ ይህ ስርዓት በኢትዮጵያ እንዴት እየተዋወቀ እንደሆነ እና ለንግዱ ማኅበረሰብ እና ለሸማቾች ምን ማለት እንደሆነ፣ ሰፊ አቅም ካለው የአፍሪካ ገበያ ተደራሽነት ጋር የሚኖረውን ግንኙነት ጨምሮ ሌሎች ጉዳዮችን እንዳስሳለን። የዋይልድቤሪስ የኢትዮጵያ ተወካይ ብሩክ ገነነ ደግሞ ለጥያቄዎቻችን ምላሽ እየሰጡ አብረዉን ቆይታ ያደርጋሉ።
ሙሉ መረጃውን ለማግኘት በእንግሊዝኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ያዳምጡ:
“ኢራን እና አሜሪካ መሰረታዊ የግጭት መንሳኤ የሆኑ ጉዳዮችን በተመለከተ መግግባባት ላይ ከደረሱ ወደ ዘላቂ ሰላም ሊመጡ ይችላሉ። ነገር ግን እነዚህን መሰረታዊ መንሳኤዎች መፍታት ከልቻሉ፣ ይህ የሁለት ሳምንት ጊዜያዊ የተኩስ አቁም ስምምነት ጊዜ በመግዛት አቅም አሰባስበው ዳግም ወደጦርነት ለመመለስ የሚያስችላቸውን ሁኔታ እየፈጠሩ ሊሆን ይችላል" ሲሉ በውጭ ጉዳይ ኢንስቲቲዩት የመካከለኛው ምስራቅ ከፍተኛ ተመራማሪ መሐመድ ሰኢድ (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናገሩ።
በዛሬው የድረም ኦቭ ቼንጅስ ጉዳያችን በፈርጆቹ መጋቢት 8፣ 2026 ኢራን እና አሜሪካ የተስማሙበትን የሁለት ሳምንት የተኩስ አቁም ስምምነት ስፋት ይቃኛል። በውጭ ጉዳይ ኢንስቲቲዩት ከፍተኛ ተመራማሪ መሐመድ ሰኢድን (ዶ/ር) አነጋግረናል። በሁለተኛው ክፍል ደግሞ በፈርጆቹ መጋቢት 7፣ 2026 በሆርሙዝ ሰርጥ የመጓጓ ነፃትን ለማስከበር የኃይል አማራጭን ለመውሰድ የጸጥታው ምክር ቤት ቀርቦ የነበረውን ረቂቅ የውሳኔ ሐሳብ በሩሲያና ቻይና ድምጽን በድምጽ የመሻር መብት ውድቅ መሆኑን እንመለከታለን። ይህ ሁኔታ አቅሙ እየተዳከመ ስለመጣው የምዕራቡ ዓለም ሁኔታ ምን ይነግረናል? የእዮብዘር ዘውዴ፣ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነቶች መምህር በዚህ ጉዳይ ዙሪያ አስተያየታቸውን አጋርተዉናል።
ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ:
“የምዕራባውያን ስረዓቶች በአመፃ የታጀቡ ናቸው። ዛሬ በዓለም ዙሪያ ያሉትን ብዙ ግጭቶች ብንመለከት፣ በአንድ ወይም በሌላ መልኩ የምዕራባውያን እጅ አለበት። ይህንን ሁኔታ በተመሳሳይ ቀውስ ውስጥ ሁለት ሚና ይዞ መገኘት እለዋለሁ። ችግር ፈጣሪዎች ለችግሩ ስም ያወጡለታል፣ ለፈጠሩት ችግር ደግሞ መፍትሄ ፈጣሪዎች ሆነው ይመጣሉ። ይህ ምዕራባውያን መገለጫ ነው” ሲሉ በደቡብ አፍሪካው ዩኒቨርሲቲ የድህረ ምረቃ ምርምር ባልደረባ ቺዶካሼ ንዬሬ (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግሩ።
በዛሬው የድረም ኦቭ ቼንጅስ ቀዳሚው ጉዳያችን አፍሪካ የምትታይበትን እይታ የሚቀርፀው ማነው ስንል እንተይቃለን። ለዚህም በደቡብ አፍሪካ ዩኒቨርሲቲ የታቦ ምቤኪ የህዝብ እና ዓለም አቀፍ ጉዳዮች የድህረ ምረቃ ምርምር ባልደረባ ቺዶካሼ ንዬሬን (ዶ/ር) አነጋግረናል። ሁለተኛ ጉዳያችን ደግሞ 10ኛው የኢትዮ ጤና ኤግዚቢሽን እና ኮንግረስ 2026 ላይ የሚያተኩር ይሆናል።
ሙሉ መረጃውን ለማግኘት በእንግሊዘኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ያዳምጡ:
በዛሬው የድረም ኦቭ ቼንጅስ ቀዳሚው ጉዳያችን ወቅታዊውን የመካከልኛው ምስራቅ ሁኔታ መነሻ አድርገን በኢትዮጵያ የቀድሞው ሐረር ጠቅላይ ግዛት የአውሮጳ አይሁዶችን ለማስፈር ተይዞ የነበረው ውጥን እና የኢትዮጵያን ምላሽ ያስቃኘናል። በቀደመው ጊዜ ዓለም አቀፍ የፖሊሲ አማካሪ እና የምጣኔ ሀብት ባለሙያ ቆስጠንጢኖስ በርኸተሰፋ (ዶ/ር) አነጋግረናቸዋል። የሃርቫርድ ዩኒቨርሲቲ የህዝብ ጤና ባለሙያ እና ምሁር እንዲሁም ተመራማሪ የሆኑትን ኃይሉ ታምሩን (ዶ/ር) አነጋግረን ሰው ሰራሽ አስተውሎ በአፍሪካ የጤና ምርምርን ከማገዝ አንፃር የሚኖረዉን ሚና ቃኝተናል።
ሙሉ መረጃውን ለማግኘት በእንግሊዘኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ያዳምጡ:
በገና በመንፈሳዊ ዝማሬዎች ውስጥ ካለው ቦታ ባለፈ፣ ለመንፈሳዊ ፈውስነት መዋል የሚችል ጥንታዊ እና ጥልቅ ሚስጥር ያለው ማሳሪያ ነው።
“ዘመናዊ የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎች ከጊዜ ወደ ጊዜ ከተፈጥሮ ውጪ የሆኑ ንዝረቶችን ያመነጫሉ ... ይህ ደግሞ የሰዎችን አዕምሮ ሎም አካል ሊጎዳ ይችላል። ይሁን እንጂ በገና በተቃራኒው ከዚህ በተለየ መልኩ ጥቅም ይሰጣል ... የውስጥ ሰላምን እና እርጋታን የሚያጎናፅፉ ንዝረቶችን ያመነጫል” ሲሉ ፕሮፌሰር ብረሃኑ ግዛው ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።
በዛሬው የድረም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅታችን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ውስጥ ካሉ ጥንታዊ እና የጥልቅ መንፈሳዊ ዝማሬ ማጀቢያዎች መካከል በገና እንቃኛለን። በገና ለመንፈሳዊ ፈውስ መዋል ስለመቻሉም እናነሳለን። ለዚህም ብፁዕ አቡነ ፊሊጶስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የደቡብ ኦሞ ሀገረ ስብከት ሓላፊ እና የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ዩኒቨርሲቲ ጠባቂ፣ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ግዛው የድምፅ ኢንጅነር፣ አቶ ካሳሁን ሓይለማሪያም የማሕበረቅዱሳን ሰብሳቢ፣ እንዲሁም ብሌን ዮሴፍ የሙዚቃ መምህርት እና ባለሞያን አነጋግረናል።
ሙሉ መረጃ ለማግኘት በእንግሊዘኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራምን ያዳምጡ:
From the publisher's feed