Drum of Changes

Drum of Changes

Download on the App Store

Drum of Changes episodes

  • የጋራ ሀብቶች እና የጋራ ዕጣ ፈንታዎች፦ ሉዓላዊነትን እና ትብብርን እንደገና ማጤን በአፍሪካ

    "አፍሪካውያን ሉዓላዊነትን የምንገልፅበት እና የምንረዳበት መንገድ ምዕራባውያን በ'ዌስታፋሊያ' ሰምምነት መሰረት ከሚነግሩን የሉዓላዊነት እሳቤ የተለየ ነው።[...] አፍሪካውያን የወረስነውን የምዕራቡን ዓለም ሉዓላዊነት መንገድ በመተዉ [...] ወደውስጥ መመልከት፣ የጋራ ሀብቶቻችንን በጋራ ስለመጠቀም ማሰብ አለብን።" ሲሉ በጆሃንስበርግ ዩኒቨርሲቲ የአስተዳደር እና የአፍሪካ ጥናት ማዕከል ዳይሬክተር ሰይፈ ታደለ ኪዳኔ (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።

    ዛሬ በድረም ኦቭ ቼንጅስ ቀዳሚ ጥንቅራችን 'አፍሪካ ሀብቶቿን በጋራ ለመጠቀም ትችል ዘንድ ሉዓላዊነትን በተመለከተ ያለውን ምዕራብ ተኮር እሳቤ መተው ስትችል ነው' የሚል መከራከሪያ ከሚያቀርቡት እና በጆሃንስበርግ ዩኒቨርሲቲ የአስተዳደር እና የአፍሪካ ጥናት ማዕከል ዳይሬክተር ሰይፈ ታደለ ኪዳኔ (ዶ/ር) ጋር ቆይታ ያደርጋል። በሁለተኛው የዝግጅታችን ክፍል ደግሞ ከሰሞኑ በአዲስ አበባ የተካሄደውን የከንቲባዎች ምክክር መነሻ በማድርግ የአፍሪካ ከተሞችን እና የእድገት ጉዟቸዉን ይዳስሳል። ለዚህም ከተለያዩ የአፍሪካ አገራት የመጡ እንግዶች ጋር ቆይታውን ያደርጋል።

    በእንግሊዘኛ ቋንቋ የቀረበውን ሙሉ መረጃ ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ:

    1 hr
  • ሩሲያን የመነጠል ሙከራዎች መክሸፋና ከአፍሪካ ጋር የተጠናከረው ሁለንተናዊ ግንኙነት

    "በዩክሬን ውስጥ ምን እየሆነ እንዳለ [አሜሪካኖቹ] ሙሉ በሙሉ እንደሚረዱ እርግጠኛ ነኝ። ምዕራባውያን በተለይም አውሮፓውያን የሞራል ኪሳራ እንዲሁም በወታደራዊ አቅርቦት እና ቴክኖሎጂ አቅማቸው ላይ በዩክሬን ከፍተኛ ኪሳራ እንዳጋጠማቸው ተረድተዋል። የትራምፕ አስተዳደርም በዩክሬን ውስጥ ማን የበላይ እንደሆነ በትክክል ያውቃል። ስለዚህ ስለ ሰላማዊ መፍትሄ በቁም ነገር ማሰባቸው ተገቢ ነው።" ሲሉ በዲላ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነቶች መምህሩ ዳዊት መዝገበ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።

    በድረም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅታችን በቀዳሚነት በጥር 20፣ 2026 (እ.ኤ.አ) የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌይ ላቭሮቭ 2025 ዲፕሎማሲያዊ ግምገማ እና ለ2026 የተያዘውን ውጥን አስመልክተው በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ በዲላ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነቶች መምህር ዳዊት መዝገበ ምልከታቸውን ያጋሩናል። በሁለተኛው ክፍል የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥና የአህጉሪቱን የግብርና ዘርፍ ለማበልፀግ ስለተነደፈ እቅድ እንዳስሳለን። የኢትዮጵያ ግብርና ትራንስፎርሜሽን ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ንጉሴ ማንደፍሮን (ዶ/ር) አነጋግረናል።

    በእንግሊዘኛ ቋንቋ የቀረበውን ሙሉ መረጃ ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ:

    1 hr
  • ኢትዮጵያዊው ዲፕሎማት ከተማ ይፍሩ፦ ለፓን አፍሪካኒዝም እና ለአፍሪካ አንድነት ድርጅት መመስረት ምን ዋሉ ?
    "አባቴ፣ ለኢትዮጵያ ከአፍሪካውያን እህት ወንድሞቻችን የተሻለ አጋር የለም ብሎ ያምን ነበር … አባቴ በአሜሪካን ሀገር በትምህርት ላይ ሳለ ጥቁር በመሆኑ ብቻ የደረሰበትንም አልረሳም … እነዚህ ሁኔታዎች የፓንአፍሪካኒዝም እንቅስቃሴ ላይ እንዲበረታ አድርገዉታል"- ሲሉ መኮንን ከተማ ይፍሩ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።

    በዛሬዉ ድረም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅታችን በቀዳሚነት ታላቁን ኢትዮጵያዊ ዲፕሎማት ከተማ ይፍሩን እንዘክራለን። ለዚህም በቅርቡ "ከተማ ይፍሩ፡ የሰላም፣ የእድገት እና የአፍሪካ አንድነት ሻምፒዮን" በሚል ርዕስ አባታቸዉን የሚዘክር መጽሐፍ ያሳተሙት ልጃቸው አቶ መኮንን ከተማ ይፍሩ እንግዳችን ናቸው። ሁለተኛው ጥንቅራችን ደግሞ፣ በቅርቡ 75ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን ያከበረው አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲን ጉዳዩ አድርጎታል። ለዚህም በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ ጥናት ተቋም የኢትዮጵያ ታሪክ እና ማህበረሰብ ጥናት ማዕከል ኃላፊ የሆኑትን ዘላለም ተፈራን (ዶ/ር) አነጋግረናል።



    ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ:



    1 hr
  • አፍሪካ የቆዳ ማንጫ ቅባቶን የመጠቀም ልማድ ማሻቀብ፣ መንስኤዎቹ እና ማህበራዊ መዘዞቹ
    “አፍሪካውያን የቆዳ ማንጫ ቅባቶችን እንዲጠቀሙ ከሚገፋፉ ምክያቶች መካከል የምዕራቡ ዓለም የውበት መስፈሪያ የራሱን አስተዋፅኦ አድርጓል[…]ምርቶች እንዲሸጡላቸውም በማህበራዊ ሚዲያ የውበት መስፈርትን የሚያወጡ ዓለም አቀፍ ተቋማትም አሉ” ሲሉ በአለርት ሆስፒታል የቆዳ እና አባላዘር ሕክምና ስፔሻሊስት እንዲሁም በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተባባሪ ፕሮፌሰር የሆኑት ዶክተር አኒሳ በፈቃዱ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።

    በዛሬው የድረም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅታችን በመላው አፍሪካ፣ የቆዳ ማንጫ ቅባቶችን የሚጠቀሙ ዜጎች ቁጥር እየጨመረ መማጣቱን በማንሳት ጤና እና አጠቃላይ ማህበረሰቡ ላይ የሚያስከትለውን ቀውስ እንቃኛለን። በዚህ ወሳኝ ጉዳይ ዙሪያ ሞያዊ ምልከታቸዉን እንዲያጋሩንም በአለርት ሆስፒታል የቆዳ እና አባላዘር ሕክምና ስፔሻሊስት እንዲሁም በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተባባሪ ፕሮፌሰር የሆኑት ዶክተር አኒሳ በፈቃዱን አነጋግረናል። በሁለተኛው ጥንቅራችን ደግሞ ከ 12,000 ዓመታት በኋላ እንደፈነዳ የተነገረለትን የሃይሊ ጉቢ እሳተ ገሞራ በተመለከተ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጂኦፊዚክስ፣ የጠፈር ሳይንስ እና የስነ ፈለክ ተቋም ዳይሬክተር የሆኑትን ፕሮፌሰር አታላይ አየለን አነጋግረናል።

    ሙሉ መረጃዉን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ ፡

    1 hr
  • የእስራኤል እውቅና ለሶማሊላንድ ፦ የሶማሊያ ተቃዉሞ እና የቀጣናው እጣፈንታ

    ሶማሌላንድ ከእስራኤል ያገኘችው የሀገርነት እውቅና በተወሰነ ደረጃ ህጋዊነትን እንድታገኝ ቢያስችላትም፣ ከሶማሊያ፣ ከአፍሪካ ህብረት እና ከሌሎች ሀገራት እየተሰጠው ያሉ ምላሾች በመጭው ጊዜያት የግዛት አንድነት ጥያቄዎች ማዕከላዊ ሆነው እንደሚቆዩ ያሳያል።

    "እስራኤል ለሶማሊላንድ የሰጠችው እውቅና ከዓለም አቀፍ ሕግ ይልቅ፣ ፖለቲካዊ አንድምታው ጎልቶ ይታያል … በቀጣናው ሶማሊላንድ አዲስ ተዋናይ ሆና ብቅ ልትል ትችላለች፣ አዲስ ዓይነት የኃይል አሰላለፍም ሊፈጠር ይችላል" ሲሉ ጠበቃ፣ የዓለም አቀፍ ሕግ ባለሞያ አንዷለም በእውቀቱ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።

    በዛሬው የድረም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅታችን ሦስት ጉዳዮችን እንመለከታለን። በቀዳሚው ጥንቅራችን ከሰሞኑ እስራኤል ለሶማሊላንድ የሰጠችዉን የሀገርነት እውቅና እንስተን አንድምታዎቹን እንመለከታለን። ለዚህም ኢትዮጵያዊውን ጠበቃ እና የዓለም አቀፍ ሕግ ባለሞያ አንዷለም በእውቀቱን አነጋግረናል። በሁለተኛው ጥንቅራችን ደግሞ የዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂን በማንሳት በኢትዮጵያ ዲጂታል ኢኮኖሚን ለመገንባ የሚኖረዉን ሚና እንቃኛለን። ወርቁ ጋቸና (ዶ/ር) የኢትዮጵያ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ተቋም ዋና ዳይሬክተር፣  የሺዓለም ገዛኸኝ (ዶ/ር) በደብረ ብረሃን ዩኒቨርሰቲ የኮምፒዉተር ሳይንስ ትመህርት ክፍል ረዳት ፕሮፌሰር፣ እና አቶ አበበ ፀጋዬ በደብረ ብረሃን ዩኒቨርሰቲ የአይሲቲ ዋና ዳይሬክተርን አነጋግረናል። በመጨረሻው ጥንቅራችን ደግሞ የኢትዮጵያ አየር ኃይል 90ኛ ዓመት የምስረታ በዓል አከባበር ዝግጅትን መነሻ አድርገን ብርጋዴር ጄኔራል መሰረት ጌታቸው፣ የኢትዮጵያ አየር ኃይል የመጀመሪያ ዲቪዚዮን የከባድ ጥገና ማዕከል ምክትል አዛዥ ለስፑትኒክ አፍሪካ የሰጡትን ገለፃ ወደእናንተ እናደርሳለን።

    ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ ፡

    1 hr
  • የአውሮፓ የከሸፈው ቁማር እና የሩሲያ ድል ፡- በፑቲን ወሳኙ ዓመታዊ ንግግር

    “ፕሬዝዳንት ፑቲን አሁን ኢኮኖሚውን በማረጋጋት እና ተጨባጭ እድገት ወደሚታይበት ደረጃ ማድረስ ችለዋል … ዛሬ በሩሲያ እያየን ያለነው የኢኮኖሚ ለውጥ ብቻ ሳይሆን፣ የፑቲንን አመራር ተጽእኖ ፈጣሪነት ነው” ሲሉ ዓለም አቀፍ የፖሊሲ አማካሪው ቆስጠንጢኖስ በርሁተስፋ (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።


    አዉሮፓዉያን ዛሬም በከሸፈ የቁማር መንገዳቸው ቢቀጥሉም የሩስያ ገናና ድል ግን ቀጥሏል። 

    ”አውሮፓውያን በውጭ አገራት የተቀመጡ የሩሲያን ንብረት እና ገንዘብ በመውሰድ ለዩክሬን ለመስጠት ማሰባቸው የደቡቡ ዓለም ከአውሮፓውያን ጋር የሚኖረውን አሰራር እንዲያጤን ቀጥተኛ መልዕክት የሚያስተላልፍ ነው” ያሉት ደግሞ በኢትዮጵያ ፐብሊክ ሰርቪስ ዩቨርሲቲ የዲፕሎማሲ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት መምህሩ አንዳለ ንጉሴ ናቸው።

     በዛሬው የድረም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅታችን የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን የዓመቱ ማጠቃለያ መግለጫ ወቅት ያነሷቸዉን ጉዳዮች መነሻ በማድረግ ከዓለም አቀፍ ጂኦፖለቲካ እና ከደቡብ ለደቡብ ትብብር አንፃር የሚኖራቸዉን አንድምታዎች እንቃኛለን። ለዚህም ዓለም አቀፍ የፖሊሲ አማካሪዉን ቆስጠንጢኖስ በርሁተስፋን (ዶ/ር) እና በኢትዮጵያ ፐብሊክ ሰርቪስ ዩቨርሲቲ የዲፕሎማሲ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት መምህሩን አንዳለ ንጉሴን አነጋግረናል።



    ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ:


    1 hr
  • የናሬንድራ ሞዲ የኢትዮጵያ ጉብኝት አንድምታ እና የሩሲያ በዘመናት የተፈተነ ከጭቁኖች ጋር የመቆም ታሪክ

    “የብሪክስ መድረክ ለአባል ሀገራት የበለጠ ስትራቴጂካዊ፣ ዘላቂ እና የጋራ ጥቅምን መሰረት ያድረጉ ግንኙነቶችን ለመመስረት እድል ይሰጣል። ከዚህ አናፃር የኢትዮጵያ እና የህንድ ግንኙነት ከዚህ ማዕቀፍ በእጅጉ ይጠቀማል” ሲሉ በኢትዮጵያ ፐብሊክ ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ የፖሊሲ ጥናት መምህሩ ሙከረም ሚፍታህ (ዶ/ር) ሲሉ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።

    የዛሬው የድረም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅታችን የሕንዱን ጠቅላይ ሚኒስቴር ናሬንድራ ሞዲ የኢትዮጵያ ጉብኝት ከብሪክስ አገራት ትብብር አንፃር ቀዳሚ ጉዳዩ አድርጎ ይቃኛል። ለዚህም በኢትዮጵያ ፐብሊክ ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ የፖሊሲ ጥናት መምህሩ ሙከረም ሚፍታህን (ዶ/ር) አነጋግረናል። በሁለተኛው ጥንቅራችን የሶቪየት ኅብርት ለአፍሪካ የነፃነት ምን ሚና ነበራት ሲል ይጠይቃል ፣ ዛሬም ድረስ የቀጠለውን አጋርነትም በሰፊው እንዳስሳለን።

    “ሩሲያ በታሪኳ በሙሉ በአፍሪካ ሕዝቦች ጭቆና ውስጥ ተሳትፋ አታውቅም ካለማወቋም በላይ እራሷን በዓለም ዙሪያ ለተጨቆኑ ሕዝቦች ድምፅ እንዲሁም የትግላቸው ደጋፊ ነች” ሲሉ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መምህር እና የታሪክ ተመራማሪ ዘላለም ተፈራ (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።

     ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ:

    1 hr
  • የጥቁር ህዝቦች የካሳና ፍትህ ጉዳይ ፦ አውሮፓዉያኑ እንዲነሳ የማይፈልጉት ጥያቄ ለምን ሆነ ?
    "ብዙዎቻችን ከየት እንደመጣን ምንም ባናውቅም፣ ስደተኞች ግን አይደለንም። በእገታ የተወሰድን አፍሪቃውያን ነን። አያት ቅድመ አያቶቻችን ማንነታቸዉን ሳያውቁ ወደ መቃብር ወርደዋል። የ'ባሪያ' ልጆች መሆናችንን ብቻ ነው የተማርነው። ይህም ለሕዝባችን ብዙ ግራ መጋባት ፈጥሯል፣ የማንነት እጦትን ፈጠሯል"- ሲሉ ጸሐፊ እና የፓንአፍሪካኒዝም አቀንቃኟ ጅኔል ሆይሌት ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።

    በዛሬው የድረም ኦቭ ቼንጅስ ጥንቅራችን፣ የአፍሪካን የቅኝ ግዛት በደልና ፍትህ እንዲሁም የካሳ ጥያቄን እናነሳለን ፡፡ ይሄው ጥያቄ በአውሮፓውያን ዘንድ ከመውያያ አጀንዳነት ለምን እንደሚገፋና ሌሎችንም ጉዳዮችን መነሻ አድርገን ጸሐፊ እና የፓንአፍሪካኒዝም አቀንቃኝ ጅኔል ሆይሌት ጋር በሰፊው እንወያያለን። በሁለተኛው ጥንቅራችን ደግሞ አፍሪካ ከሕገ መንግሥታዊነት፣ ከዳኝነት ነፃነት ጋር በተያያዘ ያላትን ቀጣይ ትግል እና በዓለም አቀፍ የወንጀል ፍርድ ቤት ዙሪያ ስላለው ሰፊ ክርክር እንመለከታለን። ዶ/ር ጌታቸው አሰፋ፣ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሕግ ተባባሪ ፕሮፌሰር እና አቶ ቸርነተት ሆርዶፋ፣ የአፍሪካ ሕገ መንግሥታዊ ዳኝነት ኮንፈረንስ አባልን አነጋግረናል።

    ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ:

    1 hr
  • ድርብ መስፈርት ፡- የዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት እና የአፍሪካ የፍትህ ጥያቄ

    ‘‘ዓለም አቀፉ የጦር ወንጀለኞች ፍርድ ቤት በሶሪያ ፣ ኢራቅና አፍጋኒስታን ውስጥ የተፈጸሙ ወንጀሎች፣ በብሪታኒያ በተፈጸሙ ወንጀሎች ዙሪያ ተጀምረው የነበሩ ምርመራዎች በአሜሪካ ጣልቃ ገብነት በድንገት እንዲቋረጡ ሆነዋል፡፡ ለምን ብለህ ብትጠይቃቸው ግን አሳማኝ ምክንያት አይሰጡህም፡፡ ተመሳሳይ ነገሮችን በተለያየ መንገድ የሚዳኝበት መንገድ በጣም የገዘፈ ነው፡፡’’ ሲሉ ኢትዮጵያዊው የህግ ባለሙያና ጠበቃ አንዷለም በእውቀቱ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡

    የዛሬው ድረም ኦፍ ቼንጅስ ዝግጅታችን በሁለት ጉዳዮች ላይ እንወያያለን፡፡ በቀዳሚነት አፍሪካን ማጥቂያ የሆነው በዓለምአቀፉ ወንጀለኞች ፍርድቤት የሚደርስባት አድሏዊ አሰራርና በደልን እንዳስሳለን። ለዚህም የህግ ባለሙያና ጠበቃ አንዷለም በእውቀቱ አብረዉን ቆይታ ያደርጋሉ። በሁለተኛው ጥንቅራችን ደግሞ የአፍሪካ ደራሲያን እና አሳታሚዎች የአህጉሪቱ የባህልና የቋንቋ ሀብቶች ተገቢ እና እውነተኛ እውቅና ያገኙ ዘንድ በአለም አቀፍ መድረኮች ስለሚያሰሟቸው ጥሪዎች እንወያያለን ፤ በጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ የእንግሊዘኛ ቋንቋ እና ስነጽሁፍ መምህር እንዲሁም በዩኒቨርሲቲው የማህበራዊ ሳይንስ እና ስነሰብ ኮሌጅ ዲን አስቻለው ለገሰ (ዶ/ር)ጋር ቆይታ አድርገናል።

     ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ:

    1 hr
  • ከትናንት እስከ ዛሬ ፡ የዓለምአቀፍ ተቋማት አድሏዊነትና የፍትሐዊነት ጥያቄ ከሊግ ኦፍ ኔሽን እስከ ጸጥታው ም/ቤት
    "አፍሪካ እንደገና የተዋቀረ፣ ገለልተኛ፣ ተጠያቂነት የሰፈነበት ዓለም አቀፍ ስረዐት ያስፈልጋታል። የተባበሩት መንግስታት አሁን ባለው አቋም የአፍሪካን ጥቅም የሚያስከብር አይደለም። በእኔ እይታ የተባበሩት መንግስታት፣ በዩናይትድ ስቴትስ የሚጋለብ፣ምዕራባውያን የሚነዱት ፈረስ ነው።" - ሲሉ በዲላ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካል ሳይንስ እና አለም አቀፍ ግንኙነት መምህርና ተመራማሪ የሆኑት አቶ ዳዊት መዝገበ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።

    በዛሬው የድረም ኦቭ ቼንጅስ ጥንቅራችን ፣ በቀዳሚነት አፍሪካ በተባበሩት መንግስታት እና ሌሎች አለም አቀፍ ተቋመት ውስጥ ፍትሃዊ እና እኩል ውክልና ለማግኘት የምታደርገውን ቀጣይነት ያለው ጥረት እንፈትሻለን። ለዚህም በዲላ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካል ሳይንስ እን አለም አቀፍ ግንኙነት መምህርና ተመራማሪ የሂኑትም አቶ ዳዊት መዝገበን አነጋግረናል። በሁለተኛው ጥንቅራችንም ኃይማኖታዊ እና ባህላዊ ትውፊቶችን ጠብቆ ማቆየት ለአፍሪካ፣ ብሎም ኢትዮጵያ እንደ ሩሲያ ካሉ አገራት ጋር ለሚኖራት መልካም ግንኙነት ስለሚኖራቸው ቦታ ደግሞ ሁለተኛው ጥንቅራችን ያስቀኛናል። በዚህ ጉዳይ ያላቸውን ሃሳብ እንዲያጋሩን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የጥናት እና ምርምር ዳይሬክተር የሆኑትን መምህር ዳንኤል ሰይፈሚካኤልን አነጋግረናል።



    ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ:

    1 hr

About Drum of Changes

From the publisher's feed

From the heart of ancient kingdoms to the pulse of modern cities, a new rhythm echoes across the continent. Africa is rising — a formidable force shaping the world’s future. For generations, Africa…